.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚታየውን የትጥቅ ትግል ተንተርሶ እርሻ አለመታሩሱን ታጋዮች ተናገሩ

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርበኞች ግንቦት7 ስር ታቅፈው እንደሚንቀሳቀሱ የገለጹት ታጋዮቹ ፣ ህወሃት ለአንድ አርበኛ ታጋይ 400 ያክል ወታደሮችን አሰልፎ ታጋዮቹን ለመፈለግ በሚያደርገው ዘመቻ አርሶአደሩ እየተያዘ እስር ቤት በመወርወሩ እርሻ አልታረሰም። “ አንድ ሰኔ የነቀለውን 10 ሰኔ አይተካውም “ የሚሉት ታጋዩ፣ “ከማረሻ ውጭ ምን አለን? ማረሻ ከተሰቀለ፣ ቀንበር ከተሰቀለ፣ ጅራፍ ከተሰቀለ ከዚህ ...

Read More »

የኩራዝ አንድ የስኳር ፕሮጀክት ምርት ጀመረ ተብሎ መዘገቡን ሰራተኞች አስተባባሉ ።ማኔጂመንቱና ሜቴክ እየተወዛገቡ ነው።

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ህወኃት በአማራጭነት ያቋቋመው የቴሌቪዥን ጣቢያ ፣ ኢኤንኤን /ENN/ በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ “ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና በአካባቢው ነዋሪዎች ‘ፋብሪካው ሥራ የሚጀምረው በምጽዓት/በፍርድ ቀን ነው፣ ወይም የፋብሪካውን ሥራ መጀመር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው (ሜቴክም አያውቀውም)’ ሲባል የነበረው የኦሞ-ኩራዝ 1 የስኳር ፋብሪካ ምርት ጀመሮ ፤ በቀን 650 ቶን ስኳር እንደሚያመርት ፣ ...

Read More »

በአዲስ አበባ በደረሰ የጎርፍ አደጋ አምስት ሰዎች ሞቱ። የአባትና ልጅ አስከሬን እስካሁን አልተገኘም።

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት ሁለት ቀናት በተከታታይ የጣለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በአዲስ አበባ አምስት የከተማዋ ነዋሪዎች መሞታቸውን የአደጋ ሰራተኞች አስታወቁ። የአዲስ አበባ እሳት አደጋ መከላከያ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ እንዳሉት ”በመዲናዋ ደቡባዊ አዋሳኝ ላይ የሚገኝውን ወንዝ ለመሻገር በሚሞክሩበት ወቅት አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል።” በተጨማሪም በቦሌ ጃክሮስ ...

Read More »

በበቆጂ ከተማ የውሃ እጥረት ነዋሪዎችን አማረረ

ሰኔ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርሲ ዞን የምትገኘው የበቆጂ ከተማ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ ሙሉ ለሙሉ በማጣታቸው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን አስታውቀዋል። በከተማዋ የነበረው ጥንታዊ የውሃ መስመር አገልግሎት መስጠት ካቆመ ረዥም ጊዜያት ሆኖታል። የከተማዋ መስተዳድርም ሆነ የውሃ ልማት ድርጅቱ የነዋሪዎችን የውሃ ችግር ለመፍታት ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታይም። አንድ የአካቢው ነዋሪ ”እኛ የምንኖረው ኑሮ ኑሮ ...

Read More »

የአልሸባብ ታጣቂዎች በኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት አደረሱ

 ሰኔ 28/2009 የአልሸባብ ታጣቂዎች ረቡእ ጠዋት በኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሶስት ፖሊሶች ሲገደሉ ስድስት ቆስለዋል ። ላሙ በተባለች ሃገሪቱን ከሶማሊያ ጋር በሚያዋስን መንደር በሚገኝ የኬንያ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የደረሰውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ ብዛት ያላቸው የአካባቢው ሰዎች የት እንደገቡ እንደማይታወቅ የኬንያው ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል ። ሰባት የሚሆኑ የፖሊስ አባላትም የደረሱበት አልታወቀም ። ውጊያው ለ10 ሰአታት መካሄዱን ያመለከተው የቢቢሲ ዘገባ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬድዮ የተመሰረተበት 7ኛ ግምት በቴነሲ ግዛት ናሽቪል ከተማ ተከበረ

