(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 18/2009) በእነ መልካሙ ክንፉ የክስ መዝገብ ከወንድሙ ቦንሳ በየነ ጋር ከኦነግ ጋር ተባብራችኋል በሚል ክስ የቀረበበት አየለ በየነ ለዘጠኝ ወራት በማእከላዊ እስር ቤት መቆየቱን ጓደኞቹ ሐምሌ 18/2009 በዋለው ችሎት ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። የጸር ሽብር ህጉ ከሚፈቅደው ግዜ በላይ ተጨማሪ 5 ወራት በአጠቃላይ ዘጠኝ ወራት በማእከላዊ ምርመራ በእስርና በምርመራ ላይ መቆየታቸውን የገለጹት የወጣት አየለ በየነ አባሪዎቹ ህክምና ለማግኘት በተደጋጋሚ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ብቻ ሶስት ሺ ቤቶች ሊፈርሱ ነው
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 18/2009)የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አንዴ በግብር፣ሌላ ጊዜ በመፈናቀል ሲብስ ደግሞ በኑሮ ውድነት በአገዛዙ መከራቸውን እያዩ መሆናቸውን ይናገራሉ። አበሳና መከራው ግፍና በደሉ የበዛባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እሮሮአቸውን ለሮይተርስ ገልጸዋል።ሮይተርስ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በ360 ሔክታር ላይ የሚኖሩና 3 ሺ የሚደርሱ ቤቶቻቸው ከሚፈርስባቸው መካከል ያሉትን ነበር። እናም ነዋሪዎቹ ከኖርንበት አካባቢና ቀየ ሀብት ንብረታችንን ጥለን እንድንሄድ ተገደናል ነው ያሉት። አቡበከር በፈራረሰ የንግድ ማእከሉ ...
Read More »በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የመንግስት ባለስልጣናትና ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
(ኢሳት ዜና– ሐምሌ 18/2009) የመንግስት ባለስልጣናቱንና ነጋዴዎቹን ማሰር የተጀመረው ዛሬ መሆኑን የገለጹት የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን እስራቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል። ስለታሰሩት ነጋዴዎችም ሆነ ባለስልጣናት ማንነት የተገለጸ ነገር የለም።የመገናኛ ብዙሃኑ ስለታሳሪዎቹ ማንነት ዝርዝር መረጃው እንደደረሳቸው እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ቀን ላይ ይፋ የሆነው የባለስልጣናቱና የነጋዴዎቹ እስራት በመንግስት ባለስልጣናትም ሆነ በሚመለከታቸው የህግ አስፈጻሚ አካላት ይፋዊ መግለጫ ሳይሰጥበት ከቆየ በኋላ ማምሻውን የኮሚኔኬሽን ...
Read More »እየተካሄደ ያለው የነጋዴዎች አድማ እንደቀጠለ ነው
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላለፉት 2 ሳምንታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የሰነበተው የነጋዴዎች አድማ ዛሬም ቀጥሎአል። በታላቁ መርካቶ ገበያ ትናንት ሰኞ የተጀመረውን አድማ ለማስቆም ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የደህንነትና የፖሊስ ሰራዊት በማሰማራት በነጋዴዎች ላይ ማስፈራሪያ ሲያደርግ ቢውልም፣ ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች መደብሮች ተዘግተው ታይተዋል። በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ቄራ የገበያ አዳራሽ ደግሞ ...
Read More »ህወሃት በአገሪቱ ለሚታየው ችግርና ለኢህአዴግ ውድቀት ብአዴንን ተጠያቂ አደረገ። የብአዴን አመራሮች የክልሉ ጸጥታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው በማለት ተናግረዋል።
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብአዴን የክልል አመራሮችን፣ ሁሉም የቢሮ ምክትል ኃላፊዎችን እንዲሁም በጥንቃቄ የመረጣቸውን አባሎቹንና አገዛዙን የደግፋሉ ያላቸውን የሃገር ሽማግሌዎች ቡድን ይዞ መቀሌ ቢሰነበትም፣ ያገኘው መልስ ወቀሳና ተጠያቂነትን ያዘለ ትችት ብቻ እንደነበር ምንጮች ይገልጻሉ። ብአዴንና ህወሃት የህዝብ ለህዝብ ፣ የከፍተኛ አመራሮች እና የሁለቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ብቻ የተገኙበትን “ሶስትዮሽ” የተባለውን ውይይት አድርገዋል። ...
