(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 4/2009)ከአዲስ አበባ ወደ ጅጅጋ የሚወስደው መንገድ በባቢሌና በሃረር መካከል መዘጋቱን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ። በጦር መሳሪያየተደገፈ ከፍተኛ የተኩስ ለውውጥ እየተካሄ መሆኑንና መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው መንቀሳቀሱን ኤምባሲው ገልጿል። የአሜሪካ ዜጎች በባቢሌና ሃረር መካከል ባሉ ቦታዎች እንዳይጓዙ ኤምባሲው አስጠንቅቋል። በባህርዳርም አፈሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሆቴል ባለቤቶችና ከፍተኛ ነጋዴዎችም እየታሰሩ ነው። በሀዋሳ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ አድርገው ውለዋል። የመንግስት ተሽከርካሪዎችና የከተማ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በደብረታቦር ከግብርና ከአስተዳደር በደል ጋር ተያይዞ የተጀመረው አድማ መቀጠሉ ተሰማ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 3/2009) በደብረታቦር ከግብርና ከአስተዳደር በደል ጋር ተያይዞ የተጀመረው አድማ ለ3ኛ ቀን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ። በከተማዋ ሁሉም የንግድ መደብሮች ዝግ ሲሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎትም ሙሉ በሙሉ እንደቆመ ነው። የአካባቢው ካድሬዎችና ፖሊሶች የተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ በግዳጅ እየፈቱ መሆናቸው ተነግሯል። ሕዝቡ ግን የንግድ መደብሮችን በሚከፍቱና ተሽከርካሪ በሚያንቀሳቅሱት ላይ እርምጃ እንወስዳለን በማለት በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛል። በደብረታቦር ለ3ኛ ቀን የቀጠለው አድማ መረር ያለና ጠንካራ መሆኑን ...
Read More »የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት በመባል የሚታወቁት አቶ ሐብተስላሴ ታፈሰ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
(ኢሳት ዜና–ነሀሴ 3/2009)የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት በመባል የሚታወቁት አቶ ሐብተስላሴ ታፈሰ በ90 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ለረጅም አመታት የኢትዮጵያ ቱሪዝም መለያ ምልክት የሆነውን “የ13 ወር ጸጋ ፈጣሪ” የሆኑት አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ ህይወታቸው ያለፈው በባልቻ ሆስፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። የኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት የሚባሉት አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ በቱሪዝም ኮሚሽነርነትና የቱሪዝም አስጎብኝ በመሆን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶችን በማስተዋወቅ ...
Read More »አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 8 ነጥብ 5 በመቶ ደረሰ
(ኢሳት ዜና– ነሐሴ 3/2009)አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 8 ነጥብ 5 በመቶ ደረሰ። ይህ አሃዝ በፊት ከነበረው በ700 ሺ ጭማሪ አሳይቷል። የበልግ ዝናብ መዛባት፣የእንስሳት ምግብና ግጦሽ መመናመን እንዲሁም የምርት መቀነስና የውሃ እጥረት በፈጠረው ድርቅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከ7 ነጥብ 8 ሚሊየን ወደ 8 ነጥብ 5 ሚሊየን አሻቅቧል። የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ከመንግስታዊ ተቋማት፣የተባበሩት ...
Read More »የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብድር የሰጠውን ገንዘብ በማስመለስ ረገድ ችግር አለበት ተባለ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 3/2009) የመንግስት የፋይናንስ ድርጅቶች ዳይሬክተር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብድር የሰጠውን ገንዘብ በማስመለስ ረገድ ችግር እንደነበረበት አስታወቁ። በአመቱ የተበላሸ ብድር መጠንም በከፍተኛ ደረጃ በማሻቀብ 25 በመቶ መድረሱ ተገለጿል። ልማት ባንኩ ከጋምቤላ የእርሻ ኢንቨስትመነት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሀገር ሀብት ማባከኑን በራሱ በመንግስት የተካሄደው ጥናት አረጋግጧል። የመንግስት የፋይናንስ ድርጅቶች ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ልማት ባንኩ ...
