.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢትዮጵያ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች 8 ሚሊዮን መድረሳቸውን ተመድ አስታወቀ

ሰኔ ፰ ( ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም /World Food Program/ በኢትዮጵያ በደረሰው ድርቅ ምክንያት ከሰኔ ወር መቋጫ ጀምሮ ለርሃብ ተጋላጭ የሆኑና አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጭማሪ አሳይቷል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ከሆነ 7.8 ሚሊዮን የነበረው አፋጣኝ የእለት እረዴት ጠባቂዎች ቁጥር ወደ 8 ሚሊዮን ማሻቀቡን አስታውቋል። ይህም 8 ሚሊዮን በሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ...

Read More »

የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሃውልት ሙሉ በሙሉ ፈረሰ

ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009) የታዋቂው የህክምና ባለሙያ፣ የመአህድ መስራችና ፕሬዚደንት የነበሩት የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሃውልት ሙሉ በሙሉ ፈረሰ። አፅማቸው ወዴት እንደሚወሰድ የታወቀ ነገር የለም። የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ አቡነ ሳዊሮስ ስለጉዳዩ እንደማያውቁ ለኢሳት ገልጸዋል። ከሳምንታት በፊት የመካነ መቃብሩን አጥር በማፍረስ የተጀመረው እንቅስቃሴ ማክሰኞ ሰኔ 6 ፥ 2009 ሙሉ በሙሉ ሃውልቱን በማፍረስ ተጠናቋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ፣ አጽማቸው ከመካነ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የኮንትሮባንድ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቷል ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ኮንትሮባንድ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋቱንና የሃገሪቱም የውጭ ንግድ እያሽቆለቆለ መገኘቱን የንግድ ሚኒስትሩ ገለጹ። የመንግስት ባለስልጣናት ከፍተኛ የስልጣን መዋቅር እስከታችኛው ዕርከን በኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው ተዋናይ መሆናቸውም ከንግድ ሚኒስትሩ መግለጫ መረዳት ተችሏል። በሳምንቱ አጋማሽ የመስሪያ ቤታቸው የ11 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ማክሰኞ ዕለት ለፓርላማ ያቀርቡት አዲሱ የንግድ ሚኒስትር ዶ/ር በቀለ ቡላዶ ችግሩ ስር የሰደደ በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ...

Read More »

የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ (ሜይቴክ) ላላከናወነው ግንባታ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ ተፈጸመለት

ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009) በህወሃት የጦር መኮንንኖች የሚመራው የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ (ሜይቴክ) ላላከናወነው ግንባታ ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ክፍያ ተፈጸመለት። በህወሃት የጦር ጄኔራሎች የበላይ አዛዥኘት ክፍያውን የወሰደው ሜቴክ ከ 3 አመት በፊት ግንባታውን አጠናቅቆ ለማስረከብ ውል ስለተፈረመበት ያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ መሆኑ ከዋና ኤዲተሩ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።  ሜቴክ ማዳበሪያ ፋብሪካውን ሰርቶ በማጠናቀቅ ማስረከብ የነበረበት በ 2006 አ’ም ቢሆንም አስከ ...

Read More »

የ2010 አጠቃላይ በጀት ውስጥ 100 ቢሊዮን ብር የሚሸፈነው በውጭ ብድርና ዕርዳታ እንደሚሆን ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009) የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መ/ቤት የ2010 ጠቅላላ የበጀት ወጪ 321 ቢሊዮን ብር አቀረበ። በጀቱ 54 ቢሊዮን ብር ጉድለት የታየበት ሲሆን፣ 100 ቢሊዮን ብር የሚሸፈነው በውጭ አገር እና በአገር ውስጥ ብድርና ዕርዳታ እንደሚሆን ተገልጿል። የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ የ2010 የበጀት ዕቅዱን ለፓርላማ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከተያዘው አመት ጋር ያሉትን ልዩነቶች አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ...

