(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010)ከአባይ ግድብ ፕሮጀክት ከ2ሺህ በላይ ሰራተኞች መቀነሳቸው ተገለጸ። በገንዘብ እጥረት ወደፊት መቀጠል ያልቻለው የግድቡ ግንባታ በመጀመሪያው ዙር ከተቀነሱት ሌላ በቀጣይ ሌሎችም እንዲዘጋጁ እንደተነገራቸው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ቀደም ሲል ለበዓል ወጥተው የነበሩ ሰራተኞች በዚያው እንዲቀሩ መድረጉንም ታውቋል። ከ8ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉት የሚነገረው የግድቡ ፕሮጀክት በተከታታይ ዙሮች ሰራተኞቹን እንደሚያሰናብት የውስጥ ምንጮች ካደረሱን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የተለያዩ የፕሮጀክቱ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችም የግድቡን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ93 ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010) በአፋር ክልል በአምቤዬራ ዞን፣በጅማ፣በደቡብ ምስራቅና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከ93 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ። የአፍሪካ ጋዜጠኞች ማዕከል/ሲ ኤ ጄ/ እንደዘገበው አዲስ አበባን በሚያዋስኑ ልዩ ዞኖችና በተጠቀሱት አካባቢዎች ካለማቋረጥ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ 18 ሺ 628 ቤተሰቦች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአፍሪካ ጋዜጠኞች ማዕከል/ሲ ኤ ጄ/ ዘገባ እንዳመለከተው ከ93 ሺ በላይ ሰዎችን ከቀያቸው ...
Read More »የእሬቻ በአል ላይ የመከላከያ፣የፌደራል ፖሊስና የጸጥታ ሃይል እንደሚሰማራ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010) እሁድ በሚከበረው የእሬቻ በአል ላይ የመከላከያ፣የፌደራል ፖሊስና የጸጥታ ሃይል እንደሚሰማራ የፌደራል ፖሊስ ገለጸ። ይህ ውሳኔ የተላለፈው የአባ ገዳዎች ምክር ቤት የታጠቀ የመንግስት ሃይልና ባለስልጣናት በበአሉ ላይ እንደማይገኙ ከገለጸ በኋላ ነው። በመንግስት ዛሬ የተሰጠው መግለጫ የአባገዳዎቹን ውሳኔ የሚሽርና መንግስት ቀደም ሲል ከሰጠው መግለጫ ጋር የሚጋጭ ነው ተብሏል። መግለጫው በበአሉ አከባበር ላይ ውጥረት እንዲነግስ ማድረጉንም ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ...
Read More »በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ከስራቸው ተባረሩ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010) በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር በኤምባሲው ሰራተኞች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ በመፈጸማቸው ከስራቸው መባረራቸው ታወቀ። በአዲስ አበባ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩት አምባሳደር ኪም ሙንሁዋን የቀረበባቸውን የወሲባዊ ትንኮሳ ድርጊት ሲመረምር የቆየው የደቡብ ኮሪያ መንግስት የዲሲፒሊን ቦርድ በድርጊቱ ተጠያቂ ስላደረጋቸው ከሃላፊነት እንዲነሱ ተወስኗል። ማክሰኞ ከአምባሳደርነታቸው የተባረሩት ሚስተር ኪም ሙንሁዋን በበርካታ የኤምባሲው ሴት ሰራተኞች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ በመፈጸም እንዲሁም ...
Read More »በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች ተጽእኖ ስር መውደቃቸው ተሰማ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010)በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞች ተጽእኖ ስር መውደቃቸውንና ለአደጋ መጋለጣቸውን ቢቢሲ ዘገበ። በናይሮቢ የኢትዮጵያ አምባሳደር ድርጊቱ አይፈጸምም ሲሉ ማስተባበያ ሰጥተዋል። ሒዩማን ራይትስ ዎች የተባለው አለም አቀፍ የመብት ተሟጋች የድርጊቱን አሳሳቢነት በተመለከተ በሳምንቱ መጀመሪያ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። የብሪታኒያው የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ የአለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎችን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ባቀረበው ዘገባ የኢትዮጵያ መንግስት ...
