.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ከሌለባቸው ከመጨረሻዎቹ ሃገራት ተርታ መመደቧ ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) ኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ከሌለባቸው የመጨረሻዎቹ አምስት ሃገራት ተርታ እንደምትመደብ ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ የተባለ አለም አቀፍ ተቋም ገለጸ። ተቋሙ የ2017 ጥናታዊ ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ እንደገለጸው ኢትዮጵያ ከ161 ሃገሮች ጋር ስትነጻጸር የሰላምና መረጋጋት እጦትን በተመለከተ 134 ደረጃ ላይ ትገኛለች። በጥናቱ መሰረት ኢትዮጵያ ሰላሟን እያጣቸው የመጣችው በሃገሪቱ የተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ነው። በሃገሪቱ በከፊል በብሄር ...

Read More »

የእርዳታ ምግብ አቅርቦት እጥረትን ተከትሎ 700ሺ ሰዎች ድጋፍ ሳያገኙ መቅረታቸው ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ያጋጠመውን የእርዳታ ምግብ አቅርቦት እጥረትን ተከትሎ በግንቦት ወር እርዳታ ማግኘት የነበረባቸው 700 ሺ አካባቢ ሰዎች ያለምንም ድጋፍ መቅረታቸው ተገልጿል። በዚሁ የምግብ እጥረት ዙሪያ መግለጫን ያወጣው የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ወደ አራት ሚሊዮን የሚሆኑ ህጻናት በከፍተኛ የምግብ ችግር ውስጥ መሆናቸው አስታውቀዋል። ይሁንና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪው በቂ ምላሽ ባለመስጠቱ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ...

Read More »

የድርቅ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ 175 ት/ቤቶች መዘጋታቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መፈናቀላቸውን ተመድ ገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) በኢትዮጵያ እየተባባሰ ያለውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ 175 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውንና ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በአፋር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስር የሚገኙ በርካታ ዞኖች በዚሁ የድርቅ አደጋ ክፉኛ መጎዳታቸውን በድጋሚ ያወሳው ድርጅቱ በምግብ እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ህጻናት ተማሪዎች በመበራከታቸው ትምህርት ቤቶቹ ሊዘጉ መቻላቸውን ገልጿል። ከአደጋው ...

Read More »

በግንቦት 20 በአል ሰበብ በተጠራው የመኮንኖች ስብሰባ ላይ የተነሱት ጥያቄዎች የመከላከያ አዛዦችን አሳስቧቸዋል።

ግንቦት ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንቦት 20 በአልን ምክንያት በማድረግ ለመከላከያ አባላት ገለጻ በተደረገበት ወቅት የጦር መኮንኖች ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎችና የሰነዘሩዋቸው አስተያየቶች ከዚህ በፊት ያልተለመዱና ያልታዩ በመሆኑ፣ ወታደራዊ አዛዦችን አሳስቧል። በቅርቡም በመካለከያ ውስጥ አዲስ ጥልቅ ተሃድሶ ሊጠራ እንደሚችል ምንጮች ተናግረዋል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ የመከላከያ መኮንኖች ግንቦት20ን በማስመልከት አገሪቱ ስለምትገኝበት ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ተደርጎላቸው ...

Read More »

በሳውድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሬታቸውን እየገለጹ ነው

ግንቦት ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በሳውድ አረቢያ ለአመታት በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የቆዩ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ በቂ አገልግሎት እየሰጠን አይደለም ብለዋል። ለተመላሽ ኢትዮጵያውያን የትራንስፖርት አገልግሎት ከማመቻቸት አንስቶ እቃዎቻቸውን ከቀረጽ ነጻ የሚያስገቡበት ሁኔታ እንደሚመቻችላቸው በመንግሰት መገናኛ ብዙሃን ሲገለጽ ሰንብቷል። የተለያዩ የኢህአዴግ መሪዎችና የሃይማኖት አባቶች ሳይቀሩ ከዚህ ቀደም በተመለሱት ዜጎች ...

