.የኢሳት አማርኛ ዜና

በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውስጥ አንዱን ብሔር ማግለልና ሌላውን ማወደስ ይታያል ተባለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010) በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውስጥ አንዱን ብሔር ማግለልና ሌላውን ማወደስ እንደሚታይ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። የቀድሞ ተማሪዎች የሚሰባሰቡት በፖለቲካና በርዕዮተ አለም አመለከታተቸው ነበር ብለዋል። በአፋር ክልል የሕወሃት አገዛዝ ኣያከበረ ያለውን “የብሔረሰቦች ቀን” በማስመልከት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በዩኒቨርስቲዎች አካባቢ እየተየ ያለውን ተቃውሞና አመጽ በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አቶ ሃይለማርያም በዩኒቨርስቲዎች አካባቢ ብሄር ተኮር ...

Read More »

የህወሃት አገዛዝ ሕዝቡን ወዳልተፈለገ ብጥብጥ እያመራው ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010) የህወሃት አገዛዝ ትዕግስተኛውንና በፈሪሃ እግዚአብሔር በተመሠረተ ጨዋነት ላይ የሚኖረውን ሕዝባችንን ወዳልተፈለገ ብጥብጥ እንዲያመራ እየገፋፋው ነው ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ። “ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም ፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም ”በሚል ርዕስ መግለጫ ያወጣው ቅዱስ ሲኖዶስ በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን እጅግ ኋላ ቀር በሆነ ፖለቲካ አገርን ለመምራት መሞክር በዘመኑ ያለመኖርን ያህል ይቆጠራል በዓለም መድረክ ፊትም ...

Read More »

አርዱፍ የህወሃትን ሰራዊት መቶ መለሰ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰራዊት የአርዱፍን ይዞታ ሰብሮ ለመግባት ያደረገው ሙከራ መክሸፉንና ተመቶ መመለሱን የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አርዱፍ አስታወቀ። መብታችን እስኪከበር በሕወሃትና በመልዕክተኛው የአፋር ልዩ ፖሊስ ሃይል ላይ የጀመርነው ውጊያ ይቀጥላል ሲልም አስታውቋል። የውጭ ሀገር ዜጎችና ጎብኚዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አርዱፍ አስጠንቅቋል። የብሔር ብሄረሰቦች በአል ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በሚል በአርዱፍ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ከአርዱፍ ተዋጊዎች ...

Read More »

የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ሊያደረግ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) የሕወሃት አገዛዝ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ሊያደርግ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ውድድሩ እንዲቆም የተፈለገው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይና በአማራ ክልል እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለም በወሎ ወልዲያ ግጭት በተካሄደ ማግስት የደሴ ከተማ ነዋሪዎች የነቀምት ከነማ ክለብ ተጫዋቾችና ደጋፊዎችን በደመቀ ስነስርአት ተቀብለዋቸዋል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በክለቦች መካከል ባሉ ...

Read More »

ሃማስ የአመጽ ጥሪ አስተላለፈ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና ነች ሲሉ እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ ሃማስ የአመጽ ጥሪ ማስተላላፉ ተሰማ። የትራምፕን ውሳኔ ተከትሎም በኢየሩሳሌም፣በራማላህና በቤተልሄም ተቃውሞ ተቀስቅሷል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢየሩሳሌም እውቅና መስጠታቸውና በቴላቪቭ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ ኢየሩሳሌም ለማዛወር መወሰናቸው ከሀገራት መሪዎችና ከእስልምናው አለም ውግዘትን አስከትሏል። እስራኤላውያንም ሆኑ ፍልስጤማውያን ኢየሩሳሌም በመዲናነት ትገባናለች ብለው ያምናሉ::ይህም ለዘመናት አጨቃጫቂ ጉዳይ ሆኖ ...

Read More »

አባ ገብረኢየሱስ በእስር ቤት ሲደበደቡ አደሩ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) የዋልድባው መነኩሴ አባ ገብረኢየሱስ ዛሬ ለሊቱን በእስር ቤት ሲደበደቡ አድረው ወደ ጭለማ ቤት መወርወራቸው ተሰማ። በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለምንም ብይን በጭለማ ቤት ታስሮ የሚገኘው አስቻለው ደሴ አባ ገብረየሱስ ስብርብር እንዲሉ ተደርገው ከተደበደቡ በኋላ በሱ ጭለማ ክፍል መጣላቸውን መስክሯል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስልጣኑን ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መታቀዱ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) ሰነድ የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ በፈቃደኝነትም ሆነ በማስገደድ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የአውሮፓ ሕብረትና የኢትዮጵያ አገዛዝ መስማማታቸውን አፈትልኮ የወጣ አንድ ሰነድ አመለከተ። በስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ስደተኞችን ከአውሮፓ ወደ ሀገራቸው በግዳጅ ለመመለስ ሙሉ ትብብር ያደርጋል። ስደተኞቹ ዜግነታቸውን የሚያረጋግጥ ፓስፖርት ባይዙ እንኳን የደህንነት መስሪያ ቤቱ ማንነታቸውን ካረጋገጠ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የጉዞ ሰነድ ...

Read More »

አቶ አባይ ወልዱን ከክልል ፕሬዝዳንትነት የማንሳት ጉዳይ ተቃውሞ ገጠመው

(ኢሳት ዜና –ሕዳር 28/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ አባይ ወልዱን ከትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትነት ለማንሳት የሚደረገው ሙከራ ተቃውሞ እንደገጠመው ምንጮች ገለጹ። ለተቃውሞ ምክንያት የሆነውም የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከልጣናቸው ሳይወርዱ አቶ አባይ ወልዱ መነሳት የለባቸውም በሚል እንደሆነም ታውቋል። በዚህ ሳቢያ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በቅድሚያ ለማውረድ በሕወሃት ጣልቃ ገብነት እንቅስቃሴ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ብአዴን ...

Read More »

በአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ የሚመራ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊላክ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 28/2010) አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ በማኔጂንግ ዳይሬክተሩ የሚመራ የልዑካን ቡድንን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ መዘጋጀቱ ታወቀ። ተቋሙ ቡድኑን ወደ ኢትዮጵያ የሚልከው በሀገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የኢኮኖሚው ሁኔታ እያሳሰበው በመምጣቱ መሆኑ ታውቋል። የሀገሪቱ ተጠባባቂ የውጭ ምንዛሪ ወደ 700 ሚሊየን ዶላር የወረደ ሲሆን በውጭ ምንዛሪ ዕጥረት በጅቡቲ የተከማቹ እቃዎችን ማንሳት እንዳልተቻለም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በወጭ ንግድ ...

Read More »

አሜሪካ ለኢየሩሳሌም እውቅና ሰጠች

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 27/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ እንድትሆን እውቅና ሰጡ ። ይህን ተከትሎም የአረብ ሀገራት መሪዎች የፕሬዝዳንት ትራምፕን ርምጃ ሲያወግዙ የካቶሊካውያኑ ሊቀጳጳስ ኢየሩሳሌም የሁሉም ነች በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ በጉዳዩ ላይ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት እንደሚያነጋግሩ አስታውቀዋል። አሜሪካ ቴል አቪቭ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ለማዛወር መወሰኗንም ሆነ ለኢየሩሳሌም ዋና ከተማ የሰጡትን እውቅና የፍልስጤማውያኑ ፕሬዝዳንት ...

Read More »