.የኢሳት አማርኛ ዜና

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ለአቤቱታ አዲስ አበባ ገቡ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 18/2009) በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች በልዩ ፖሊስ የሚፈጸመውን ጭፍጨፋ በመቃወም ለአቤቱታ አዲስ አበባ መግባታቸው ተነገረ። የሀገር ሽማግሌዎቹ በልዩ ፖሊስ በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ስቃይ እንዲቆም አቤቱታቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል። ከምስራቅ ሀረርጌ ወደ አዲስ አበባ ለአቤቱታ የመጡት የሀገር ሽማግሌዎች ባለፉት ወራት ብቻ በልዩ ፖሊስ የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር 55 መድረሱን ተናግረዋል። በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በሚል በ1999 ...

Read More »

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ለሁለት ተከፍለው በባህርዳር በነበረው አድማ ዙሪያ መወዛገባቸው ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 18/2009) የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ለሁለት ተከፍለው በባህርዳር በነበረው አድማ ዙሪያ መወዛገባቸው ተሰማ። በባህርዳር ከአድማው ጋር ተያይዞ የታሰሩት ታዋቂ ነጋዴዎች ሕግን መሰረት ባደረገ መልኩ የተካሔደ አልነበረም በሚል የተወሰኑት የብአዴን ማእከላዊ አባላት በግልጽ በማንሳት ተከራክረዋል። ነጋዴዎቹም ከእስር የተለቀቁት ይህ ውዝግብ በማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ከተካሄደ በኋላ በማግስቱ መሆኑ ታውቋል። ብአዴን በሶስትና በአራት የተከፈል ቡድን እንዳለውም የኢሳት ምንጮች ...

Read More »

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የተጀመረው አድማ በርካታ ከተሞችንና አካባቢዎችን ማዳረሱ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 18/2009) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የተጀመረው አድማ በርካታ ከተሞችንና አካባቢዎችን ማዳረሱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ከሕዝቡ ብሶትና በደል ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል የተጠራው አድማ በደቡብና በአማራ የተወሰኑ አካባቢዎችም መከሰቱ ታውቋል። በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ከተካሄደው ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ቀጥሎ የተካሄደው የኦሮሚያ ክልል አድማ የነጻነት ትግሉ ሀገር አቀፍ መሰረት እየያዘ መምጣቱን እንደሚያመላክት ተንታኞች ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል ወጣቶች ከትላንት እሮብ ጀምሮ ...

Read More »

ከ1ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ዛሬ ከጣሊያን ፖሊስ ጋር ተጋጩ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 18/2009)ከመኖሪያ ህንጻቸው በሌሊት የተፈናቀሉት ከ1ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ዛሬ ከጣሊያን ፖሊስ ጋር ተጋጩ። ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት በድንገት ህንጻቸውን በመውረር ከመኖሪያቸው ያስወጣቸው ፖሊስ ዛሬ በጊዜያዊነት ካረፉበት ጎዳና ላይ እንዲነሱ ለማድረግ በወሰደው እርምጃ ግጭት ተከስቶ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ጉዳት እንደደርሰባቸው ለማወቅ ተችሏል። የጣሊያን ፖሊስ እየወሰደ ያለው እርምጃ ዓለም ዓቀፍ ህግን የጣሰ ነው በሚል ከተለያዩ አካላት ተቃውሞ እየተሰማ ነው። በጣሊያን የኢትዮጵያ ...

Read More »

በሀረርና በድሬደዋ እንዲሁም በሆለታና አምቦ አካባቢዎች ዜጎቹ እንዳይንቀሳቀሱ የካናዳ መንግስት ጥሪ አቀረበ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 18/2009)በሀረርና በድሬደዋ እንዲሁም በሆለታና አምቦ አካባቢዎች ዜጎቹ እንዳይንቀሳቀሱ የካናዳ መንግስት ጥሪ አቀረበ። የካናዳ መንግስት ዜጎቹ በአካባቢዎቹ እንዳይዘዋወሩ ያዘዘው በአካባቢዎቹ የተኩስ ልውውጦች እየተካሄዱ መሆኑ ከተሰማ በኋላ ነው። የካናዳ መንግስት የኢትዮጵያን የጸጥታ ሁኔታ በትኩረት እንደሚከታተልም አስታውቋል። በጅማ ዛሬ የደረሰውና ምናልባትም የመንግስት እጅ ሳይኖርበት አይቀርም የተባለው የቦምብ ጥቃትም በሀገሪቱ ያለውን ያለመረጋጋት ሁኔታ የሚያሳይ መሆኑን መረጃዎቹ አመልክተዋል። በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እያሳሰበው ...