Read More »የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፖሊ ቴክኒክ የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም በማለታቸው ከተቋሙ ተባረሩ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010)የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፖሊ ቴክኒክ ግቢ የ4ኛና 5ኛ አመት የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም በማለታቸው ከተቋሙ መባረራቸው ተነገረ። በፌደራልና በልዩ ሃይል ተከበው ከግቢ እንዲወጡ የተደረጉት ተማሪዎች ለፈተና ዝግጅት በቂ ጊዜ አልተሰጠንም በማለታቸውና ጥያቄ በማቅረባቸው ተቋሙን ኣእዲለቁ ተገደዋል። ተማሪዎቹ የመማር ማስተማሩን ተግባር ኢዲሞክራሲያዊና ኢፍትሃዊ በሆነ መልኩ አስተጓጉላችኋልም ተብለዋል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የፖሊ ቴክኒክ ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ለፈተና በቂ ጊዜ ይሰጠን ባሉ ጸረ ሰላምና ...
Read More »ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ከእስር ተለቀቁ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010) በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ከ2 መቶ ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ታስረው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ከእስር ተለቀቁ። አቃቢ ሕግ ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ኣንዲለቀቁ ያደረገው በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ እመሰክራለሁ በማለታቸው እንደሆነ ጉዳዩን ለሚከታተለው ችሎት ገልጿል። ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 የስኳር ፕሮጀክት ለዚሁ ተብሎ የተመደበውን በጀት ተቀናሽ በማድረግ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ...
Read More »በእሬቻ በዓል ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ንግግር አያደርጉም ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010) ዕሁድ በሚከበረው የእሬቻ በዓል ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ንግግር እንዳያደርጉ መወሰኑን የኦሮሚያ አባገዳዎች ምክር ቤት አስታወቀ። በበዓሉ ላይ መሳሪያ የታጠቀ የመንግስት ሃይል እንደማይኖርም የኦሮሚያ አባገዳዎች ምክር ቤት ማስታወቁንም የቢቢሲ አማርኛው ክፍል ዘግቧል። በበዓሉ ላይ የመንግስት ሰዎች ንግግር እንዳያደርጉና ታጣቂዎች በስፍራው እንዳይኖሩ የተላለፈው የአባገዳ ምክር ቤት ውሳኔ የባለፈው ዓመት ዕልቂት ተጠያቂው ማን እንደሆነ ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው ተብሏል። ለተገደሉት ወገኖች ...
Read More »በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ከእስር ተለቀቁ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 18/2010) በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው ከ2 መቶ ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ታስረው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ከእስር ተለቀቁ። አቃቢ ሕግ ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ ኣንዲለቀቁ ያደረገው በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ እመሰክራለሁ በማለታቸው እንደሆነ ጉዳዩን ለሚከታተለው ችሎት ገልጿል። ጄኔራል ኤፍሬም ባንጌ በኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 የስኳር ፕሮጀክት ለዚሁ ተብሎ የተመደበውን በጀት ተቀናሽ በማድረግ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ...
Read More »ሳውዲአረቢያ ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ ፈቀደች
(ኢሳት ዜና–መስከረም 17/2010)በአለም ላይ ሴቶች መኪና እንዳያሽከረክሩ በሕግ ክልከላ ያደረገችው ብቸኛ ሀገር ሳውዲአረቢያ እገዳውን በማንሳት ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ ፈቀደች። የሳውዲው ንጉስ ሳልማን እገዳውን በማንሳት ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ መፍቀዳቸውን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአድናቆት ተቀብለውታል። የሴቶችን መብት ለማክበር አዎንታዊ ርምጃ ሲሉም ገልጸውታል። ሴቶች መንጃ ፈቃድ ማውጣት እንዲችሉ የሚፈቅደው ይህ የንጉሱ ውሳኔ ከ10 ወራት በኋላ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከሰኔ 24/2018 ጀምሮ ተግባራዊ ...
Read More »