.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኦዴግ ህወሃት/ኢህአዴግ ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ የሚኖረውን ጥቅም በተመለከተ ያወጣው ረቂቅ ህግ ተቀባይነት የለውም አለ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2009) የኦሮሞ ህዝብ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ኪሳራ የተለየ ጥቅም ባልፈለገበት ሁኔታ በሃገሪቱ ያለው አገዛዝ አዲስ አበባ በተመከተ ያወጣቅ ረቂቅ ህግ ተቀባይነት እንደሌለው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ገለጸ። ድርጅቱ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ይኖረዋል የተባለው ልዩ ጥቅም አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው አዲስ አበባ ከተማ በሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ኪሳራ የኦሮሞ ህዝብ ለመጠቀም እንደፈለገ ተደርጎ የተቃኘውና በውዥንብር የተሞላው ረቂቅ ህግ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ህወሃት/ኢህአዴግ ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞች ቤቶችን አፈረሰ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2009) በሰሜን ጎንደር ቋራ በረሃ ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞች ላይ ያነጣጠረ የቤት ማፍረስ ዘመቻ በአገዛዙ ሃይሎች መጀመሩን የኢሳት ምንጮች ገለጹ ። በቋራ ጉላን ከተማ ብቻ 200 ቤቶች ፈርሰዋል ። ለነጻነት የሚታገሉ ሃይሎች መሬታቸው እንዳይታረስ ሲያደርግ የቆየው የአገዛዙ ወታደራዊ እዝ እርሻቸው ለስርአቱ ደጋፊዎች ሲሰጥ መቆየቱም ተነግሯል ። የቋራ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ወይም ወታደራዊ እዝ በኮለኔል ገብረመስቀል በየነ የሚመራ ...

Read More »

አዲሱ የቀን ገቢ ግምትና የግብር ክፍያ ነጋዴው ለተቃውሞ እየተቀሰቀሰ ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2009) ከቀናት በኋላ ለሁሉም የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ይፋ የሚሆነው የቀን ገቢ ግምትና የግብር ክፍያ የደረጃ ምደባ በነጋዴው ውስጥ ቅሬታ እንደፈጠረና ውስጥ ለውስጥ ተቃውሞ እየቀሰቀሰ መሆኑን በከተማዋ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በተጨማሪም የችርቻሮ ሱቆችን እስከ ማዘጋት እንደሚደርስ ነጋዴዎቹ አስጠንቅቀዋል ። መርካቶ ፣ፒያሳ ፣ቂርቆስ ገበያን ጨምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች በመዟዟር መረጃ ያሰባሰቡት የአዲስ አበባ የኢሳት ምንጮች ...

Read More »

ኤርትራ በአለም አቀፍ መንግስታት ድጋፍ ማግኘቷ ለኢትዮጵያ ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2009) የኤርትራ መንግስት ወደ አለም አቀፍ መድረክ እየተመለሰ መምጣቱና የገንዘብ ድጋፍ እያገኘ መሄዱ ለኢትዮጵያ መንግስት ስጋት መደቀኑን የአሜሪካውያኑ የትንተና መጽሄት ፎርየን ፖሊሲ ዘገበ። The Rehabilitation of Africa’s most isolated dictators በሚል ርእስ መጽሄቱ ባሰፈረው ሰፊ ዘገባ ኤርትራ ከመከላከኛው ምስራቅ ሃገሮች ባሻገር ከምእራብያውያን ጋርም ግኑኝነቷን  ተንትኗል። በየመን የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ ከሳውዲ አረቢያና ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ጋር የፈጠረችውን ...

