(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010)የኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው ሼባ ሌዘር ኢንደስትሪ አዲስ ፋብሪካ አስመረቀ። አዲሱ ፋብሪካ ለውጭ ገበያ በሚያቀርበው ምርት በአመት ከ36 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምናዛሪ ያገኛል። በኤፈርት ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አዜብ መስፍንና በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መብራሕቱ መለስ መስከረም 22 በትግራይ ውቅሮ ከተማ የተመረቀው ይህ ፋብሪካ ለውጭ ገበያ ከሚያቀርባቸው ቆዳ ጫማዎች በተጨማሪ ያለቀላቸው የሴቶች የእጅ ቦርሳዎችን ያመርታል። የህወሃት ፖሊት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ብአዴን የቢሮ ሐላፊዎችን ማቀያየርና መመደብ መጀመሩን የኢሳት ምንጮች ገለጹ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010)በሕዝብ ተወክሏል ለሚባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት ቀርቦ ሳይጸድቅ ብአዴን የቢሮ ሐላፊዎችን ማቀያየርና መመደብ መጀመሩን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ብአዴን ሰሞኑን ያካሄደውን ግምገማ ተከትሎ የክልሉን ካቢኔ አባላት በክልሉ ምክር ቤት እንዲጸድቅ ሳይደረግ ስራ ያስጀመራቸውም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በአዲሱ ምደባ የክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ሃላፊ አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት ከሃላፊነት ተነስተው በምትካቸው አቶ እዘዝ ዋሴ መመደባቸው ይነገራል። አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት ወደ ግብርና ...
Read More »በኦሮሞና በኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች መካከል የማፈናቀሉ ሒደት መቀጠሉ ተዘገበ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010) በምስራቅ ኢትዮጵያ በኦሮሞና በኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች መካከል የማፈናቀሉ ሒደት መቀጠሉ ተዘገበ። አካባቢውን በማረጋጋትና መፈናቀሉን በመግታት በኩል ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው የመከላከያ ሰራዊት ተፈናቃዮችን እያጀበ በማመላለስ ላይ መሆኑን በስፍራው ተገኝተው ሂደቱን የተከታተሉ የሀገር ቤት ጋዜጦች ዘግበዋል። እስካለፈው ሳምንት ብቻ የኦሮሞ ተፈናቃዮች ቁጥር 67 ሺ መድረሱም ተመልክቷል። በኦሮሚያ ክልልና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የነዋሪዎቹ መፈናቀል ...
Read More »አንዱአለም አራጌ አለምአቀፍ ሕግን በመጣስ በአገዛዙ መታሰሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010) የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ አመራር የነበረው አንዱአለም አራጌ በዘፈቀደ እርምጃ አለምአቀፍ ሕግን በመጣስ በአገዛዙ መታሰሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ። ገለልተኛ ሆኖ የተቋቋመውና አግባብ ያልሆኑ እስሮችን የሚያጣራው የመንግስታቱ ድርጅት ቡድን አንዱአለም አራጌ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ጥሪ አቅርቧል። አንዱአለም አራጌ ከእስር እንዲለቀቅና የጉዳት ካሳ እንዲከፈለው የወሰነው የዘፈቀደና ሕገወጥ እስሮችን የሚያጣራው የተባበሩት መንግስታት ቡድን ነው። አምስት ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎችን ያካተተው ...
Read More »በአሜሪካ ላስቬጋስ አንድ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ 58 ያህል ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 22/2010)በአሜሪካ ላስቬጋስ አንድ የ64 አመት ግለሰብ የሙዚቃ ትዕይንት ይከታተሉ በነበሩ ሰዎች ላይ በከፈተው የተኩስ ሩምታ 58 ያህል ሰዎች መግደሉ ተሰማ። ግለሰቡ ካረፈበት ሆቴል 32ኛ ፎቅ ላይ በመሆን ለሙዚቃ በታደሙ ሰዎች ላይ በከፈተው ሩምታ ከ5 መቶ በላይ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። ጅምላ ግድያው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1949 ወዲህ በአሜሪካ ታሪክ ከተፈጸሙ ወንጀሎች ዘግናኙ ተብሏል። ያለምንም ርህራሄ ማንዴላይ ከተባለው ሆቴል ...
