.የኢሳት አማርኛ ዜና

በግብር ተመን የተነሳ በመላ ሀገሪቱ እየተደረገ ያለው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 25/2009)በግብር ተመን የተነሳ በመላ ሀገሪቱ እየተደረገ ያለው ተቃውሞ መቀጠሉን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ መረጃዎች አመለከቱ። ምስራቅ ጎጃም በበርካታ ከተሞች የስራ ማቆም አድማው እንደቀጠለ ነው። አዳዲስ ከተሞችም በመቀላቀላ ላይ ናቸው።በሰሜን ጎንደር ዳባርቅም ዛሬ የአድማ ርምጃ ተወስዷል።የስራ ማቆም አድማ በተደረገባቸው ከተሞች የስርአቱ ወታደሮችና የፖሊስ ሃይል መሰማራታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ነጋዴው ማህበረሰብ አንድ ላይ እንዳይነሳ የግብር ተመኑን እየነጣጠሉ እንዲደርስ ማድረጋቸው እየተገለጸ ነው። ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን አይሁዶች አላግባብ እየተጨቆኑ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 25/2009)የእስራኤል ጺዮናውያን እያራመዱት ባሉት ዘረኝነት በኢትዮጵያውያን አይሁዶች ላይ የከፋ ሰቆቃ ማሳደሩን አንድ ዘገባ አመለከተ። አህሉልባይት የተባለው የዜና ወኪል እንዳወጣው ሪፖርት ከሆነ ጺዮናውያኑ የኢትዮጵያውያኑን ጉልበት አላግባብ እየበዘበዙ መሆኑን ያመለክታል። ዘረኝነትን እያራመዱ ያሉት ጺዮናውያን በሀገሪቱ ቁልፍና ከፍተኛ የሚባሉ ቦታዎችን የያዙና የሚኖሩትም የቅንጦት በሚባሉ ዘመናዊ ቤቶች ነው። በዘመናዊ ቤቶቻቸው ውስጥ ደግሞ ኢትዮጵያውያን አይሁዶችን የሚያሰሩት እንደጥንቱ የባሮች ስርአት ነው ይላል ዘገባው። ...

Read More »

ጫት በኢትዮጵያ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 25/2009)ጫት በኢትዮጵያ እጅግ አደገኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና የሀገሪቱን አምራች ዜጋ የከፋ አዘቅት ውስጥ እየከተተው መሆኑን በአንድ ጥናት ላይ ተገለጸ። በማህበራዊ ጥናት መድረክ አማካኝነት የተደረገው ጥናት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የጫት አምባሳደር ሆነዋል ሲል አትቷል። በአዳማ ናዝሬት ብቻ 3 ሺ የጫት ቤቶች እንዳሉ ተጠቁሟል።እንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪ በጫት ስርቆት የተነሳ በተፈጠረ ጸብ ህይወቱ አልፏል ተብሏል። ከሀገር ቤት የሚሰራጨው ሸገር ኤፍ ...

Read More »

የወልቃይት ማንነት ጥያቄ ያነሱ 12 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ተከሰሱ

(ኢሳት ዜና–ሀምሌ 25/2009)የወልቃይት ማንነት ጥያቄ ያነሱ 12 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ተከሰሱ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በክሱ ላይ የሽብር ቡድን አመራር መባላቸውን ጠበቆች ተቃውመዋል ተከሳሾቹ ከጎቤ መልኬና ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር በመገናኘት ወልቃይት ውስጥ የሚገኙትን የመንግስት ደጋፊዎችና የትግራይ ተወላጆችን የሰፈራ ቦታ በመለየት ጥቃት ለመፈፀም ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄን ያነሱ 12ቱ ግለሰቦች ‹‹የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ...

Read More »

የቀድሞው የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ የአሸባሪነት ክስ ተመሰረተባቸው።

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 25/2009)የቀድሞው የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት አማረ የአሸባሪነት ክስ ተመሰረተባቸው። አቶ ማሙሸት አማረ የጎንደርንና የጎጃምን አመጽ በማስተባበር እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በማቋቋም ተወንጅለዋል። የአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ማሙሸት አማረ ከመአሕድ ምስረታ ጀምሮ በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የቆዩና በኋላም በመኢአድና ቅንጅት ውስጥ በማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ማክሰኞ ሐምሌ 25/2009 የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ማሙሸት አማረ በኦሮሚያ ክልል ...

