ኢሳት (ግንቦት 28 ፥ 2009) የደቡብ ሱዳን የጎሳ መሪዎችና የፓርላማ አባላት ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳንና አማጺ ቡድን መካከል ከሁለት አመት በፊት የተደረሰውን የሰላም ስምምነት በአዲስ መልክ እንዲቀጥል ለማድረግ ገለልተኛ አይደችም ሲሉ ተቃውሞ አቀረቡ። የኢትዮጵያ መንግስት የፊታችን ሰኞ በኢጋድ አማካኝነት በደቡብ ሱዳን ላይ የሚመክር ጉባዔ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ጥሪ ማቅረቡን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ሰኞ ዘግቧል። ይሁንና ኢትዮጵያ ላቀረበችው ጥያቄ ምላሽ የሰጡ የደቡብ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት ሊሻሻል አይችልም ሲሉ ሌ/ጀኔራሊ ጻድቃን ገ/ተንሳይ ገለጹ
ኢሳት (ግንቦት 28 ፥ 2009) በፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው የኤርትራ መንግስት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት ሊሻሻል እንደማይችል ሌ/ጀኔራሊ ጻድቃን ገ/ተንሳይ ገለጹ። በኤርትራ ህዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል ሲያበቃ ግንኙነቱ ጤናማ እንደሚሆንም ተስፋቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ስለሚፈጸመውና አለም አቀፍ ተቋማት ጭምር ስለሚያጋልጡት የሰብዓዊ መብት ረገጣ ምንም ሳይጠቅሱ አልፈዋል። በአንጋፋው የህወሃት ታጋይና የቀድሞ ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጻድቃን ገ/ተንሳይ ከመንግስታዊው አዲስ ...
Read More »የባህር ዳር ከነማ ክለብ ለኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ
ኢሳት (ግንቦት 28 ፥ 2009) በመቀሌ እግር ኳስ ቡድን እና ደጋፊዎች በደል ደርሶብን እያለ አለአግባብ የሆነ ውሳኔ ተወስኖብናል ያለው የባህርዳር ከነማ ክለብ ለኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ። የክለቡ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ በማምራት በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አንቀጽ 95 መሰረት አስተናጋጅ አገር እና ክለብ ወይም ደጋፊዎች ሲያጠፉ በፎርፌ ሊሸነፍ ሲገባ ውሳኔው የተገላቢጦሽ የባህርዳርን ክለብ የጎዳ ነው ሲሉ ይግባኝ ...
Read More »ህወሃት ኢህአዴግ ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች ወደ ሰሜን ጎንደር እያንቀሳቀሰ ነው
ግንቦት ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች በተደረጉ አውደ ውጊያዎች ተደጋጋሚ ሽንፈትን ያስተናገደው ገዥው ህወሃት ኢህአዴግ ተጨማሪ ወታደሮችን በሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች በመጫን ማጓጓዙን ቀጥሏል። ምንጮች እንዳሉት ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሚያርፉበት ወቅት እንዳያስታዋሉት አብዛሃኞቹ እድሜያቸው ለአቅመአዳም ያልደረሱ በግምት ከ17 ዓመት በታች የሚሆናቸው ለጋ ወጣቶች መሆናቸውንም ተናግረዋል። እነዚህ አዲስ ምልምል ወታደሮች ከወታደራዊ ...
Read More »አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በእስራኤል ድንገተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው
ግንቦት ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በአገራቸው ጉዳይ ላይ ለማነጋገር ወደ እስራኤል የተጓዙት አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ያልታሰበ ድንገተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው። የህወሃት/ኢህአዴግ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎችን ለይቶ በሚስጥር በመጥራት ለማወያየት ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ተሰብሳቢዎች በስም ጥሪ እንዲገቡ ተደርገዋል። በአገራችን ጉዳይ ያገባናል ያሉ ዜጎች ወደ ስብሰባው አዳራሽ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው ሲሆን ...
Read More »በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት ነጋዴዎች ክፉኛ መጎዳታቸውን አስታወቁ
ግንቦት ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብሔራዊ ፈተናን ምክንያት በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ የንግድ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል። በኢንተርኔት መቋረጥ ገቢያቸውን በማጣት ባንኮች፣ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ የመረጃ ተቋማት ጨምሮ የሆቴል አገልግሎት ዘርፎች በቀዳሚነት ተጠቂ ከሆኑት ውስጥ ይጠቀሳሉ። በኢንተርነእት መቋረጥ ሳቢያ የገቢና ወጪ ንግድ የገንዘብ ልውውጥ ላይ ከፍተኛ እክል ተፈጥሯል። ድርጅቶቹ ላጋጠማቸው ኪሳራዎች በኢትዮ ቴሌኮምም ...
Read More »ከሳኡዲ አረቢያ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን እየተጉላሉ ነው
ግንቦት ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ሕገወጥ ስደተኞች ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ የውጭ አገር ዜጎች አገርቷን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው። የተለያዩ አገራት በኤንባሲዎቻቸውና በቆንስላዎች አማካኝነት ከቀረጥ ነጻ እቃዎቻቸውን እንዲያስገቡ ለዜጎቻቸው እገዛ እያደረጉ ነው። ፈቃደኛ ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ግን ወደ ኤንባሲዎቸው በመሄድ ለመመለስ ቢጠይቁም የጉዞ ሰነዶችን በአፍጣኝ ለማግኘት ተቸግረዋል። ...
Read More »የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች አሰግድ ተስፋዬ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ግንቦት ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በልዩ የእግር ኳስ ክህሎቱ በመላው ኢትዮጵያዊያን እግር ኳስ አድናቂዎች ተወዳጁ አሰግድ ተስፋዬ ቅዳሜ ግንቦት 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በድንገት መታጠቢያ ቤት ውስጥ በመውደቁ ሕይወቱ አልፏል። አሰግድ ተስፋዬ በ1962 ዓ.ም በድሬደዋ ከተማ ደቻቱ ውስጥ ተወልዶ በ47 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ዓመለ ሸጋው አሰግድ ተስፋዬ ለድሬደዋ ጨርቃጨርቅ፣ መድህን ድርጅት፣ ...
Read More »አሜሪካ በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የአለም ሙቀትን ለመቀነስ ከተደረሰው ስምምነት መውጣቷን ይፋ አደረገች
ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሃገራቸው ከሁለት አመት በፊት በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ የአለም ሙቀትን ለመቀነስ ከተደረሰው ስምምነት መውጣቷን ይፋ አደረጉ። የፓሪስ ስምምነት በመባል የሚታወቀው ይኸው አለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነት በ187 ሃገራት መካከል ተቀባይነትን አግኝቶ የነበረ ሲሆን፣ ዕርምጃውም የአለም ሙቀትን በሁለት ዲግሪ ሴንቲግሬድ ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ታውቋል። ይሁንና በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት የፓሪሱን ስምምነት ውድቅ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተው ...
Read More »የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ተጠየቀ
ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2009) በቀጣዩ ሳምንት ጠቅላላ ጉባዔውን የሚያካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በኢትዮጵያ ስላለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ውሳኔዎች እንዲያስተላልፍ አለም አቀፍ የሰብዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥያቄን በድጋሚ አቀረቡ። ሂማን ራይትስ ዎች፣ ፍሪደም ሃውስ ኢንተርናሽናል፣ ፌዴሬሽን ፎር ሂማን ራይትስ የተሰኙና ሌሎች ተቋማት ምክር ቤቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ውሳኔ እንዲተላለፍ ጠይቀዋል። ከቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ ለ15 ...
Read More »