.የኢሳት አማርኛ ዜና

የእንግሊዝ ፖሊስ በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ ክስ መሰረተ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ታደሰ ክስ የተሰመረተባቸው በጥር ወር ኤርትራ ቆይተው ወደ እንግሊዝ ሲገቡ፣ አየር ማረፊያ ላይ በተደረገው ፍተሻ አንዳንድ ጽሁፎችን ከዌብ ሳይት ላይ ወስደው ኮምፒተሮቻቸው ላይ አውርደውና ቦርሳቸው ውስጥ ይዘው በመገኘታቸው ነው። ጽሁፎቹ በእንግሊዝ ፖሊሶች በጥርጣሬ መታየታቸውን ተከትሎ፣ ክስ እንደተመሰረተባቸው ታውቋል። ዶ/ር ታደሰ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የዲሞክራሲና የፍትህ ትግል ውስጥ በአርበኞች ...

Read More »

ህወሃት መራሹ መንግስት ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የቴሌቪዥና የራዲዮ ስርጭት ሙሉ በሙሉ ለማፈን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለማክሽፈፍ ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ  ጥሪ ቀረበ።  

ኢሳት ሰኔ 27/2009 ህወሃት መራሹ መንግስት ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የቴሌቪዥና የራዲዮ ስርጭት ሙሉ በሙሉ ለማፈን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለማክሽፈፍ ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ  ጥሪ ቀረበ።  የኢሳት ዋና ዳይሬክተር አበበ ገላው ጉዳዩን በማስመልከት ለኢሳት በሰጠው መግለጫ አንዳስገነዘበው ህወሃት መራሹ መንግስት በከባድ ፈተና ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ከመቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድቦ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ገልጿል።  የህውሃት/ ...

Read More »

241ኛው የአሜሪካ የነጻነት ቀን በዛሬው እለት ተከብሮ ዋለ

ኢሳት ሰኔ 27/2009 አስራ ሶስት የአሜሪካ ግዛቶች ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ ወጥተው ዩናይት ስቴት ኦፍ አሜሪካን የመሰረቱበት 241ኛው የአሜሪካ የነጻነት ቀን ማክሰኞ እለት በመላው አገሪቱ ተከብሮ ውሏል። እ.ኤ.አ በ July 4, 1776 የ13 ግዛቶች ተወካዮች በፔንሲልቬንያ ተሰባስበው ነበር። ከእንግሊዝ አገዛዝ ነጻ መውጣታቸውንና እራሳቸውን የቻሉ ሉአላዊ ግዛቶች መሆናቸውንና በዚሁም ቀን ዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ መመስረቷን አወጁ። ዲክላሬሽን ኦፍ ኢንዲፔንደንስ የተሰኘውንም የአሜሪካን ነጻነት ...

Read More »

ለቤት ግንባታ በአለም አቀፍ ጨረታ የተመዘገቡ የውጭ አገር ኩባንያዎች ወደ ስራ አለመግባታቸው ተገለጸ

ኢሳት ሰኔ 27/2009 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ለቤት ግንባታ ባወጣው አለም አቀፍ ጨረታ 28 የሚጠጉ ደረጃ አንድ የውጭ ኮንትራክተሮች ተወዳድረው የተመረጡ ቢሆንም አንዳቸውም ወደ ስራ መግባት እንዳልቻሉ የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ከዛሬ ሁለት አመት በፊት የኮንስትራክሽን ሚኒስትሩና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ በሰጡት የጋራ መግለጫ የውጭ ኮንትራክተሮችን በመኖሪያ ግንባታ ዘርፍ ለማሳተፍ ቅድመ-ዝግጅቱ የተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸው በጥቂት ቀናት ወደ ...

Read More »

የህዉሃት/ ኢህ አዴግ መንግስት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ለሱማሊያ መንግስት ማስረከቡ ተገለጸ

ኢሳት ሰኔ 27/2009 የህዉሃት/ ኢህ አዴግ መንግስት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ለሱማሊያ መንግስት ማስረከቡ ተገለጸ። 29ኛውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ እየተካፈሉ ያሉት የሱማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊ በቲውተር ገጻቸው የመረጃውን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል።  የሱማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ሰኞ እለት እንደገለጹት ከሆነ ሃገራቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በገባችው ስምምነት መሰረት 120 የሱማሊያ እስረኞችን ተረክባለች። እስከ ኣስር አመት እና ከዚያ በላይ መታሰራቸው የተገለጸው እስረኞች በምን ...

