ሰኔ 21 ፥ 2009 በኦሮሚያ በቅርቡ ይፋ ከተደረገው የኢኮኖሚ አብዮት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ምስቅልቅል እየተፈጠረ መሆኑ ተገለጸ። በክልሉ በባለሃብቶች ተይዘው የነበሩ ስራዎች ለወጣቶች እንዲሰጡ ጫና እየተደረገ በመሆኑ በኢንቨስትመንት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። በኦሮምያ የኢኮኖሚ አብዮት በሚል እየተቀነቀነ ያለው ባለፈው ጊዜ በክልሉ የነበረውን ተቃውሞ ለማብረድና ወጣቶችን ስራ ለማስያዝ በሚል እንደሆነ ይነገራል ። የኢኮኖሚ አብዮቱ በርካታ በአክሲዮን የሚመሩ ኢንዱስትሪዎች እንደሚገነቡ እቅድ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሜድሮክ ኩባንያ ለገደንቢ ላይ ሲያካሄድ የነበረው ወርቅ የማውጣት ፈቃድ እንዲታደስለት ፈቃድ ጠየቀ
ሰኔ 21 ፥ 2009 የሼህ መሐመድ አላሙዲ ንብረት የሆነው ሜድሮክ የወርቅ ማውጫ ኩባንያ በኦሮሚያ ለገደንቢ ላይ ለ20 አመታት ሲያካሂድ የነበረው የወርቅ ማውጣት ስራውን ለመቀጠል የሚያስችለው ፈቃድ አንዲታደስለት ጠየቀ። ኩባንያው ስምምነቱ ሊጠናቀቅ አንድ አመት ስለቀረው በለገደንቢ በብቸኝነት ሲያካሄደው የነበረውን የወርቅ ማውጣት ስራ ለማስቀጠል ለማዕድን የነዳጅና የተፈጥሮ ሐብት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቧል። ጥያቄው የቀረበላቸው ሚኒስቴር አቶ ሞቱማ መካሳ ጉዳዩን እያጤኑት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ...
Read More »በእስር የሚገኙ የኦፌኮ መሪዎች የአውራ ፓርቲ አስተሳሰቦች ለቀው አዲስ ስርዓት እንዲፈጠር መግለጫ አወጡ
ሰኔ 21 ፥ 2009 በእስር ቤት የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ/ ኦፌኮ/ መሪዎች የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የልማታዊ መንግስትና የአውራ ፓርቲ አስተሳሰቦች ቦታ ለቀው አዲስ ሥርዓት እንዲፈጠር በመጠየቅ መግለጫ አወጡ። የድርጅቱን ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌኮን መሪዎች አሁን በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በተሐድሶ ስም የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተግባራዊ የማይሆንና ሕዝብን ለመደለል የሚደረግ ሙከራ ነው ብለዋል። እስረኞቹ “በአሮጌ አቁማዳ አዲስ ...
Read More »በአዳማ ዙሪያ ያለካሳ መሬታቸውን የተቀሙ ገበሬዎች ለክልሉ ፕሬዚደንት አቤቱታ አቀረቡ
ሰኔ 21 ፥ 2009 በኦሮሚያ አዳማ ዙሪያ ከ80 በላይ ገበሬዎች መሬታቸው ያለካሣ ክፍያ መቀማታቸውን ተከትሎ ለክልሉ ፕሬዚደንት አቤቱታ ማቅረባቸው ተነገረ። ገበሬዎቹ እንዳሉት የአዳማ ከተማ አስተዳደር መሬታቸውን የወሰደው ያለምንም ካሳ ድንገት በወረራ ነው። ከመሬቱ ጋር ተያይዞ አካባቢውን እንዲለቁ ከ2002 ዓ/ም ወዲህ በመጠየቃቸው ውዝግቡ ያኔ እንደተጀመረ ገበሬዎቹ በአቤቱታቸው አስታውቀዋል። የአዳማ አስተዳደር ለገበሬዎቹ ከ2 መቶ እስከ 5 መቶ ስኩር ሜትር ተለዋጭ ቦታ እንስጣችኋልን ...
