.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት መባባሱ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 12/2009)በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ድንበር ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት መባባሱ ተገለጸ። በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሃት የተለየ ድጋፍ የሚደረግለት የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አወዛጋቢ በተባሉ ቀበሌዎች የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ግድያ፣ ድብደባና አስገድዶ መድፈር እየፈጸመ መሆኑንም ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ኦብነግ ለኢሳት እንዳስታወቀው የህወሃት መንግስት በሶማሌ ልዩ ሃይልና በስውር ባስታጠቃቸው የኦህዴድ ሚሊሺያዎች አማካኝነት የእርስ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ ሶስት ልጆቻቸው ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 12/2009)ከአሜሪካ ወደ ካናዳ አልበርታ አምርተው በጉብኝት ላይ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ ሶስት ልጆቻቸው ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተሰማ። በአደጋው ከባድ የመቁስል አደጋ የደረሰባቸው የልጆቹ አባትና እናት ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን አንድ ሕጻንን ጭምሮ 3ቱ ልጆቻቸው ግን አደጋው በደረሰበት ስፍራ ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል። ከአሜሪካ ወደ ካናዳ አልበርታ አምርተው በጉብኝት ላይ በነበሩ ኢትዮጵያውያን የአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ ...

Read More »

በቀበሌ ቤት የሚገኙ የወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች ከአቅማቸው በላይ ከፍተኛ የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው

(ኢሳት ዜና ነሐሴ 12/2009) በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉና በቀበሌ ቤት የሚገኙ የወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች ከአቅማቸው በላይ ከፍተኛ የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወሰነባቸው። ለ30 እና 40 ዓመታት 5 ብር በወር ይከፍሉ የነበሩ በአዲሱ ተመን ከ200 እስከ 300 ብር እንዲከፍሉ እየተጠየቁ መሆናቸውን ከወሊሶ ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ነዋሪው በወር በደመወዝ የማያገኘውን ብር ለቀበሌ ቤት እንዲከፍል በመወሰኑ ቁጣውን እየገለጸ መሆኑም ታውቋል። በወሊሶ ባለፈው ...

Read More »

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳና የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ ትእዛዝ ተሰጠ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 12/2009) ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳና የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ትእዛዝ ሰጠ። የሕወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ከጥቅምት 27-ጥቅምት 29/2010 ባለው ጊዜ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የታዘዙት ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/አመራሮች ከእነ አቶ በቀለ ገርባ ጋር በተያያዘ የመከላከያ ምስክሮች እንዲሆኑ በመጠራታቸው ነው። በእነ አቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ለአራት ...

Read More »

እስክንድር ነጋም ሆነ አንዱአለም አራጌ አሸባሪዎች ሳይሆኑ የይስሙላ ፍርድ ቤት ሰለባዎች ናቸው ሲሉ ኬት ባርት የተባሉ የመብት ተሟጋች ገለጹ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 11/2009) በሽብር ወንጀል የተከሰሱትና የተፈረደባቸው እስክንድር ነጋም ሆነ አንዱአለም አራጌ አሸባሪዎች ሳይሆኑ የይስሙላ ፍርድ ቤት ሰለባዎች ናቸው ሲሉ ኬት ባርት የተባሉ የመብት ተሟጋች ገለጹ። ፍሪደም ናው የተባለው ተቋም የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት ኬት ባርት መሰረታዊ የሰው ልጆች መብቶችን ወንጀል እንዲያደርግ በተቃኘው ህግ ዜጎች ዋጋ እየከፈሉ መሆናቸውን ተናግረዋል። መቀመጫውን በዩኤስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የመብት ተሟጋቹ ፍሪደም ናው የሕግ ...

