.የኢሳት አማርኛ ዜና

አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 27/2009)የቀድሞው የብአዴን ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ በባህርዳር ከሚገኘው ፓፒረስ ሆቴል የ75 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው የአካባቢው የደህንነት ሃላፊ ሆነው የቆዩት አቶ አያሌው መንገሻ ይፋ አደረጉ። አቶ አዲሱ ለገሰ በይፋ የፓፒረስ ሆቴል ባለቤት በመሆን ከሚታወቁትና አሁን በሕይወት ከሌሉት አቶ ጠብቀው ባሌ ጋር የንግድ ግንኙነት የጀመሩት የሽግግር መንግስቱ ጊዜ የባህርዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ምርቶችን እንዲያከፋፍሉ ያለጨረታ በመስጠት ...

Read More »

የመብራትና ውሃ እጥረት በመላ ሃገሪቱ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 27/2009) የመብራትና ውሃ እጥረት በመላ ሃገሪቱ ህዝቡን ለከፍተኛ ችግር እየዳረገ መሆኑን ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ። በመዲናይቱ አዲስ አበባ የኤሌክትሪክና የውሃ እጥረት እየተባባሰ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ንጽህና የጎደለው ውሃ ከመጠቀም ባለፈ ዝናብ እየጠበቁ ውሃ ማጠራቀምና ለእለታዊ ፍጆታ ማዋል እየተለመደ መጥቷል። በአማራ ክልልም የውሃና የኤሌክትሪክ እጥረቱ በህዝቡ ላይ የፈጠረው አደጋ እየከፋ መምጣቱ ተገልጿል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍልም በተለያዩ አካባቢዎች መብራትና ...

Read More »

በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተጣለው የቀን ገቢ ግብር እየተከፈለ እንዳልሆነ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 27/2009) የግብር መክፈያው የጊዜ ገደብ ሐምሌ 30 እየተቃረበ ቢመጣም በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች የንግዱ ማህበረሰብ የተጣለበትን የቀን ገቢ ግብር እየከፈለ እንዳልሆነ የደረሰን መረጃ አመለከተ። በአብዛኛው የአማራ ክልል ከተሞች ነጋዴው ግብር እንደማይከፍል በማስታወቁ የመንግስት ሃላፊዎች ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ እንደተጋቡ ተገልጿል። በሸዋ ሮቢት ለ4ኛ ቀን አድማው በቀጠለበት በዛሬው እለት ተሳትፈዋል የተባሉ የንግድ ቤቶች በመታሸግ ላይ ናቸው። በደብረታቦር ቤት ለቤት ቅስቀሳ በማድረግ ...

Read More »

አንድ የመከላከያ ባልደረባ የሆኑ ጄኔራል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 27/2009)አንድ የመከላከያ ባልደረባ የሆኑ ጄኔራል በሌብነት ወይንም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ይፋ ሆነ። ፓርላማው ለነገ የጠራው አስቸኳይ ስብሰባም ለምን እንደተጠራ ሳይነገር የሰአታት ጊዜ ቀርቶታል። የገዢው ፓርቲና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ፓርላማው የተጠራው አዳዲስ ሚኒስትሮችን ለመሾም ጭምር እንደሆነ ገልጸዋል። የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በቁጥጥር ስር ውለው ዛሬ ሐሙስ 27/2009 ፍርድ ቤት የቀረቡት ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ የተባሉ የመከላከያ ...

Read More »

ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የተባበሩት መንግስታት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ተደረጉ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 27/2009) በኢትዮጵያ ከሴቶች ወሊድ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ አገልግሎት የሰጡት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የተባበሩት መንግስታት የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ተደረጉ። ሽልማቱ የተሰጠው የተባበሩት መንግስታትን እሴቶች በበጎ ላስተዋወቁ አውስትራላውያን እውቅና በሚሰጠው ተቋም አማካኝነት ነው። ዶክተር ካትሪን ሐምሊን የሕይወት ዘመናቸውን በኢትዮጵያ ለፌስቱላ የተጋለጡ 50ሺ ሴቶችን በመታደግ አገልግሎት የሰጡ አውስትራሊያዊ ሀኪም ናቸው ዶክተር ሐምሊን እድሜ ልካቸውን ከባለቤታቸው ጋር በመሆን በፌስቱላ የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያንን በመርዳት ...