Read More »

ዶክተር መራራ ጉዲና ሁለት እጃቸውን ወደ ኋላ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 25/2009)ታዋቂው ፖለቲከኛና የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ዶክተር መራራ ጉዲና ሁለት እጃቸውን ወደ ኋላ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ። በዘረፋ የታሰሩ እንዲሁም ነፍስ ያጠፉ ግለሰቦች ላይ የማይፈጸም ድርጊት ዶክተር መራራ ላይ መከሰቱ አነጋጋሪ ሆኗል። ዶክተር መራራ ጉዲና ሁለት እጃቸውን ወደ ኋላ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት የማቅረቡ ርምጃ እሳቸውን በማዋረድ የደጋፊዎቻቸውን ቅስም ለመስበር ነው የሚለው የበርካቶች እምነት ነው።ርምጃው ደግሞ ቁጣን ...

Read More »

በኬንያ አንድ ከፍተኛ የምርጫ ኮሚሽን ባለስልጣን ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 24/2009) በኬንያ አንድ ከፍተኛ የምርጫ ኮሚሽን ባለስልጣን መገደላቸው ተነገረ። አንድ ሳምንት በቀረው የኬንያ ምርጫ ባለስልጣኑ መገደላቸው በሀገሪቱ ከፍተኛ ወጥረትን ፈጥሯል በኬንያ ተገደሉ የተባሉት ባለስልጣን የመረጃና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የነበሩና ከፍተኛ የሚባል ሰቆቃ ተፈጽሞባቸው መገደላቸው ተነግሯል። ቸሪስ ማሳንዶ የተባሉት እኒሁ ባለስልጣን ተገድለው ከመገኘታቸው በፊት ለ3 ቀናት ተሰውረው እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል። በኬንያ በሚቀጥለው ማክሰኞ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።በዚሁም ...

Read More »

ከግብር ጭማሪው ጋር በተያያዘ የተጀመረው ተቃውሞ በስራ ማቆም አድማና ፍቃድ በመመለስ ቀጥሏል

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 24/2009)ከግብር ጭማሪው ጋር በተያያዘ የተጀመረው ተቃውሞ በተለያዩ ከተሞች በስራ ማቆም አድማና ፍቃድ በመመለስ መቀጠሉ ታወቀ። በአዲስ አበባ የተቃውሞ ጥሪ በአንዳንድ አካባቢዎች ተበትኗል።ስለ ግብር የተጠራው ስብሰባም አጀንዳው በመቀየሩ ሕዝቡ ስብሰባውን ረግጦ መውጣቱ ተገልጿል። በምስራቅ ጎጃም በደብረማርቆስ በተወሰኑ የንግድ ቦታዎች የስራ ማቆም አድማ ተደርጓል።ደብረወርቅ ካለፈው አርብ ጀምሮ በአድማ ላይ እንደሆነች የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በባህርዳር ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በጎንደር ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ህብረት ለለውጥ ከሚታገሉ ከማናቸውም ሃይሎች ጋር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 24/2009)የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ህብረት ኢትዮጵያ ውስጥ ለለውጥ ከሚታገሉ ከማናቸውም ሃይሎች ጋር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። ንቅናቄው ይህን ያስታወቀው 3ኛውን አመታዊ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ባካሄደበት ወቅት ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ህብረት 3ኛው አመታዊ ጉባኤ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄዷል። ህብረቱ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሀምሌ 29ና 30 ባደረገው አመታዊ ጉባኤ የአመታዊ አፈጻጸም ሪፖርቱን አዳምጧል። በማስከተልም ተጋባዥ እንግዶች በንቅናቄው የትላንትና የሚቀጥሉት ጉዞዎች ላይ ...

Read More »

ለሜቴክ የሸጡ ሁለት መርከቦች ጅቡቲ ወደብ ላይ ያለስራ ስድስት ወራት መቆማቸው ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 24/2009)የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት ኢንተርፕራይዝ በመንግስት ትእዛዝ ለሜቴክ የሸጣቸው ሁለት መርከቦች ጅቡቲ ወደብ ላይ ያለስራ ስድስት ወራት መቆማቸው ተገለጸ። ከዚህ ጋር ተያይዞም ሐገሪቱ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ያህል ያለኣአግባብ ማውጣቷንና እየተፈጸሙ ባሉ ሕገ-ወጥ ርምጃዎች የሃገሪቱ መልካም ስም እየተጎዳና ገጽታዋ እየተበላሸ መሆኑም ተገልጿል። በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጻፉት ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ሜቴክ ...

Read More »