ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) በደቡብ ኢትዮጵያ ከፋ ዞን የቴፒ ወህኒ ቤትን በመስበር እስረኞችን ያስመለጡትን ታጣቂዎች መንግስት በሽምግልና ካስገባቸው በኋላ ወደ ወህኒ እንደወረዳቸው የአካባቢው ምንጮች ገለጹ። በከተማው ነዋሪ ላይ የሚፈጸመው ግፍና በደል መጠናከሩንም እነዚሁ ምንጮች አስታውቀዋል። ከሁለት አመት በፊት ሃሙስ ግንቦት 27/2007 ሌሊት በቴፒ ከተማ ወህኒ ቤት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከመቶ በላይ እስረኞችን በማስፈታትና መሳሪያ በመንጠቅ ተመልሰው ጫካ የገቡት ታጣቂዎች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የብሉምበርግ የዜና ወኪልን ዘገባ በኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊው በኩል አጣጣለ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) የብሉምበርግ የዜና ወኪል በሲምንቶ ምርት ላይ በኦሮሚያ ተሰማርቶ የነበረው ዳንጎቴ ሲምንቶ ፋብሪካ ከአስተዳደሩ እየደረሰበት ባለው ጫና ምክንያት ፋብሪካውን ዘግቶ ሊወጣ እንደሚችል ዘግቦ ነበር። የጽ/ቤት ሃላፊው አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት አስተያየት “የብሉምበርግ የዜና ወኪል የሰራው ዘገባ መሰረታዊ የጋዜጠኝነት የስነ-ምግባር ያልተከተለ የክልሉን መንግስት መልካም ስም ለማጉደፍ ሆን ተብሎ የተሰራ ተራ ፕሮፖጋንዳ ነው” በማለት አጣጥለውታል። አቶ አዲሱ አያይዘው ...
Read More »የአጋዚ ክ/ጦር በሰሜን ጎንደር መሳሪያ ለማስፈታት ያደረገው ሙከራ ግጭት አስከተለ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) የአጋዚ ክፍለጦር አባላት በሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ መሳሪያ ለማስፈታት ያደረጉት ሙከራ ወታደራዊ ግጭት አስከተለ። የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ሃሙስ ሰኔ 22/2009 በተካሄደ ግጭት 7 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ ሶስት መቁሰላቸው ተመልክቷል። በነጻነት ሃይሎች በኩል ስለደረሰው ጉዳት የተገለጸ ነገር የለም። ሐሙስ ሊነጋጋ ሲል በሰሜን ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ የተንቀሳቀሱት የአጋዚ ክፍለጦር አባላት ስለዘመቻው በቂ መረጃ በነበራቸው የነጻነት ...
Read More »የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የመቀሌ አቻው ለጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባለመገኘቱ ፎርፌ እንዲሰጠው ጥያቄ አቀረበ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለተመሳሳይ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም የመቀሌ አቻው ውድድር ሜዳ ላይ ባለመገኘቱ ፎርፌ እንዲሰጠው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ጠየቀ። ክለቡ ከዚህ ቀደም በመቀሌ ከተማ ከዚሁ ቡድን ጋር በነበረው ጨዋታ በተፈጠረ ግጭት ውድድሩ ከተቋረጠ በኋላ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥፋተኛ ተብሎ ተጫዋቾቹና ቡድን መሪዎቹ በገንዘብ መቀጣታቸው ይታወቃል ። የባህር ዳር ከተማ ...
Read More »የአሜሪካው ጠ/ፍርድቤት የ6 እስልምና ዕምነት ተከታይ ሃገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክለውን ህግ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ ሰጠ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) የአሜሪካው ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰኞ በወሰነው መሰረት በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታዩች ካሉባቸው ስድስት አገሮች የሚመጡ ጎብኝዎች እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከሰኔ 29/2017 ምሽጥ 8 ሰአት ጀምሮ ወደ አገሪቱ መግባት እንደማይችሉ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አስታወቀ። ጎብኚዎቹ አሜሪካ የሚኖሩ የቅርብ ዘመድ ከሌላቸው ወይንም በአሜሪካ ከሚገኝ ድርጅት እና የትምህርት ተቋም ጋር የስራ ስምምነት ከሌላቸው ወደ ሃገሪቱ መግባት አይችሉም። የውጪ ጉዳይ ...