Read More »

በለንደን ከተማ በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ አደጋ 12 ሰዎች ሞተው 68 ሌሎች ቆሰሉ

ኢሳት (ሰኔ 7 ፥ 2009) በእንግሊዝ አገር በምዕራብ ለንደን ከተማ በአንድ ህንጻ ላይ በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ 12 ሰዎች መሞታቸውንና 68 ሌሎች ደግሞ ቆስለው ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ ተገለጸ። በአደጋው የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል። በለንደን የ24 ፎቅ ርዝመት ባለው ግሬንፈል ታወር መኖሪያ ህንጻ ላይ የእሳት ቃጠሎ የተከሰተው ነዋሪዎቹ ተኝተው በነበረበት ረቡዕ እኩለ ሌሊት ላይ መሆኑን የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።  ...

Read More »

በወልቂጤ የብሄር ግጭት ይነሳል የሚል ስጋት መኖሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቆሙ

ሰኔ ፯ (ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጉራጌ ዞን ዋና ከተማ ወልቂጤ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ላይ አንድ የቀቤና ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑ ሴት መገደላቸውን ተከትሎ አቶ መስፍን አዳነ የተባሉ የአማራ ብሄር ተወላጅ በጥርጣሬ ከተያዙ በሁዋላ በቡድን የተደራጁ ሰዎች ወደ እስር ቤት ገብተው ግለሰቡን የገደሉት ሲሆን፣ ፖሊሶች ቆመው እያዩም መኖሪያ ቤቱ እንዲቃጠል ተደርጓል። የአካባቢው ፖሊሶች እጃቸው እንዳለበት የሚያመለክቱ መረጃዎች ...

Read More »

የህወሃት የግንባታ ኩባንያዎች የሚሰሩዋቸው ግንባታዎች በጥራት ችግርና በሙስና እየተወነጀሉ ነው

ሰኔ ፯ (ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት የግንባታ ድርጅቶች በአማራ ክልል የሚሰሩዋቸው የግንባታ ስራዎች የጥራት ችግር ያለባቸው እንዲሁም ከተያዘላቸው የማጠናቀቂያ ጊዜ በላይ በማዘግየት በህብረተሰቡ ላይ ችግር እየፈጠሩ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በክልሉ የህንጻ ግንባታና መንገድ ስራዎችን በስፋት የተቆጣጠሩት የህወሃት ድርጅቶች ስራቸውን ለምን እንዳላጠናቀቁ በአካባቢው ነዋሪዎችና አመራሮች ሲጠየቁ፣ በማዕከላዊ ደረጃ የሚገኙ የህውሃት አመራሮችን እንደመከታ በመጥራት በቂ መልስ እንደማይሰጡ ...

Read More »

የእንግሊዝ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎችን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ

ሰኔ ፯ (ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎች የደህንነት ዋስትናቸውን በተመለከተ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል። ምንም እንኳ ከ10 ቀናት በሁዋላ ተቋርጦ የነበረው የኢንትርኔት አገልግሎት መልሶ ቢመጣም፣ አገልግሎቱ ያለምንም ማስጠንቀቂያ በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ እንደሚችል በማስጠንቀቅ፣ ዜጎቹ ሌሎች የስልክ የመገናኛ አማራጮችን እንዲጠቀሙ አስጠንቅቋል። የእንግሊዝ ኢምባሲ በኢንተርኔት መቆራረጥ የተነሳ በቂ አገልግሎት ...

Read More »

የአሜሪካ መንግስት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጣ

ኢሳት (ሰኔ 6 ፥ 2009) የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጣ። ሚኒስቴሩ ማክሰኞ ባወጣው ማሳሰቢያ እንዳለው አስቸኳይ ጊዜ ከታወጀበት ከመስከረም 2009 በኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ ብዛት ያላቸው ሰዎች ለእስርና ለእንግልት መዳረጋቸውን ገልጿል።  ሚኒስትሩ በድጋሚ በድረገጹ ያወጣው የጉዞ ጥንቃቄ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀጣይ ከተደረገበት እኤአ ከ ማርች 2017 ጀምሮ በአማራ ክልል ...

Read More »