.የኢሳት አማርኛ ዜና

አንጋፋዋ ድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን ከዚህ አለም በሞት ተለየች

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 1/2010)አንጋፋዋ ድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን ከዚህ አለም በሞት ተለየች። በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በአዲስ አመት ዜማዋ እንቁጣጣሽ ይበልጥ የምትታወቀውና ትዝታ በፖስታና ሌሎች መሰል ታዋቂ የሙዚቃ ስራዎችን ለህዝብ ያደረሰችው አንጋፋዋ ድምጻዊት ዘሪቱ ጌታሁን ባደረባት ሕመም ምክንያት ዛሬ ረቡዕ ረፋዱ ላይ በህክምና ላይ እያለች ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። ከ1949 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቲያትር፣በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ወይንም በብሔራዊ ቲያትር እንዲሁም በፖሊስ ሰራዊት ኦኬስትራ በድምጻዊነት ...

Read More »

በአፋር አርብቶ አደሮችና በትግራይ ልዩ ሃይል መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 1/2010) በአፋር አርብቶ አደሮችና በትግራይ ልዩ ሃይል መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ። የአፋር የሰብዓዊ መብት ድርጅት ለኢሳት እንዳስታወቀው በመጋሌ ወረዳ ዳንቲ በተባለ አካባቢ ከትላንት ጠዋት ጀምሮ በሁለቱ ወገኖች በጦር መሳሪያ የታገዘ ውጊያ እየተደረገ ነው። የትግራይ ልዩ ሃይል የፈጸመው ድንገተኛ ወረራ ለግጭቱ መንስዔ መሆኑን የሚገልጸው የአፋር የሰብዓዊ መብት ድርጅት በግጭቱ ከልዩ ሃይሉ ስድስት፡ ከአፋር ደግሞ ሶስት ሰዎች ...

Read More »

በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬ የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 1/2010)በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬ የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ። ሶስት ሰዎች በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸውም ታውቋል። በአምቦ፣ ሻሸመኔ፣ ነቀምት፣ አዳባ፣ ኮፈሌና በሀረርጌ የተካሄዱት ሰልፎች የስርዓት ለውጥ በሚጠይቁ መፈክሮች የታጀቡ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የጠየቀው ህዝብ የህወሀት መንግስት ከስልጣን እንዲወርድ በከፍተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መጠየቁንም ለማወቅ ተችሏል። የሻሸመኔው ተቃውሞ ከበድ ያለ፡ እንደወትሮውም የመንግስት ታጣቂዎች ጭካኔ ...

Read More »

በኬንያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ቢሮ ሰራተኞች ጉቦና የወሲብ ጥያቄ ለመደለያ ይጠይቃሉ ተባለ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 1/2010)በኬንያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ቢሮ ሰራተኞች ጉቦና የወሲብ ጥያቄ ለመደለያ ይጠይቁናል ሲሉ በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ስደተኞች አማረሩ። ስደተኞቹ እንደሚሉት ጉቦ ሳይጨመርበት የስደተኛ ማመልከቻውን ለኮሚሽኑ ያስገባ ስደተኛ ሰራተኞቹ ማንነቱን አጋልጠው ችግር ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። ዘ ስታር የተባለው የኬንያ ጋዜጣ ባወጣው ሰፊ ዘገባ የኮሚሽኑ ሰራተኞች የኢትዮጵያውያኑን የስደተኝነት ጥያቄ ለማቀላጠፍ ጉቦ እንደሚጠይቁ በተለይም ሴቶቹ የወሲብ ጥያቄ እንደሚቀርባላቸው ካለዛ ...

Read More »

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በተነሳው ሰደድ እሳት ቢያንስ 11 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በተነሳው ሰደድ እሳት ቢያንስ 11 ሰዎች ሲሞቱ ከ1500 በላይ ቤቶች ወድመዋል። ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም የመቃጠልና በጭስ የመታፈን ጉዳት የደረሰባቸው ከ100 በላይ ሰዎችም ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ብሏል ፎክስ ኒውስ በዘገባው።። በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የተነሳው ሰደድ እሳት የወይን ሀገር በመባል የሚታወቁትን የናፓ፣ሶኖማ፣ዮባና ሜንዶሲኖ አካባቢዎችን ክፉኛ መጉዳቱ ታውቋል። ከ12 በላይ ሰደድ እሳት ...

