.የኢሳት አማርኛ ዜና

አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ አምስት አምባሳደሮች ወደ ሀገር ቤት ተጠሩ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009)አምባሳደር ግርማ ብሩን ጨምሮ አምስት አምባሳደሮች ወደ ሀገር ቤት መጠራታቸው ተዘገበ። በተጠሩት አምባሳደሮች ምትክ አዳዲስ ግለሰቦች እንደሚሾሙም ተመልክቷል። በማይታወቅ የገንዘብ ምንጭ በተለያዩ የንግድ ተቋማት ውስጥ ባለድርሻ መሆናቸው የሚገለጸው አምባሳደር ግርማ ብሩ የጸረ መስናው ዘመቻ እስኪያቆም በሕክምና አሳበው ሊዘገዩ እንደሚችሉም የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ። በዩ ኤስ አሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሆኑት ከአቶ ግርማ ብሩ በተጨማሪ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ስዩም መስፍን ...

Read More »

በኢትዮጵያ 16 የጥጥ እርሻ ልማት ድርጅቶች ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ተጭበረበርን አሉ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009) በኢትዮጵያ 16 የጥጥ እርሻ ልማት ድርጅቶች በአንድ የቱርክ ኩባንያ ከ21 ሚሊየን ብር በላይ መጭበርበራቸውን አመለከቱ። የጥጥ ልማት ድርጅቶቹ በደረቅ ቼክ የተጭበረበሩት ኤልሴ አዲስ በተባለ የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ ነው። የቱርኩን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኩባንያው ባለቤት 1 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ብር ተበድሮ መጥፋቱን አስታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ የጥጥ አምራቾች በጠራራ ጸሃይ በኢንቨስትመንት ስም በመጣ የቱርክ ጨርቃ ጨርቅ ...

Read More »

በ16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የ7ኝነት ደረጃን አገኘች

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009)በእንግሊዝ ለንደን በተካሄደው 16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የ7ኝነት ደረጃን አገኘች። ከአፍሪካ ደግሞ የ3ኝነት ደረጃን ይዛለች። ኢትዮጵያ እነዚህን ደረጃዎች የያዛቸው ሁለት የወርቅና ሶስት የብር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ነው። ቅዳሜ ምሽት በተካሄደው የወንዶች 5ሺ ሜትር ውድድር አትሌት ሙክታር እድሪስ ሞፋራህን በማሸነፍ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሩ ማስገኘቱ ታውቋል። በ5ሺ ሜትር ሴቶች በ10 ሺ ሜትር ርቀት ወርቅ ያስገኘችው አልማዝ አያና ሁለተኛ በመውጣትና ...

Read More »

አልማ ለገቢ ማስገኛ በሚል ያስገነባው ማተሚያ ቤት ከጥቅም ውጪ መሆኑ ተነገረ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 5/2009) የአማራ ልማት ማህበር/አልማ/ለገቢ ማስገኛ በሚል ያስገነባው ማተሚያ ቤት የህትመት ማሽኑን ሊያስገባ ባለመቻሉ 24 ሚሊየን ብር የወጣበት ግንባታ ከጥቅም ውጪ መሆኑ ተነገረ። ባልተጠና የግንባታ ዲዛይን የተሰራው ማተሚያ ቤት ከጥቅም ውጪ ከሆነ በኋላ በሌላ ቦታ ግንባታ ለማከናወን የተገዛው ከ900 በላይ ከረጢት ሲሚንቶም ተበላሽቶ መጣሉ ተነግሯል። በአያያዝ ችግር እንዲወገድ የተደረገው የአማራ ልማት ማህበር/አልማ/ ከ900 በላይ ከረጢት ሲሚንቶ ከ324 ሺ ብር ...