Read More »በጋሞ ጎፋ ዞን ባለው ድርቅ ሰዎችና እንስሳት ህይወታቸው እያለፈ ነው
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች፣ አርሶአደሮች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንስሳት ያለቁ ሲሆን፣ ሰዎችም መሞት ጀምረዋል። ድንችና የመሳሰሉት ሰብሎች በዝናብ እጥረት መጥፋታቸውን የሚገለጹት ነዋሪዎች፣ በሴፍትኔት እንዲታቀፉ ለተደረጉ ካድሬዎች እህል ቢከፋፈልም አብዛኛው ህዝብ እርዳታ ባለማግኘቱ ከፍተኛ አደጋ ተደቅኖበታል። በድርቁ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቁት መካከል ኮንሶ፣ ደራሸ፣ ...
Read More »ከዎላይታ ዞን ወደ ሲዳማ ዞን በኃይል ለማካለል የተጀመረውን እንቅስቃሴ የዎላይታ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ዎህዴግ/ ተቃወመ
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዎህዴግ ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓም ባወጣው ባለ 4 ገጽ መግለጫ የዎላይታ ህዝብ ብዛትና የመሬት ጥበትን ተከትሎ የዎላይታ ወጣቶች በትምህርት መቅሰሚያ ዕድሜኣቸው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየሄዱ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮኣቸውን እየገፉ መሆኑን ጠቅሶ፣ በአካባቢው ያለው የመሬት ጥበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ጊዜ፣ አሁን ደግሞ ‹‹ ...
Read More »የዋልድባ ገዳም መነኮሳት በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ተዘገበ
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት ከእስር የተፈታው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣው ዘገባ እንደገለጸው መነኮሳቱ በጎንደር ከተማ በነበረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል ተብለው ይፈለጉ ለነበሩ ግለሰቦች ከለላ ሰጥተዋል በሚል ምክንያት የሽብርተኝነት ክስ ተከፍቶባቸዋል፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት ሰኔ 20/2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት ...
Read More »የትምህርት ሚኒስትሩን የዝርፊያ ሰንሰለት የሚያሳዩ ተጨማሪ መረጃዎች እየመጡ ነው
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አሁን ትምህርት ሚኒስቴርን የሚመሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በሙስና መዘፈቃቸውን በተመለከተ ኢሳት መረጃዎችን ማውጣቱን ተከትሎ፣ የክልሉ ነዋሪዎች በተለይ የአቶ ሽፈራውን የሙስና ሰንሰለት የሚያሳዩ መረጃዎችን እየላኩ ነው። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው የአቶ ሽፈራው የሙስና ሰንሰለት እስከ ወረዳ የተዘረጋ ነው ይላሉ። ...
Read More »ወደ ማላዊ ሲገቡ የነበሩ 26 ኢትዮጵያዊያን መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ
ሰኔ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር ቆራርጠው በማላዊ የድንበር ከተማ ካሮንጋ በኩል በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ተጭነው የነበሩ 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በድንበር ፖሊስ መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪዎችን ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ ከቺቲፓ ወደ ካሮንጋ አውራጃ የሚወስደውን M1 አውራ ጎዳና ይዘው ሲጓዙ ነበር። የድንበር ፖሊሶችን መምጣት በማየት መንገዳቸውን ቀይረው በካሮንጋ አየር ...
Read More »ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ክልል ላይ ያለውን መብት የተመለከተው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ም/ቤት መጽደቁ ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 20 ፥2009) ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን መብት የተመለከተው ረቂቅ ኣዋጅ በሚንስትሮች ም/ቤት መጽደቁ ተሰማ። በቀጣዩ ሳምንት ፓርላማ ቀርቦ እንደሚጸድቅም ይጠበቃል። ከሳምንት በፊት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተወያይቶ ያሳለፈው ይህ ረቂቅ ኣዋጅ አዲስ አበባ የሚባለው የከተማው ስያሜ በነበረበት እንዲቀጥል ፊንፊኔ የሚለውም መጠሪያ በተጨማሪነት እንዲያገለግል ወስኗል። በሚኒስትሮች ም/ቤት ማክሰኞ እለት የጸደቀው ረቂቅ አዋጅ ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር በአዲስ ...
Read More »