Read More »

በአማራ ክልል በአብዛኛው አካባቢ የግብር ተመን ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 26/2009)በሰሜን ሸዋ ሸዋሮቢት ነጋዴው የመታውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ ስብሰባ ተጠርቷል። በስብሰባው ላይ ግን የከተማዋ ከንቲባና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት መስማማት አልቻሉም።ነጋዴዎቹም የጀመሩትን አድማ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። በአማራ ክልል በአብዛኛው አካባቢ የግብር ተመኑ ይፋ ሆኗል። ይህን ተከትሎም አድማ ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት በመንግስት ዘንድ ተፈጥሯል። የንግዱ ማህበረሰብ በአንድነት ቅሬታውን እንዳያሰማና በተቃውሞ እንዳይነሳ በመንግስት በኩል ከተወሰዱት ርምጃዎች አንዱ የተጣለውን የግብር ተመን ...

Read More »

የአባባ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 26/2009) የአንጋፋው የኪነጥበብ ሰው የአቶ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ። ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በኢትዮጵያ የኪነጥበብ መድረክ ውስጥ የቆዩትና በኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለይም በልጆች ፕሮግራም እጅግ ታዋቂ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ሳህሉ በ93 አመታቸው ባለፈው እሁድ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። የአንጋፋው የኪነጥበብ ሰው የአቶ ተስፋዬ ሳህሉ የቀብር ስነስርአት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ...

Read More »

ኤሪክሰን ኩባንያ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 26/2009)የቴሌኮም ማስፋፊያዎችን ከኢትዮ-ቴሌኮም በመውሰድ የሚሰራው ኤሪክሰን ኩባንያ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ። የስዊዲን ኩባንያ የሆነው ኤሪክሰን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የቴሌኮም ማስፋፊያ አራት ፕሮጀክቶችን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2014 በመፈራረም ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል። ባጋጠመው የአለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ችግርና የትርፍ ማጣት ምክንያትም ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መግባቱን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ኤሪክሰን ከተረከባቸው አራት ፕሮጀክቶች መካከል በደቡብና ደቡብ ምእራብ አካባቢዎች በሚገኙት አርባምንጭ፣ወላይታ ...

Read More »

የፓርላማው ቃል አቀባይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለምን እንደተጠሩ አላውቅም አሉ

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 20/2009)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፊታችን አርብ ሐምሌ 28/2009 አስቸኳይ ስብሰባ መጠራቱን የፓርላማው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ገለጹ። ሆኖም ፓርላማው ለምን እንደተጠራ የፓርላማው ቃል አቀባይ እንደማያውቁ በሐገር ቤት ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፓርላማው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወይዘሮ አጸደ ረጋሳ ፓርላማው አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን አረጋግጠዋል። ሆኖም ፓርላማው ለምን እንደተጠራ እንደማያውቁ አመልክተዋል። አንዳንድ የገዢው ፓርቲ መገናኛ ብዙሃን ጥሪው የአስቸኳይ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የብድር ጫና በባለስልጣናት ዘንድ ጭንቀት እየፈጠረ ነው

(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 26/2009)የኢትዮጵያ የብድር ጫና ከመቼውም ጊዜ በላይ እየጨመረ በመምጣቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ባሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዘንድ ጭንቀት መኖሩ ተጠቆመ። እየጨመረ በመምጣቱ በባለስልጣናት ዘንድ ከፍተኛ ጭንቀት የፈጠረው የኢትዮጵያ የብድር ጫና በአብዛኛው የተገኘው ከቻይና መንግስት ነው ተብሏል። በኢትዮጵያ ላይ የተቆለለው ከፍተኛ የብድር ጫና በአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም/አይ ኤም ኤፍ/ ሳይቀር ሪፖርት መደረጉንም ዘገባዎች ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ የብድር ጫና በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ...

Read More »