 ሰኔ 28/2009 የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬድዮ የተመሰረተበት 7ኛ ግምት በቴነሲ ግዛት ናሽቪል ከተማ ተከበረ ። በከተማዋ የሚገኙ የኢሳት ደጋፌዎች በተገኙበትና በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄደው መድረክ ኢሳትንና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ውይይትም ተካሂዷል ። የናሽቪል  የኢሳት ኮሚቴ ባዘጋጀውና ቅዳሜ ጁላይ 2/20/17 በተካሄደው ዝግጅት ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንዲሁም ኮሜዲያን ክበበው ገዳ የተገኙ ሲሆን ከአጎራባቿ ከተማ ሜንፈስ የመጡ የኢሳት ደጋፊዎችና በዝግጅቱ ...

Read More »

በወላይታ ሲዳማ ዞን የተነሳው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ወደ ግጭት እንዳያመራ መንግስት እጁን ከጉዳዩ እንዲሰብስብ ጥሪ ቀረበ

ሰኔ 28/2009 በወላይታ ሲዳማ ዞን የተነሳው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ወደ ግጭት እንዳያመራ መንግስት እጁን ከጉዳዩ እንዲሰብስብና በሃገር ሽማግሌዎች እንዲፈታ ጥሪ ቀረበ ። በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበር በውዝግቡ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የወላይታ ህዝብ የሲዳማን ህዝብ ጨምሮ ከሁለቱ ጎረቤቶቹ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖርን በማስታወስ አሁን የገጠመንም ችግር ከሲዳማ ህዝብ ጋር በመነጋገር እንዲፈታው ያለውን እምነት ገልጿል ። የውዝግቡ መነሻ የሆነውንና አሁን ...

Read More »

በአማራ ክልል ስራቸውን የሚለቁ አመራሮች ቁጥር እያሻቀበ ነው

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት የበላይነት በሚዘወረው ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ስራቸውን የሚለቁ የፖሊስ አዛዦች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ፣ እስካሁን ባለው መረጃ ከ21 በላይ ኮማንደሮች ስራቸውን ለቀዋል። ትናንት በነበረው ግምገማ በባህርዳር የጣና ክ/ከተማ ሃላፊ ኮ/ር በላይ ደምሴ ፣ የህዳር 11 ክ/ከተማ ሃላፊ ኮማንደር አልምነው አደመ፣ የበላይ ዘለቀ ክፍለከተማ ...

Read More »

የደቡብ አሪ ወረዳ አስተዳደር መምህራኑን ለማስፈራራት እየሞከረ ነው

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወረዳው መምህራን እንደሚሉት ከሰኔ ወር ደሞዛቸው ላይ ያለፈቃዳቸው 30 በመቶ ተቆርጦ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ሊሰጥባቸው መሆኑን በመቃወም ፊርማቸውን አሰባስበው ካስገቡ በሁዋላ ፣ ሚስጢራችንን “ለጸረ ሰላም ሃይሎች አሳልፋችሁ ሰጥታችሁዋል” በሚል ማስፈራሪያ እየደረሳቸው ነው። መምህራኑ ማስፈራሪያውን ወደ ጎን በማለት አሁንም በአቋማቸው በመጽናት ጥያቄያችን ይመለስልን በማለት እየተጠየቁ ነው። በመጋቢት ወር መምህራኑ ...

Read More »

በሃረር በተጀመረው የዲያስፖራ ቀን በአል የመንግስት መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ በመደረጉ ህዝቡ ሲጉላላ ዋለ

ሰኔ ፳፰ ( ሃያ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው ዛሬ ረቡዕ በተጀመረው የዲያስፖራ ቀን በአል ላይ ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና አቶ አባይ ጸሃየ የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ አጠቃላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በመዘጋታቸው ህብረተሰቡ አገልግሎት ለማግኘት ሲንገላታ ውሎአል። መረጃዎቸ እንደሚያሳዩት አጠቃላይ የዝግጅቱን ሃላፊነት የወሰዱት ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች ናቸው። አጠቃላይ ዝግጅቱ ለአንድ ...

Read More »