Read More »

ደኢህዴን በትግራይ ክልል ትምህርት ቤት አስገንብቶ ማስረከቡ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010) የደቡብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደኢህዴን በትግራይ ክልል ትምህርት ቤት አስገንብቶ ማስረከቡ ተሰማ። ለትምህርት ቤቱ ግንባታ 12 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉም ታውቋል። በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበርነት የሚመራው የደቡብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ንቅናቄ/ደኢህዴን የተመሰረተበት ጊዜና ቦታ በፓርቲው እራሱ ስምምነት ያለ አይመስልም። አንዴ ከደርግ ውድቀት በፊት የስምጥ ሸለቆ ንቅናቄ በሚል ደቡብ ውስጥ ተመሰረተ።ሌላ ጊዜ ደግሞ በትግራይ ክልል ተቋቋመ በሚል የተምታታ ታሪክ ነው ...

Read More »

የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መቋጫ ሳያገኝ አንድ ሳምንት እንዳለፈው ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010)ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ /ሕወሃት ለአራት ቀናት ያቀደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መቋጫ ሳያገኝ አንድ ሳምንት እንዳለፈው ተገለጸ። ሆኖም ሕወሃት ስብሰባው ተጠናቋል ሲል መግለጫ አውጥቷል። የሕወሃት ምንጮች በአደባባይ እንደጻፉት የማዕከላዊ ኮሚቴው ለመወያየት ከያዛቸው የተለያዩ አጀንዳዎች ግማሹን ያህል እንኳን ሳይወያይ አንድ ሳምንት ተቆጥሯል። በስብሰባው ቀደምት የህወሃት መሪዎች መገኘታቸው በመክፈቻው ላይ የታየ ቢሆንም በዝርዝር ውይይቱ ስለመሳተፋቸው ግን የተገለጸ ነገር የለም። ሕዝባዊ ...

Read More »

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በተቀሰቀሰው የኮሌራ በሽታ በትንሹ 10 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በተያዘው ወር በተቀሰቀሰው የኮሌራ በሽታ በትንሹ 10 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። በክልሉ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ከተማ በተቀሰቀሰው በዚሁ የኮሌራ በሽታ በከተማው የሚገኘው ጤና ጣቢያ ሌላ አገልግሎት እንዳይሰጥ መከልከሉም ታውቋል። በተለይ በአርሶአደሮች መንደር በሽታው የተስፋፋ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይነገራል። በተመሳሳይ ወረርሽኙ በድሬደዋ ከተማም መቀስቀሱንና በበሽታው 127 ሰዎች መጠቃታቸው ታውቋል። በመንግስት ...

Read More »

44 ሺ ኩንታል ስኳር ከ2 ወራት የሞያሌ ቆይታ በኋላ ለብልሽት ተዳርጎ ወደ ወንጂ ተመለሰ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010) በ110 የጭነት መኪናዎች ተጭኖ ወደ ኬንያ ሊገባ የነበረው 44 ሺ ኩንታል ስኳር ከ2 ወራት የሞያሌ ቆይታ በኋላ ለብልሽት ተዳርጎ ወደ ወንጂ በመመለስ ላይ መሆኑ ተነገረ። እስካሁን 44 የጭነት መኪናዎች ስኳሩን እንደጫኑ ናዝሬት ገብተዋል። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ስኳሩን ዱባይ ለሚገኘው አግሪ ኮሞዲቲ የተባለ ኩባንያ የሸጠው በሀገር ውስጥ ከፍተኛ የስኳር እጥረት ባለበት ሁኔታ ነው። ስኳሩን ኬንያ ለማድረስ ተዋውሎ ሞያሌ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም 15 በመቶ እንዲቀንስ ተወሰነ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010) የኢትዮጵያ ብር የመግዛት አቅም 15 በመቶ እንዲቀንስ በመወሰኑ ከነገ ጥቅምት 1/2010 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገለጸ። በዚህም አንድ የአሜሪካን ዶላር በ27 የኢትዮጵያ ብር እንደሚመነዘር ተመልክቷል። የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ መስከረም 29/2010 ሲጀምር ፕሬዝዳንቱ ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ መወሰኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም ኤክስፖርትን ለማበረታታት ታልሞ መሆኑን በንግግራቸው ቢጠቅሱም ርምጃው ግን የዋጋ ግሽበትን እንደሚያስከትል ...

Read More »