.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ሠራተኞች በቻይናውያን አሠሪዎቻቸው ድብደባ ደረሰባቸው

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሀዋሳ የቻይናውያን ኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሠራተኞች በቻይናውያን አሰሪዎቻቸው የከፋ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው በተለይ ለኢሳት ገለጹ። የፕሮጀክቱ ሠራተኞች እንደገለጹት በአሰሪዎቻቸው የከፋ ድብደባ የተፈጸመባቸው ላለፉት ወራት ያልተከፈላቸውን ደመውዝ እንዲከፈላቸው በጋራ ጥያቄ በማቅረባቸው ነው። “የሠራንበት የላባችን ዋጋ ሊከፈለን ይገባል። የሠራንበትን ደመወዝ ባለማግኘታችን ቤተሰቦቻችን ችግር ላይ ወድቀዋል” በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም ...

Read More »

በምስራቅ ኢትዮጵያ በምግብ እጥረት የተጠቁ ሕጻናት አስር እጥፍ መጨመሩን እና 67 ሕጻናት በርሃብ መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ኢትዮጵያ በኦጋዴን ዶሎ ዞን ያለው የርሃብና ያልተመጣጠነ ምግብ እጥረት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን በአካባቢው የተሰማራ የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ። ”ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ በዶሎ ዞን ነዋሪ የሆኑ ታዳጊ ሕጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋላጭ ሆነዋል። የሕክምና ቡድናችን ባለፉት አስር ዓመታት በአካባቢው የሥራ ቆይታችን እንደዚህ ዓይነት ዘግናኝ ...

Read More »

አቶ ንዋይ ገብረአብ ለአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነርነት ታጩ

ሰኔ ፲፱( አሥራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃቱ ባለስልጣን ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅትን እንዲመሩ በተመረጡ 2 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ፣ አቶ ንዋይ ገብረአብን ለአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ቦታ በእጩነት አቅርቧል። የአፍሪካ ህብረት ሹመት በመንግስታት ድጋፍ የሚገኝ በመሆኑ፣ አቶ ንዋይ ቦታውን የመውሰድ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ህወሃት አዲስ አበባ በገባ በአመቱ የአቶ ...

Read More »

የአርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ፣ የወያኔ ስርዓት ባንዳዎችን የሀብት ማከማቻ ድርጅቶችን የማፅዳት ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ።

ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ የሰሜን ዕዝ ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 4:00 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ ቆላድባ አካባቢ ልዩቦታው ወንፈላ በተባለው የሚገኝ የገዥው ፓርቲ ንብረት ላይ ጥቃት ፈፀሟል። ንብረትነቱ የዳሽን ቢራ በሆነ መጋዝን ላይ በተፈፀመው በዚህ ጥቃት የኦክስጅን ጋዝ መጋዝን ከነ ሙሉ ዕቃው ሲቃጠል፣ የጂኒሪተር ክፍሉበከፊል ቃጠሎ ደርሶበታል። ...

Read More »

የኮሚሽነርነት ማዕረግ የመጣለት የምርመራ ኃላፊ አልፈልግም ብሎ ሥራውን ለቀቀ

ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ሥራቸውን በፈቃዳቸው በሚለቁ ፖሊሶችና ሹመኞች ውዝግብ እየታመሰ ነው። በተለይ ሰሞኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የአቶ ዓለምነው መኮነን አጃቢ በባህር ዳር ግራንድ ሆቴል መገደላቸውን ተከትሎ እስከ ኮማንደር ድረስ ማዕረግ ያላቸው ፖሊሶችና አዛዦች በፈቃዳቸው ከሥራቸው እየለቀቁ ነው። የምዕራብ ጎጃም ዞን የምርመራ ሀኃፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ፓሊስ ...