Read More »በሽብር ወንጀል የተከሰሰው ወጣት ህክምና ተከልክሎ ህይወቱ ማለፉ ተዘገበ
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው የችሎቱን ውሎ ተከታትሎ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንደዘገበው በእነ መልካሙ ክንፈ የክስ መዝገብ በሽብር ተከሶ ቂሊንጦ እስር ቤት ታስሮ የነበረው ወጣት አየለ በየነ ነገሰ ፣ ህክምና እንዳያገኝ ተከልክሎ ህይወቱ አልፏል። ወጣት አየለ በየነ ህክምና ተከልክሎ ለሞት እንደተዳረገ በአባሪነት የተከሱት እስረኞች፣ ሀምሌ 18/2009 ዓ.ም ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ...
Read More »በጉጂ ኦሮሞዎቸና በደቡብ ክልል ልዩ ሃይል መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ ሰዎች ተገደሉ
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ከሁለት ቀናት በፊት የጉጆ ኦሮሞዎች ከብት መወሰዱን ተከትሎ በኮሬ ማህበረሰብና በጉጂ ኦሮሞዎች መካከል ግጭት ቢነሳም፣ የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ጣልቃ በመግባትና በጉጂዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር 3 የጉጂ ብሄረሰብ አባላት ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ወደ ቡሌ ሆራ ሆስፒታል ተወስደዋል። ግጭቱ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ...
Read More »ፖሊስ በወልቃይት ኮሚቴዎች ላይ አንድ ምስክር ለማቅረብ የበጀት እጥረት ገጥሞኛል አለ
ሐምሌ ፲፰ ( አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊስ በሽብር ተከሰው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙት የወልቃይት ኮሚቴ አባላት ላይ በተደጋጋሚ ያልቀረበውን አንድ ምስክር አስሮ እንዲያቀርብ ታዞ የነበር ቢሆንም ምስክሩ የሚኖረው ትግራይ ክልል ውስጥ በመሆኑና በጀት ስላልተለቀቀልኝ ምስክሩን አስሮ የሚያመጣ አባል መላክ አልቻልኩም ሲል ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት መልሱን በደብዳቤ ገልፆአል። ...
Read More »ሁለት ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ አንገታቸው ተቀልቶ ተገደሉ
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 17/2009)ባራሂ መንገሻና ተወልደ ገብረስላሴ በሪያድ ከተማ ፓኪስታናዊውን የታክሲ ሹፌሩ ራቅ ወዳለ ስፍራ በመወሰድና በጩቤ በማስፈራራት አንገቱን በገመድ አንቀው ከገደሉት በኋላ ከመኪናው ወንበር ጋር አስረውት መሄዳቸውን ነው የሳውዲአረቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ያስታወቀው። ኢትዮጵያውያኑ የታክሲ ሹፌሩን ከገደሉት በኋላ ገንዘቡን ዘርፈው እኩል መከፋፈላቸውን የሀገሪቱን ባላስልጣናትን ጠቅሶ ሪያድ ዴይሊ ዘግቧል። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ወንጀሉን መፈጸማቸውን በማመናቸውና በማስረጃ በመረጋገጡ አንገታቸው ተቀልቶ በሞት እንዲቀጡ መደረጉን ...
Read More »ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘ አንድ ስፔናዊ በዝሆን ተመቶ ህይወቱ አለፈ
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 17/2009)በስፔን የሚታተመው እለታዊ ጋዜጣ ላቫንጋርዲያ ሐምሌ 16/2009 ባወጣው እትሙ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘ አንድ ስፔናዊ በዝሆን ተመቶ ህይወቱ ማልፉን አስነብቧል። ስሙ ያልተጠቀሰው ጎብኚ ጨበራ ጩርጨራ በተባለውና ደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኘው የእንስሳት መጠበቂያ ስፍራ ከባለቤቱ ጋር ለጉብኝት የወጡት ከሳምንት በፊት ነበር። ጎብኚው ለአደጋ የተጋለጠው ከመኪናው ወርዶ በቅርብ ርቀት ዝሆኑን ፎቶ ለማንሳት በሞከረበት ወቅትም እንደሆነ ከዘገባው መረዳት ተችሏል። ጋዜጣው የአይን እማኞችን ...
Read More »