Read More »ለስራ ወደሩማንያ ከሄዱት የንግድ ም/ቤት አባላት ሰባቱ አለመመለሳቸው ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 22 ፥ 2009) ለስራ ከሃገር ከወጡ የንግድ ም/ቤት ልኡካን አባላት ሰባቱ ምስራቅ አውሮፓ ሩማንያ ውስጥ መቅረታቸው ተዘገበ። በግንቦት ወር ከ27 የንግድ ም/ቤት ልኡካን ጋር ወደ ቡካሬስት ሩማንያ የተጓዙት ሰባቱ ግለሰቦች ስለቀሩበት ምክንያት የተገለጸ ነገር ባይኖርም ከመካከላቸው አራቱ ወደ ጎረቤት ሃገር ሃንጋሪ ሲሻገሩ ድንበር አካባቢ መያዛቸው ተነግሯል። በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዝዳንት በአቶ ኤልያስ ገነቱ የተሰራውና ባለፈው ...
Read More »ህወሃት በዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚብሄር በኩል በአማራ ክልል ፖሊስ አዛዦች ላይ ምርመራ ጀመረ
ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በቅርቡ በክልሉ ከታየው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ በሁዋላ የታየው የፖሊሶች አቋም፣ ለህወሃት ህልውና አደገኛ ነው በሚል እምነት፣ ራሱ በሚመራው ኮማንድ ፖስት አማካኝነት እየገመገመ ስራቸውን እንዲለቁ፣ ወንጀል ስርተዋል እያለ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ካደረገ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ ዋና ዋና በሚባሉት የፖሊስ አዛዦች ላይ በህወሃቱ ...
Read More »በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች በተናጠል እየተሰቃዩ ነው። በእነ ወ/ት ንግስት ይርጋ ላይም የሃሰት ምስክር ሊቀርብ ነው
ሰኔ ፳፪ ( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን ምንጮች አስታወቁ። እስረኞች የደንብ ልብስ እንዲለብሱ የሚገደዱት ወደ ቤተሰብ ሲወጡና ተነስተው ሲዘዋወሩ ብቻ ቢሆንም፣አሁን ግን የተኙ እስረኞች ሳይቀር የደንብ ልብስ አለበሳችሁም እየተባሉ ድብደባ፣ ማዋከብ፣ እና የአመክሮ እስራት ጊዜ እንዲቀሙ ተደርገዋል። ማንገላታቱ እና አካላዊ ጥቃቶች ከሚፈጸምባቸው መካከል የፖለቲካ ...
Read More »ህወሃት/ኢህአዴግ በሲዳማና በወላይታ ብሄረሰቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ነው ተባለ
ሰኔ 21 ፥ 2009 በወላይታና በሲዳማ ብሔረሰቦች መካከል ሆን ተብሎ ግጭት ለመፍጠር በአገዛዙ በኩል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ። ግጭቱን በሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል እንዲፈጠር ምክንያት እየተደረገ ያለው በወላይታና በሲዳማ መካከል በሚገኝው ሁምቦ በተባለ የድንበር ቦታ ይገባኛል ጥያቄ ነው። ከዚህ ቀደም በድንበሩ ምክንያት በተነሳ ግጭት 13 የወላይታ ተወላጆች ሲገደሉ ከሲዳሞ ሰዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ የሰው ሕይወት ጠፍቶ ነበር። በሁለቱ ብሔረሰቦች መካከል ያለው ውዝግብ ...
Read More »ትጥቅ ለማስፈታት በሚል በተለያዩ የጎንደር አካባቢዎች የአጋዚ ጦር መስፈሩ ተነገረ
ሰኔ 21 ፥ 2009 የጎንደርን ህዝብ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል በወረታ ፣ አዘዞ፣ ዳባትና እብናት የአጋዚ ጦር መስፈሩ ተነገረ ። በጎንደር የአገዛዙን ግፍና በደል በመቃወም ህብረተሰቡ ከፍተኛ አመጽና የትጥቅ ትግል እያካሄደ መሆኑ ስርአቱን በእጅጉ አሳስቦታል ። በተለይም በሰሜን ጎንደር የሚገኙ የነጻነት ሃይሎች በስርአቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸው በአካባቢው ከፍተኛ የአጋዚ ጦር እየተሰማራ መሆኑ ተነግሯል ። በዚሁም ምክንያት በሰሜን ጎንደር ህዝቡን ...
Read More »