Read More »

በአዳማ ከተማ ሙሉ ለሙሉ መብራት በመቋረጡ ነዋሪዎቹ ተቸግረናል እያሉ ነው

ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፋብሪካዎች ተዘግተዋል በአዳማ ከተማ ከሃሙስ ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የመብራት አገልግሎት መቁረጡን ተከትሎ ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ በጨለማ መዋጧን ምንጮቻችን አስታውቀዋል። ከመብራት መቋረጥ ጋር በተያያዘ ፋብሪካዎች፣ የሕክምና መስጫ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እና የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ስራቸውን ለማቆም ተገደዋል። በተጨማሪም በተወሰኑ የከተማ ክፍል የስልክ ...

Read More »

ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰባት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ የፍርድ ብያኔ ተሰጠ

ሰኔ ፲፮( አሥራ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ኢትዮጵያ ከተቀሰቀሰው ሕዝባዊ እንቢተኝነት በኋላ በሰላማዊ መንገድ ገዥውን ሕወሃት ኢህአዴግን ይታገሉ የነበሩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ ያነጣጠረ የጅምላ እስራት ተጠናክሮ መቀጠሉ ይታወሳል። ከማእከላዊና በተለያዩ የማሰቃያ እስር ቤቶች ውስጥ ለዓመታት ሰቆቃ ሲፈሰምባቸው ከነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል በሰባቱ ላይ የፍርድ ብያኔ ተሰጠ። የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ...

Read More »

የፖለቲካ ፓርቲዎች በንግድ ስራ መሰማራት የንግድ እንቅስቃሴውን እያደከመው ነው ተባለ

ሰኔ 15/ 2009 የፓለቲካ ፓርቲዎች በንግድ ሥራ ውስጥ መሰማራታቸው የንግድ እንቅስቃሴውን እያዳከመው መሆኑን ታዋቂው የንግድ ሰው ገለፁ። በህወሓት በግል ንብረትነት የሚታወቀው ሬዲዮ ፋና “የፌደራል ስርዓት ግንባታን፣ ብዝሃነትን የጋራ ተጠቃሚነትን የማስተናገድ አቅም” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት ታዋቂው የንግድ ሰው አቶ እየሱስ ወርቅ ዛፉ የፓርቲ ኩባንያዎች በግለሰብ ሥም ጭምር እየተደራጁ በንግድ እንቅስቃሴው ላይ ተፅዕኖ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።  የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ...

Read More »

የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ ከትግራይ ክለቦች ጋር በተያያዘ የፕሮግራም መመሳቀልና ቀውስ ገጠመው ተባለ

ሰኔ 15 ፥ 2009 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሚካሄዱ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ከትግራይ ክለቦች ጋር በተያያዘ የፕሮግራም መመሳቀልና ቀውስ እንደገጠመው መረጃዎች አመለከቱ። በፌዴሬሽኑ የከፍተኛው ሊግ ኮሚቴው የወልዋሎ እና የሽሬ እንደስላሴ ክለቦች በአማራ ክልል ለመጫወት የማይችሉበት የፀጥታ ችግር መኖሩ በመረጋገጡ አዲስ ፕሮግራም የሚወጣበትና ቦታ መቀየር የተገደዱበት ሁኔት ተፈጥሯል።  ስለዚህም የመቀሌ ክለቦች በሙሉ ጨዋታቸውን በአዲስ አበባ ብቻ እንዲያደርጉ የሚያስችል አዲስ ፕሮግራም ማውጣቱን ...

Read More »

ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሊዘጋ እንደሚችል ተገለጸ

ሰኔ 15 ፥ 2009 በኢትዮጵያ ግዙፉን የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ሊዘጉት እንደሚችሉ ታዋቂው የናይጄሪያ ባለሃብት አሊኮ ዳንጎቴ አስጠነቀቁ። ባለሃብቱ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሲሚንቶ አምራቹ ኩባንያቸው የተወሰነ ሥራቸውን ለወጣቶች እንዲሰጡ ትዛዝ ከሰጡ በኋላ ነው። ናይጄሪያዊው ባለሃብት አሊስ ዳንጎቴ የኦሮሚያ መንግስት ይህንን ትእዛዙን ካላነሳ ፋብሪካውን ዘግተው ሥራውን ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ እንደሚያስወጡ ዝተዋል። የኦሮሚያ ምስራቅ ዞን አስተዳደር የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ...

Read More »