Read More »

የኪነጥበብ ሙያተኞች በሽብርተኝነት ተከሰሱ

ኢሳት ሰኔ 27/2009 ሰኔ 23 ቀን 2009 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት 5 አርቲስቶችን እና ተባባሪዎች ያላቸውን የሽብርና የወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። ሴና ሰለሞን፣ ኢፋ ገመቹ፣ ሃይሉ ነጮ፣ አሊያድ በቀለ እና ኤልያስ ክፍሉ የተባሉ አርቲስቶችና በግል ስራ እንደሚተዳደሩ የተገለጹ ቀነኒ ታምሩ እና ሞይቡሊ ምስጋኑ የቀረበባቸው ክስ ሁከትና አመጽ የሚያነሳሱ ዜናዎችን በኦሮምኛና በአማርኛ ቋንቋ አዘጋጅተው በድምጽ በመቅረጽ ማሰራጨታቸው፤ ...

Read More »

“ብአዴንንና ህወሃትን፣ ህወሃትንና ኦህዴድን ለማጋጨት ፀረ-ሰላም ሃይሎች የጠነሰሱትን ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ አግዘናቸዋል” ሲሉ አንድ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ተናገሩ

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ ብአዴን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካና ርእዮተአለም ብልሽት አጋጥሞታል። በ40 እና 50 አመታት ጊዜ ውስጥ የበለጸገ አገር የሚፈጥር መስመር ሆኖ እያለ፣ ይህንን መስመር በብቃት ባለማወቃችን ምክንያት ይህን መስመር እየተከላከልነው አይደለም” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ በእኛ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ብልሽት ምክንያት ከመስመራችን በተጻጻሪ ለቆሙ ሃይሎች አቅም ሆነን እንታያለን ሲሉ በተሃድሶ ስብሰባ ላይ ምሬታቸውን ...

Read More »

ዲፕሎማቶች የኢህአዴግ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ይሳካል ብለው እንደማያምኑ ፋይናንሻል ታይምስ ዘገበ

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው የቢዝነስ ጋዜጣ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ ይዞት በወጣው ጽሁፍ እንዳተተው ምንም እንኳ ቻይና መራሹ የኢኮኖሚ ፖሊሲ የስራ እድል በመፍጠር በአገሪቱ ውስጥ የሚታየውን የስራ አጥ ቁጥር ትክክለኛ አካሄድ መስሎ ቢታይም፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆኑ ዲፕሎማቶች አጠቃላይ የኢኮኖሚ እቅዱ ይሳካል የሚል እምነት የላቸውም። ዲፕሎማቶቹ ከሚጠቅሷቸው ምክንያቶች መካከል የፋይናንስ አገልግሎቱ ፣ ...

Read More »

በባህርዳር አየር ማረፊያ ላይ የተያዘውን ተቀጣጣይ ፈንጅ ተከትሎ በጥርጣሬ ሰዎች እየተያዙ ነው

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተያዙት ሰዎች መካከል አንደኛው ግለሰብ፣ እቃውን እንዳደርስ አንድ ሰው ላከኝ እንጅ ፈንጅ ይሁን አይሁን አላውቅም ብሎ የተናገረ ሲሆን፣ ከጎንደር መላኩንም ገልጿል። ፈንጁን ሰጥቶታል የተባለውን ሰው ለመያዝ፣ ከግለሰቡ ጋር መርመሪዎች ወደ ጎንደር ሊወስዱት ማሰባቸውን የኢሳት የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። አንድ የአየር መንገድ ሰራተኛም በቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮች ገልጸዋል።

Read More »

በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ሲሰቃዩ የነበሩ 120 ሶማሊያዊያን እስረኞች ተለቀቁ

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሶማሊያ ጠቅላይ ሚንስትር ሃሰን ዓሊ ከይሬ ለ29ኛው አፍሪካ ሕብረት ስብሰባ በመጡበት በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩ 120 ሶማሊያዊያን እስረኞችን ሰኞ እለት አስለቁ። ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ”ሁለታችንም መንግስታት በደረስንበት የጋራ ስምምነት አማካኝነት 120 ሶማሊያዊያን ዜጎቻችንን ከእስር ተፈተዋል።” በኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ አሁንም ድረስ ስላሉት ሶማሊያዊያን ...

Read More »