Read More »ሕወሃት የአፓርታይድ ስርአትን በኢትዮጵያ ተግባራዊ እያደረገ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 3/2009)በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስልጣኑን የያዘው የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ/ሕወሃት/ቡድን የአፓርታይድ ስርአትን በመገልበጥና በኢትዮጵያ ተግባራዊ በማድረግ ኢትዮጵያውያንን እየጨቆነና እየመዘበረ መሆኑን አንድ አሜሪካዊ የሕዝባዊ ንቅናቄ ኤክስፐርት ገለጹ። አሜሪካዊው ኢኮኖሚስትና የህዝባዊ ንቅናቄ ኤክስፐርት ዴቪድ ስቴማን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ የአፓርታይድ ስርአት በሚገባ ተጠንቶ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ብዙሃኑ እየተገፋ መሆኑን ተናግረዋል። አሜሪካዊው ኢኮኖሚስትና የህዝባዊ ንቅናቄ ኤክስፐርት ዴቪድ ስቴማን ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጋር ...
Read More »በኢትዮጵያ ዘረፋ ከሚፈጸምባቸው መስኮች አንዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 2/2009) በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ከሚባክንባቸውና ዘረፋ ከሚፈጸምባቸው መስኮች አንዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በተለይ ለባለስልጣናት የውጭ ሀገር ጉዞ በሚል ንግድ ባንክ የሚሰጠው ቪዛ ካርድ ሒሳቡ የማይወራረድ በመሆኑ ለከፍተኛ ብክነት ተጋልጧል። ለአንድ ጉዞ ለአንዳንዶች ከህግ ውጪ እስከ አንድ መቶ ሺ ዶላር እንድሚሰጣቸውም ምንጮች ገልጸዋል። በቪዛ ካርድ ከፍተኛ ገንዘብ በመውሰድ ከሚጠቀሙ ባለስልጣናት አንዱና ግንባር ቀደሙ ዶክተር አርከበ ...
Read More »የአምቦና የወሊሶ ነዋሪዎች የጀመሩት አድማ ወደ ታሪካዊቷ ጊንጪና ጉደር መሻገሩ ታወቀ
(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 2/2009) የወህኒ ቤት ሃላፊዎች በዶክተር መራራ ላይ የሚፈጽሙት ኢሰብአዊ ድርጊት ያስቆጣቸው የአምቦና የወሊሶ ነዋሪዎች የጀመሩት አድማ ወደ ታሪካዊቷ ጊንጪና ጉደር መሻገሩ ታወቀ። የኦሮሚያ ክልላዊ አመጽ በህዳር 2008 የተቀሰቀሰባት ጊንጪ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 2/2009 አድማውን መቀላቀሏ ይፋ ሆኗል። ዶክተር መራራ ጉዲናን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም በነጋዴዎች ላይ የተጣለው ከፍተኛ ግብር እንዲነሳ በመጠየቅ የተጀመረው አድማ በአምቦ ለሁለተኛ ...
Read More »የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄያ በአንድ ወር ለ6ኛ ግዜ ተቀጠረ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 2/2009)የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄ በአንድ ወር ለ6ኛ ግዜ ተቀጠረ። ፍርድ ቤቱ ብይኑን ዳኞች አልተሟሉም፣ዳኞች ታመዋል በሚል በማራዘም ላይ መሆኑም ታውቋል። የተመሰረተባቸው የአሸባሪነት ክስ ዝቅ ብሎ ጉዳያቸው በወንጀል ክስ እንዲታይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈው ከሶስት ሳምንት በፊት ቢሆንም የዋስትና ጥያቄያቸው ምላሽ ሳያገኝ ለ6ኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ተመልክቷል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ...
Read More »በባህርዳር የተካሄደውን አድማ ተከትሎ ወጣቶች እየታፈሱ ነው
(ኢሳት ዜና —ነሐሴ 2/2009) በባህርዳር የተካሄደውን አድማ ተከትሎ በምሽት መብራት በማጥፋት ወጣቶች እየታፈሱ መሆናቸው ተነገረ። የወጣቶቹ መታሰር በህዝብ ውስጥ ቁጣን ፈጥሯል። ከአድማው መመታት በኋላ ከፓፒረስ ሆቴል ወደ ቡና ባንክ መሄጃ ማንነቱ ያልታወቀ ወጣት ተገድሎ ተገኝቷል። በባህር ዳር የንግድ መደብሮችና ሆቴሎች ረፋዱ ላይ ተከፍተዋል።ይሁንና የአገዛዙ ባለስልጣናትና ታጣቂዎች አሁንም በስጋትና በፍርሃት ውስጥ መሆናቸው ነው የተነገረው። አድማ በታኝ ወታደሮችና የጸጥታ ሃይሎች የርእሰ መስተዳድሩን ...
Read More »