Read More »

ኢንተርኔት መዘጋቱን ተከትሎ የመንግስትና የፓርቲ የመገናኛ ብዙሃን ሳይቀሩ ዜናዎችን ማውጣት አቆሙ

ግንቦት ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ የተዘጋውን የኢንትርኔት አገልግሎት ተከትሎ የውጩን ማህበረሰብ ስለአገሪቱና ስለመንግስቱ መልካም ገጽታ እንዲኖረው በሚል ዘገባዎችን የሚያቀርቡ የመንግስት ሚዲያዎች፣ የፓርቲ ሚዲያዎችና በፌስቡክ፣ በቲውተርና በድረገጻቸው የገዢውን ፓርቲ አወንታዊ ገጽታ ሲያቀርቡ የነበሩ ሁሉ እንቅስቃሴ አቁመዋል። የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ከሆኑት መካከል የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ የኢንተርኔት ገጻቸው የተዘጋ ...

Read More »

የኮሎኔል አስናቀ እንግዳ የቀብር ስነስርዓት በዩኤስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ተፈጸመ

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2009) የኮሎኔል አስናቀ እንግዳ የቀብር ስነስርዓት በዩኤስ አሜሪካ ዋሽንግተን ተፈጸመ። በ5 አመታቱ የአርበኝነት ተጋድሎ ተሳታፊው የነበሩትና ሃገራቸው በውትድርና ውጊያ ያገለገሉት ኮሎኔል አስናቀ እንግዳ በ 103 አመታቸው ያረፉት ግንቦት 21, 2009 አም ነበር። ከአባታቸው ከአቶ እንግዳ ገ/ማሪያም እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ውቤቴ ገ/ስላሴ በጎንደር ክፍለ ሃገር ደብረታቦር አውራጃ አየር ማሪያም ደብር ጥር 7 ቀን 1906 አም የተወለዱት ኮሎኔል ...

Read More »

ለተመድ ሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባልነት የሚመረጡ ሃገራት የሰብዓዊ መብት አያያዛቸው ግምት ውስጥ መግባት እንደሚገባው ተገለጸ

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2009) ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባልነት የሚመረጡ ሃገራት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ታሪካቸው ግምት ውስጥ መግባት እንደሚገባው አለም አቀፍ ምሁራን አሳሰቡ። የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ የፌታችን ጥቅምት ወር ሁለት አዳዲስ አባል ሃገራትን ለምክር ቤት ለመምረጥ ልዩ ስብሰባን እንደሚያካሄድ ዲቬክስ የተሰኘና በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰራ መጽሄት ዘግቧል። ይሁንና ጉባዔው የአባል ሃገራትን ምርጫ ሲያካሄድ የእጩ አገራት ...

Read More »

የአዲስ አበባ አበባ ቀላል ባቡር በኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ሳቢያ ተስተጓጎለ

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2009) የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር አገልግሎት በኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት መቆራረጥ ምክንያት ስራው መስተጓጎሉን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት አስታወቀ። የኤሌክትሪክ አቅርቦቱ ችግር የማይፈታ ከሆነ ድርጅቱ ተጠባባቂ የሃይል ምንጭ የሆነው ጄኔረተር ለመግዛት እቅድ መኖሩን የህዝብ ግንኙነት ሃላፌ አቶ አወቀ ሙሉ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የከተማዋ ቀላል የአዲስ ባቡር አገልግሎት ከቻይና መንግስት በተገኘ 475 ዶላር ሚሊዮን ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠበትን ምክንያት ለመግለፅ ፈቃደኛ አለመሆኑን ሃሙስ ዘገበ

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2009) የዜና አውታሩ በርካታ የመንግስት ተቋማት ድረ-ገጾችን ለመጎብኘት ሙከራ ቢያደርጉም ሳይሳካለት መቅረቱን በአገልግሎቱ መቋረጥ ቢቢሲ ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። የእጅ ስልክን ጨምሮ መደበኛ የብሮድባንድ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ማረጋገጥ እንደቻለ የብሪታኒያው ማሰራጫ ጣቢያ ገልጿል። ባለፈው አመት የብሄራዊ ፈተና አፈትልኮ መውጣትን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ተደርጎ እንደነበር ያወሳው የዜና ማሰራጫው በርካታ አካላት ጉዳቱ ተመሳሳይነት ሊኖረው እንደሚችል ቢገልፅም በመንግስት ...

Read More »