Read More »

160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመን ባህር ውስጥ በግዴታ መወርወራቸው ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 5/2009)160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመን ባህር ውስጥ በግዴታ መወርወራቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም አይ ኦ ኤም አስታወቀ። ድርጊቱ የተፈጸመው በግዴታ ወደ ባህር ከተወረወሩት ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን ስደተኞች 50 ዎቹ መሞታቸው በተነገረ በ24 ሰአት ጊዜ ውስጥ ነው። ተቋሙ እንዲህ አይነቱ ድርጊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊገታና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በተሰማሩት አካላት ላይም በተግባር የተደገፈ ርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲል አስጠንቅቋል። እንደ አለም ...

Read More »

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ህዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 5/2009)በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ህዝባዊ ቁጣ ተቀስቅሷል። በሰሜን ጎንደር በመተማ፡ በአይከል፡ አርባያ፡ በበለሳ ህዝባዊ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ ወደ ደብረማርቆስ የሚወስደው መንገድ በህዝቡ ተዘግቷል። በምስራቅ ሀረርጌ በባቢሌ መስመር የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሷል።በርካታ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። በወልቃይት አዲረመጽ የህወሃት ታጣቂዎች ገብተው ህዝቡን እያሸበሩት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በወሊሶና ጊንጪ አድማው እንደቀጠለ ነው። በሀዋሳ በባጃጅ አሽከርካሪዎች ትላንት ...

Read More »

በሌብነት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን የማሰሩ ተግባር መቀጠሉ ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 5/2009) በሌብነት የተጠረጠሩ የ210 ግለሰቦች ሀብትና ንብረት በታገደ ማግስት ተጨማሪ ተጠርጠሪዎችን የማሰሩ ርምጃ መቀጠሉ ታወቀ። መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ጠቅላይ አቃቢ ህግን ጠቅሰው እንደዘገቡት የመንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ በቁጥጥር ስር ውለዋል። በዚህም በሌብነት ተጠርጥረው ወደ ወህኒ የወረዱ ታሳሪዎች ቁጥር 55 ደርሷል። የመንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ መታሰራቸውን ተከትሎ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የታሰሩትን ...

Read More »

በሌብነት የተጠረጠሩት የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ነጋዴዎችና ደላሎች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 4/2009 ሰሞኑን) በሌብነት ተጠርጥረው ወደ እስር ቤት ከተጋዙት የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ነጋዴዎችና ደላሎች ውስጥ 45ቱ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለመመልከት ቀጠሮ የሰጠው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ ወደ ወህኒ ቤት እንዲመለሱ አድርጓል። ባለፈው ሰኞ ፍርድ ቤት የቀረቡት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አለማየሁ ጉንጆ በእስረኛ በተጨናነቀና መላወሻ በሌለው ክፍል ውስጥ መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት ገልጸዋል። ሰኞ ነሐሴ ...

Read More »

የ210 ግለሰቦችና ተቋማት ንብረት ታገደ

(ኢሳት ዜና– ነሐሴ 4/2009) በሌብነት ወንጀል የተጠረጠሩ የ210 ግለሰቦችና ተቋማት ንብረት መታገዱን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። የታሰሩት ግለሰቦች 54 ሲሆኑ የታገደው የ210 ግለሰቦችና ተቋማት ንብረት መሆኑ ተጨማሪ የሚታሰሩ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን የሚጠቁም ሆኗል። የተጠርጣሪዎቹና ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ንብረታቸው ከታገደው ውስጥ በከፊሉን የሕወሃት ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና ይፋ አድርጓል። በዚህም አሰር ኮንስትራክሽኝ፣ግምሹ በየነ ኮንስትራክሽን፣ቲና ኮንስትራክሽን፣ዲ ኤም ሲ ኮንስትራክሽን፣የማነ ግርማይ ጠቅላላ ...

Read More »

የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደረገ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 4/2009) የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደረገ። በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት የቀረቡትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዋስትና የተከለከሉት ለ5 ጊዜያት ያህል በጉዳዩ ላይ ፍርድ ቤት ከተመላለሱ በኋላ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ የታሰሩትና በአሸባሪነት የተከሰሱት አቶ በቀለ ገርባ ከወር በፊት ክሳቸው ከአሸባሪነት ወደ ...

Read More »