Read More »

በጋምቤላ ክልል መሬት ተነጥቀው የነበሩ 186 ባለሃብቶች በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ትእዛዝ ተመለሰላቸው

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 11/2009) በጋምቤላ ክልል መሬት ተነጥቀው የነበሩ 186 ባለሃብቶች በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ትእዛዝ ተመለሰላቸው። በክልሉ ከነበሩ 6መቶ ያህል ኢንቬስተሮች የያዙትን መሬት በአግባቡ አላለሙም በሚል 296 ያህሉ ይዞታቸውን በጋምቤላ መስተዳድር ተነጥቀው ነበር። ባለሃብቶቹ ይህንኑ በመቃወም ቅሬታ በማቅረባቸው በአቶ አርከበ እቁባይ የተመራው አጣሪ ኮሚቴ በተለይ የትግራይ ባለሃብቶች ናቸው ለተባሉት 186 ባለሃብቶች መሬታቸው እንዲመለስ ተደርጓል። በኢትዮጵያ ባለው ህግ መሰረት የመሬት ሊዝ ...

Read More »

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ትእዛዝ ውጪ ማንኛውም ባለስልጣንም ሆነ የመንግስት ሰራተኛ ወደ ውጭ ሀገር መውጣት አይችልም ተባለ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 11/2009) ማንኛውም ባለስልጣንም ሆነ የመንግስት ሰራተኛ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ሲወጣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መፈቀድ እንዳለበት መመሪያ ወጣ። የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በሕዝብ ገንዘብ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን እንዳይዙ፣ ድል ያለ ድግስ እንዳይደግሱና ወጭአቸውን እንዲቆጥቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መመሪያ አውጥቷል። ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ከእንግዲህ አዲስ ቢሮ መከራየትም አይችሉም ተብሏል። የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው በሚኒስትሮች ምክር ...

Read More »

የሕዋሃት ታጋዮች አጥንታቸውን የከሰከሱት ትግራይን ለማልማት ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 11/2009) የሕዋሃት ታጋዮች አጥንታቸውን የከሰከሱት ትግራይ እንድትለማ ነው በማለት በአንድ ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት በድረገጹ አስታወቀ።   ጽህፈት ቤቱ በፌስቡክ ድረገጹ እንደገለጸው በ1984 በትግራይ መቀሌ የሕወሃት ምስረታ በአል ሲከበር አቶ መለስ ለትግራይ ወጣቶች የተከሰከሰው አጥንት ለትግራይ ልማት ሲባል መሆኑን በይፋ ተናግረዋል።   በዚያን ወቅት አቶ መለስ እኔ የተፈጠርኩት ከዚህ ወርቅ ...

Read More »

በ2017 የተፈናቀሉ አፍሪካውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፋ መሆኑ ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 11/2009) በ2017 ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ አፍሪካውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፋ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በርካታ ዜጎች ይፈናቀሉባቸው ተብለው በግንባር ቀደምትነት ከተቀመጡት ሀገራት ተርታም ኢትዮጵያ አንዷ ሆናለች። አለም አቀፉን የሰብአዊነት ቀን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ባወጣው መግለጫ የአፍሪካውያን የኑሮ ቀውስ በተያዘው አመት ተባብሶ ቀጥሏል ይላል። የህዝብ መፈናቀል ከየትኛውም አመት ልቆ መታየቱንም ይፋ አድርጓል። እንደ መግለጫው ከሆነ በ2017 ብቻ 20 ...

Read More »

ባለፉት 25ዓመታት የዳኝነት ነጻነት የለም ሲሉ የአማራ ክልል ዳኞች ገለጹ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 10/2009) ባለፉት 25ዓመታት የዳኝነት ነጻነት የለም ሲሉ የአማራ ክልል ዳኞች ገለጹ። በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና በፍትህ ቢሮ ሃላፊው በአቶ ፍርዴ በተመራውና አቃቢያን ህግ፡ ፖሊስ፡ ዳኞችና ሌሎች የፍትህ አካላት በተገኙበት ስብሰባ ላይ ዳኞች በአንድ ድምጽ እንደገለጹት በአማራ ክልል የዳኝነት ነጻነት የሚባል ነገር የለም። የፖለቲካ ጫና የበዛበት፡ በህግ አግባብ ያስረነው በቀጭን ትዕዛዝ የሚፈታበት፡ ነጻ ተብሎ በፍርድ ቤት የተለቀቀ ወዲያው ...

Read More »