የአፍሪካ ህብረት 29ኛው የመሪዎች ጉባኤ የአህጉራዊውን ተቋም የፋይናንስ ምንጭ በራሱ ለመሸፈን በሚያስችሉና አሰራሩን ለማጎልበት በሚያበቁ ጉዳዮች ለመምከር በአዲስ አበባ ሰኞ ተጀመረ ። ህብረቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባኤ በአህጉሪቱ የጸጥታና የሰላም ጉዳዮች ላይም እንደሚመክር ዘገባዎች አመልክተዋል ። የአፍሪካ ህብረት እስካሁን በነበረው ሁኔታ ወጪዎቹ የሚደጎሙት ከአውሮፓ ህብረትና ከተለያዩ እርዳታ ሰጪዎች በሚለገሰው ገንዘብ ነው ። ከዚህ በተጨማሪም የህብረቱ ሃገራት የሚያዋጡት የአባልነት መዋጮ ገንዘብም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ዝግጅት በሲያትል ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ
34ኛ አመት ያስቆጠረው የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን ዠግጅት እሁድ July 2, 20172 በዋሽንግተን ሲያትል ሬንተን ስቴድየም ብዙ ሺህ ተመልካቶች በተገኙበት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መጀመሩን በስፍራው የተገኘው የኢሳት ጋዜጠኛ ተወልደ በየነ ዘግቧል። በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ለ34ኛ ጊዜ በአሜሪካ ሲያትል ያዘጋጀው አመታዊ ስነ-ስርአት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ታዳሚ ተገኝቶበታል። የኢትዮጵያ ባህልና ወግ የተንጸባረቀበት ስነ-ስርአቱ የተከበረው በሬንተን ስቴድየም ከመሆኑ ...
Read More »የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የሚያቀርባቸው ሪፖርቶች በሃሰት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው ተገለጸ
የኢህአዴግ ፓርላማ የመንግስት ልማት ድርጅት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቀራረቡ ያልሰራውን እንደሰራ አድርጎ ሰለሆነ የተሳሳተ መረጃ እንደመስጠት ተደርጎ ሊቆጠር እንደሚገባ ተናግረዋል ። የፓርላማው ተወካዮች እንደገለጹት ሜቴክ ከአቅሙ በላይ የሆኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመረከብ ለተራዘሙ አመታት በመንጓተቱ ፤ የሃገሪቱ የፋይናንስ ስርአትን ባልተከተለ ሁኔታ ገንዘብ ማባከኑ፤ የፕሮጀክት ባለቤቶች ከሆኑ መንግስታዊ ተቋማት ጋር ጤናማ ግንኙነት መፍጠር ...
Read More »የኢትዮጵያ የሙስሊም ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላትን ጨምሮ 12 ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ጅዳ መታሰራቸው ተነገረ
ከታሰሩት መካከል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን እና ኡስታዝ ከማል ሸምሱ ይገኙበታል። 12ቱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በምን ምክንያት እንደታሰሩ ባይታወቅም የሳውዲ አረቢያ የደህንነትና የፖሊስ አባላት በትብብር ተቀናጅተው በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል። በሳውዲ የታሰሩትን ኢትዮጵያውያን በዋስ ለማስፈታት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ለዋስትናም አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር መጠየቁ ተነግሯል ። የጀርመን ድምጽ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ እዳ ከ575 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ
በውጭ ምንዛሪ ቀውስ የሚታወሰው የህዉሃት/ኤህአዴግ አገዛዝ በ2009 አ.ም አመታዊ የውጭ ወለድ ክፍያው ከ3 ቢሊዮን ብር ወደ 10 ቢሊዮን ብር እንዲሁም አመታዊ የመንግስት የውጭ እዳ ክፍያ ከ14 ቢሊዮን ብር ወደ 25 ቢሊዮን ብር አድጓል። በዚህ ምክንያት ችግሩ የህዉሃት መራሹ መንግስት አጣብቂኝ ውስጥ እየከተተው እንደሆነ ተገልጿል። ከፊሉን የውጭ እዳ ለማቃለል ከወጭ ንግድ ከሚገኘው የውጭ ምንዛሪ እሸፍናለሁ በማለት ቢገልጽም በየአመቱ ከውጭ ንግድ የሚገኘው ...