Read More »የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ በብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ሊመክር ነው
(ኢሳት ዜና–መስከረም 22/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ህወሃት/ማዕከላዊ ኮሚቴ በብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር በመቀሌ ነገ መወያየት እንደሚጀምር ተገለጸ። ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብአዴን፣ደኢህዴንና ኦህዴድ በሕወሃት የተቀመጠላቸውን ድክመት እንዲያርሙ በተሰጣቸው አጀንዳዎች ላይ ግምገማ ሲያደርጉ ሕወሃት ግን በብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል። በሕወሃት ስብሰባ ላይ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ያልሆኑ የቀድሞ ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች ይሳተፋሉ ተብሏል። በእድሜና በተለያዩ ምክንያቶች ከህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰናበቱትን አንጋፋ የህወሃት አመራሮችን ...
Read More »የባህርዳር የምህንድስና ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደረገ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 22/2010) የባህርዳር የምህንድስና ተማሪዎች ዛሬ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደረገ። በዩኒቨርስቲው ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ምግብ የተከለከሉት ከ1500 በላይ ተማሪዎች ከዛሬ መስከረም 22 ጀምሮ ማንኛውንም የግቢውን ንብረት አስረክበው እንዲወጡ መደረጋቸው ታውቋል። ተማሪዎቱ በየአብያተ ክርስቲያናት የተጠለሉ ሲሆን የመንግስት ታጣቂዎች ከአንዳንድ ቤተክርስትያን ውስጥ ተማሪዎቹን እየደበደቡ ሲያስወጡ እንደነበረ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ተማሪዎቹ አራተኛ ዓመት ላይ በሚወስዱት ፈተና ውጤት አሰጣጥ ላይ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ያወጣውን ...
Read More »የእሬቻ በዓል ላይ ተሳትፈው ወደ መኖሪያቸው ሲመለሱ የነበሩ አንድ ባስ ሙሉ ታዳሚዎች በፖሊስ ተያዙ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 22/2010) በተቃውሞ ታጅቦ በተከበረው በዘንድሮው የእሬቻ በዓል ላይ ተሳትፈው ወደ መኖሪያቸው ሲመለሱ የነበሩ አንድ ባስ ሙሉ ታዳሚዎች ትላንት ቃሊቲ ላይ በፖሊስ ተይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በፖሊስ የተያዙትን ሰዎች ለማግኘት የተደረገው ሙከራም አለመሳካቱን ምንጮቹ ገልጸዋል። የሕወሃት አገዛዝ ይብቃን ከስልጣንም ይውረድ በሚል ድምጻቸውን ያሰሙት የበአሉ ተካፋዮች የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ፎቶግራፍ በመያዝና ስማቸውን ...
Read More »የእምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር በባህርዳር ስታዲየም እንዳይካሄድ ታገደ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010) በጣና ሃይቅ ላይ የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር በባህርዳር ስታዲየም እንዳይካሄድ ታገደ። ውድድሩ በጠባብ ስታዲየም እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን ወሳኔውም በኳስ ሜዳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት መሆኑም ተመልክቷል። የእምቦጭ አረም በጣና ሃይቅ ላይ ያደረሰውን ጉዳትና የደቀነውን አደጋ ለማስገንዘብና ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ለመሳተፍ የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ቡድን ...
Read More »ኤች አር 128 እንዲጸድቅ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሳይዘናጉ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 19/2010) በአሜሪካን ኮንግረስ ለውሳኔ የቀረበው ኤች አር 128 እንዲጸድቅ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሳይዘናጉ ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ። በአውሮፓና በሌሎች ክፍለ አለማት የሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን እየሰጡ መሆኑም ታውቋል። በቀጣይም በመላው አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በግፍ ለታሰሩት ጋዜጠኞች፣የፖለቲካ መሪዎችና የሃይማኖት አባቶች ተከራካሪ በመሆን በያሉባቸው ግዛቶች ለሚገኙ የምክር ቤት አባላት ቢሮአቸው በመገኘት፣በደብዳቤና በስልክ መልዕክታቸውን እንዲያደርሱ ጥሪ ቀርቧል። በዋሽንግተን ዲሲና ...
Read More »