Read More »

ሳውዲ አረቢያ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚወጡበትን ጊዜ ለአንድ ወር አራዘመች

ኢሳት (ሰኔ 23 ፥ 2009) የኢትዮጵያውን ስደተኞችን በተመለከተ ሳውዲ አረቢያ አስቀምጣ የነበረውን ቀነ-ገደብ በአንድ ወር መራዘሙ ተነገረ። የሳውዲ አረቢያ መንግስት የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሌላቸውን የሌላ ሃገራት ዜጎች በሚመለከት በ90 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የምህረት አዋጅ መደንገጉ ይታወሳል።  ይህም ቀነ ገደብ ሰኔ 20/2009 አ ም በመጠናቀቁ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ችግር ላይ ይወድቃሉ የሚል ስጋት ነበር። በሳውዲ አረቢያ ይኖራሉ ከተባሉ ወደ 4 ...

Read More »

በአዲስ አበባ ነጋዴዎች በግምት የሚጣልባቸውን ግብር ተቃወሙ

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳ 11 የሚገኙ ነጋዴዎች ፣ በዘፈቀደ የሚተመነውን የቀን ገቢ ግምት ተንተርሶ የተጣለባቸውን የግብር ከፍያ በመቃወም አቤቱታ ሲያሰሙ፣ በፌደራል ፖሊሶች እንዲበተኑ ተደርጓል። ነጋዴዎች የንግድ ድርጅቶቻቸውን እየዘጉ ፈቃዳቸውን እንደሚመልስ ሲያስጠነቅቁ ውለዋል። ህዝቡ ወደ ቀበሌ በመሄድ ፈቃዳችንን ተቀበሉን እያለ ቢሆንም፣ ፈቃድም ለመመለስ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያስከፍል ነጋዴዎች ይናገራሉ ። በመርካቶ አካባቢም በርካታ ...

Read More »

የደቡብ አሪ ወረዳ መምህራን የተቃውሞ ፊርማ አሰባስበው አስገቡ

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ የሚገኙ መምህራን በመጋቢት ወር ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ያለፈቃዳቸው ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ እንዳይቆረጥባቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ደሞዛቸው ሳይቆረጥባቸው የቆየ ቢሆንም፣ አሁን ግን የአመቱን የስራ ማጠናቀቂያ ተከትሎ መምህራን ስለሚበታተኑ ተቃውሞ አያነሱም በሚል ከሰኔ ወር ደሞዛቸው ላይ 30 በመቶ እንደሚቆረጥባቸው ወረዳው መናገሩን ተከትሎ መምህራን ...

Read More »

የቂሊንጦ እስረኞች የግዳጅ የጉልበት ስራ እየሰሩ መሆኑን ተናገሩ

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቂሊንጦ እስር ቤት የግዳጅ የጉልበት ስራ እያሰራቸው መሆኑን በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተከሰው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙት እነ ጌታሁን በየነ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ እስረኞቹ ፣ 200 ኪሎ ግራም ቆሻሻና የ125 እስረኞች የሚቀርብን ወጥ ሁለት ሰዎች ብቻ እንዲሸከሙ እንደሚገደዱና ይህም ...

Read More »

የማላዊ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ካለምንም ሕጋዊ ቪዛ ወደ አገሬ ገብተዋል ባላቸው 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የገንዘብ ቅጣት ፈረደ

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለምንም ሕጋዊ ቪዛ በሕገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብታችኋል በተባሉ 27 ስደተኞች ላይ እያንዳንዳቸው 20 ሽህ የማላዊ ክዋቻ እንዲከፍሉ ሲል የአገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በየነ። ከተፈረደባቸው ስደተኞች ውስጥ ከአንዱ በስተቀር የተቀሩት ሃያስድስቱም በሙሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ናቸው። ስደተኞች ማክሰኞ እለት በሕገወጥ መንገድ በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ተጭነው ሲጓዋዙ ይጠቀሙበት ከነበረው ተሽከርካሪ ...

Read More »

በሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ ፋንታ በጸና ታመዋል

ሰኔ ፳፫ ( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሙስና ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ፋንታ በጸና መታመማቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ጥቅምት ወር፣ 2006 ዓም በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ መላኩ፣ በተከሰሱበት ወንጀል እንዲከላከሉ ባለፈው የካቲት ወር ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠቱ ይታወቃል። አቶ መላኩ ምንም አይነት ...

Read More »