Read More »

በአማራ ክልል አጠቃላይ አድማ ለመጥራት እንቅስቃሴ መጀመሩ ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 17/2009) በባህርዳር በግንቦት 20 ክፍለከተማ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ተቋረጠ። ከመነሻው በአንድ ነጋዴ ተቃውሞ ሲቀርብ በተቋረጠው ስብሰባ ላይ ሁለት ነጋዴዎች አስተባብራችኋል ተብለው ታስረዋል። በዘፈቀደ የተጣለውን ግብር በግዳጅ ለማስከፈል የተጠራውን ይህን ስብሰባ ነጋዴ መቃወም ሲጀምር የልዩ ሃይል አከባቢውን መውረሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአማራ ክልል አጠቃላይ አድማ ለመጥራት እንቅስቃሴ መጀመሩንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በደምበጫና ቡሬ አካባቢ ዛሬ ሱቆችና መደብሮች ተዘግተው እንደነበረም ...

Read More »

ኤች አር 128 የተሰኘው የውሳኔ ሀሳብ ለአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ሊቀርብ ነው

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 17/2009)በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ንኡስ ኮሚቴ ተቀባይነት ያገኘውና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር የሚያስችለው ኤች አር 128 የተሰኘው የውሳኔ ሀሳብ ለአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ሊቀርብ ነው። ይህ የህግ ረቂቅ የባለስልጣናት ሀብትና ንብረት እንዲያዝ አሜሪካ ወይም ምእራብ ሀገራት እንዳይገቡ የሚጠይቅና ባለስልጣናቱ በስርአቱ ባላቸው ስልጣንም ሆነ በግላቸው የሚጠየቁበት እንደሆነ ተገልጿል። ኤች አር 128 የተሰኘው የውሳኔ ሀሳብ ...

Read More »

በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ በመላው ኦሮሚያ ዛሬ ተጀመረ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 17/2009) ለ5 ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ በመላው ኦሮሚያ ዛሬ ተጀመረ። ከሀረር እስከ ጉደር፡ ከባሌ እስከ እስከ ሰላሌ፡ ሰበታ፡ ሆለታ፡ መላው የሀረርጌ ከተሞች፡ አዲስ አበባ ዙሪያ፡ አምቦ፡ ነቀምት፡ በሁሉም የኦሮሚያ አቅጣጫዎች አድማው በይፋ ተጀምሯል። ንግድ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል። የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል። መንገዶች ላይ የሚታዩት ታጣቂዎች ናቸው። በአንዳንድ አከባቢዎች የወጣቶቹን ጥሪ ወደ ጎን አድርገው ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ...

Read More »

በአንጎላ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተካሄደ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 17/2009)ከአለማችን የሐገራት መሪዎች ለረዥም አመታት ስልጣን ላይ በመቆየት በሁለተኝነት የሚጠቀሱት የአንጎላው ፕሬዝደንት ጆሴ ኤድዋርዶ ዶሳንቶስ በሰላም ስልጣናቸውን ለመልቀቅ በወሰኑት መሰረት ርሳቸውን የሚተካ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል። የገዢው ፓርቲ መከላከያ ሚኒስትር ምናልባትም የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን ሳይረከቡ አይቀርም የሚል ቅድሚያ ግምት ተሰጥቷል። የ28 ሚሊየን ህዝብ ሀገር የሆነችውን አንጎላን ለ38 አመታት የመሩት ጆሴ ኤድዋርዶ ዶሳንቶስ ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደማይወዳደሩ በማሳወቃቸው እርሳቸውን ለመተካት ...

Read More »

በጋምቤላ፣ቤንሻንጉል፣ደቡብ ኦሞና ሌሎች አካባቢዎች በግብርና የተሰማሩ ባለሃብቶች ችግር ገጠመን አሉ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 17/2009)በጋምቤላ፣ቤንሻንጉል፣ደቡብ ኦሞና ሌሎች አካባቢዎች በግብርና የተሰማሩ ባለሃብቶች አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች እንዳጋጠማቸው ገለጹ። ልማት ባንኩን ጸረ ልማት ባንክ በማለት ፈርጀውታል። የጋምቤላ እርሻ ኢንቨስተሮች ማህበር፣የቤንሻንጉል ጉምዝ እርሻ ኢንቨስተሮች ማህበር፣የደቡብ ኦሞና ጋሞጎፋ ኢንቨስተሮች ማህበር፣የሶማሌ የእርሻ ኢንቨስተሮች ማህበርና ሌሎች በአካባቢው የተሰማሩ ማህበሮች ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ባቀረቡት የአቤቱታ ደብዳቤ አጋጠመን ያሉትን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች እንዲሁም ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎቻቸውን አቅርበዋል። አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ...

Read More »