Read More »ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የተጣለው ግብር በመላ አገሪቱ ችግር እየፈጠረ ነው።
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እዳ አለባቸው የሚባሉ ነጋዴዎች በባንክ ያስመቀጡትን ገንዘባቸውን እንዳያወጡ እገዳ እየተጣለባቸው መሆኑን ነጋዴዎች ገልጸዋል። ከፍተኛ ገንዘብ ለመሰብሰብ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለው ገዢው ፓርቲ፣ ነጋዴዎች ከገቢያቸው ጋር ያልተመጣጣነ ግብር እንዲከፍሉ በማድረጉ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ነጋዴዎች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው። “ የሌለንን ገቢ እንዳለን አድርጎ የሚጣለው ግብር” በኑሮአችን ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው የሚሉት ...
Read More »በሰፈራ ወደ ተከዜ የተወሰዱ የአማራ ክልል ነዋሪዎች በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከበየዳና ደባርቅ አካባቢ ተነስተው ዘመነ ወርቅ በተባለው የተከዜ ሰው ሰራሽ ሃይቅ አካባቢ እንዲሰፍሩ የተደረጉት ነዋሪዎች የክልሉ መንግስት ምንም ዓይነት መሰረተ ልማት ሳያሟላ እንድንሰፍር በማድረጉ ከፍተኛ ችግር ላይ ጥሎናል ብለዋል። በ2008 ዓም. ከ1400 አባወራ በላይ ወደ አካባቢው እንዲሰፍር ቢደረገም በአጎራባች ክልሎች እንደሚካሄደው ሰፈራ የመሰረተ ልማት ተቋማት ሳይገነቡ በደፈናው ወደ ...
Read More »ቂሊንጦ እስር ቤትን አቃጥለዋል በሚል ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል የተወሰኑ እስረኞች ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ነው
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርና በሌሎችም ወንጀሎች ተከሰው በእስር ቤት እያሉ እንደገና ቂሊንጦን አቃጥለዋል በሚል ክስ ከቀረበባቸው ወጣቶች መካከል፣ የተወሰኑት ዝዋይ እስር ቤት ተወስደው ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። እስረኞች ፍርድ ቤት ላይ ተቃውሞ በማሰማት፣ እንዲሁም የእስር ቤቱን አስተዳደር ፊት ለፊት በመጋፈጥ ይታወቁ ነበር። በተለይ አዲስ ክስ በሀሰት ከተመሰረተባቸው በኋላና ክሱን ...
Read More »በአዋሳ ክብር ለእናቶች በሚል በተዘጋጀው በአል ላይ ተሸላሚ እናቶች ሳይገኙ ቀሩ
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው ክብር ለናቶች የልማት ተራድኦ ድርጅት በሀዋሳ መስቀል አደባባይ ፕሮግራም አዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም፣ እውቅናና ሽልማት ይሰጣቸዋል የተባሉ እናቶች ሳይገኙ ፣ በእናቶች ስም የተሰበሰበው ገንዘብ ተበልቷል። በፕሮግራሙ ላይ 50 በሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ ልጆቻቸውን ለማሳደግ ዋጋ የከፈሉ እና ዝቅተኛ ኑሮ ላይ የሚገኙ እናቶችን ለመሸለም እና እውቅና ለመስጠት ፕሮግራም ተይዞ ...
Read More »45 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ታንዛኒያ ውስጥ ተያዙ
ሰኔ ፳፮ ( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህገወጥ መንገድ ወደ ታንዛኒያ የገቡ 45 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በበቆሎ ማሳ ውስጥ ተደብቀው መያዛቸውን የታንዛኒያ ባለስልጣናት አስታወቁ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ካለምንም ሕጋዊ ሰነድ ወደ ታንዛኒያ ሲገቡ መያዛቸውን የታንጋ ክፍለሃገር የስደተኞች ጉዳይ ዋና ሃላፊ የሆኑት ክሪስፒን ኒጎያኒ ገልጸዋል። ባለስልጣኑኑ እንዳሉት ስደተኞቹ በሰሜናዊ ምስራቅ ታንዛኒያ በሚኪንጋ አውራጃ በኬኒያ እና ታንዛኒያ ድንበር አቅራቢያ ...
Read More »