(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) ማላዊ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ 22 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲባረሩ ተወሰነ። ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ ከሀገር እንዲባረሩ የተወሰነው ጉዳያቸውን በተመለከተ የሚያግዛቸው አስተርጓሚ በመጥፋቱ እንደሆነም ተመልክቷል። በሌላ ዜና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ 5 ኢትዮጵያውያን በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን አፍሪካ ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል። ማላዊ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገብታችኋል በሚል በቁጥጥር ስር የዋሉት 22 ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የማላዊው ጋዜጣ ናይሳ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሃይለማርያም ደሳለኝ በፖሊስ ታስረው እንዲቀርቡ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በፖሊስ ታስረው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡላቸው አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤቱን ጠየቁ። አቶ ሃይለማርያም በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት በፍርድ ቤት ቢጠሩም ሕጉን አክብረው ግን አልተገኙም። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አቶ ሃይለማርያም በስራ መደራረብ ለምስክርነት መቅረብ እንዳልቻሉ ለፍርድቤቱ ደብዳቤ ፅፏል። በዚህ የክስ መዝገብ 4ኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ግን አቶ ሃይለማርያምን ...
Read More »የበይነ መረብ ዘመቻ ሊካሄድ ነው
(ኢሳት ዲሲ –ታህሳስ 17/2010) የህሊና እስረኞችን ለማስታወስ ነገ የበይነ መረብ ዘመቻ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ። በሀገር ቤት የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎችና ጋዜጠኞች በጋራ ያዘጋጁት የበይነ መረብ ዘመቻ በተለያዩ ወህኒ ቤቶች የሚገኙ የህሊና እስረኞች ስቃይ እየተባባሰ መምጣቱን ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ያለመ እንደሆነ ተመልክቷል። ለአንድ ቀን በሚደረገው በዚሁ ዘመቻ እስረኞቹ ብቻቸውን እንዳልሆኑ ለማሳየት መሆኑም ተገልጿል። በማህበራዊ መድረኮች በፌስ ቡክና ቲውተር ዘመቻው እንደሚካሄድም ...
Read More »አዲስአበባ ዩኒቨርስቲ እየተጠበቀ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል የአገዛዙ የደህንነት ሃይሎች ግቢውን በአይነቁራኛ እየተከታተሉ መሆናቸው ተነገረ። በዩኒቨርስቲው ትላንት ተቃውሞ ለመጀመር ተማሪዎች ቀጠሮ ይዘው እንደነበር ይነገራል። የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ሊመሩ ይችላሉ የተባሉ ተማሪዎች በጥርጣሬ ብቻ እየታፈኑ በፒካፕ ተሽከርካሪ ወደ ማጎሪያ ቦታ መወሰዳቸው ተነግሯል። ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲቪል የለበሱ በርካታ ፖሊሶች መግባታቸውንም የኢሳት ምንጮች አረጋግጠዋል። የሕወሃት አገዛዝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ...
Read More »የፓርላማ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 17/2010) በኢትዮጵያ በተፈጠረው ቀውስ ላይ ማብራሪያ ካልተሰጠን በመደበኛ ስብሰባ አንገኝም ያሉት የፓርላማ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ። በዝግ ለ3 ሰአታት በተካሄደው በዚሁ ስብሰባ 4ቱ የኦሮሚያ፣የአማራ፣የትግራይና የደቡብ ፕሬዝዳንቶች ከአቶ ሃይለማርያም ጋር መገናኘታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአሜሪካ የሚገኘውን አይጋ ፎረም የሕወሃት ድረ ገጽ ጠቅሶ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ከፓርላማ አባላቱ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከተጠየቁ በኋላ ምላሽ ሳይሰጡ ሲያቅማሙ መቆየታቸው ታውቋል። በስተመጨረሻ ...
Read More »በዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ሙሉ በሙሉ ትምህርት ማቆሙ ተገለጸ። በአዳማ ዩኒቨርስቲ ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ ትምህርት ተቋርጧል። በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ባለፈው ዓርብ በተነሳው ተቃውሞ የህንጻዎች መስታወት መሰባበሩንም ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ በትግራይ ልዩ ሃይልና በአማራ ልዩ ሃይል መሃል ቅዳሜ ዕለት የትኩስ ልውውጥ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። በአሶሳ ዩኒቨርስቲም ተቃውሞ ተጀምሯል። በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የታሰሩ ተማሪዎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ታውቋል። ከ10ቀናት ...
Read More »የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ ሲደረግ ዋለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ ሲደረግ መዋሉ ተሰማ። በባህርዳር መውጪያና መግቢያ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ጥብቅ ፍተሻ በመደረግ ላይ መሆኑ ታወቋል። በእንጅባራ ውጥረት መኖሩ እየተነገረ ነው። በአምቦ መስመር ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ በመደረግ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አንዳንድ ከተሞች ተመሳሳይ አድማ ተጀምሯል። በኢሉባቡር ጎሬና በወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ሻምቡ ተቃውሞ በመካሄድ ...
Read More »የፈረንጆቹ ገና ተከበረ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) የፈረንጆቹ የገና በአል በበርካታ የአለም ክፍሎች በደማቅ ስነስርአት ተከብሮ ዋለ። የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ፓፕ ፍራንሲስ በበአሉ ዋዜማ ባስተላለፉት መልዕክት አለም ስደተኞችን እንድታስተናግድ የክርስትና እምነት ግድ ይላል ብለዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ቤተልሄም እየተካሄደ ያለው ግጭት በአሉን ጥላ ያጠላበት መሆኑንም መረጃዎች አመልክተዋል። የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ትላንት በዋዜማው በፈረንጆቹ ገና ዋዜማ ባስተላለፉት መልዕክታቸው በአውሮፓ ለአክራሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያለው ድጋፍ ...
Read More »ቀለብ ስዮም ተፈታች
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አመራር ቀለብ ስዮም ከእስር ተፈታች። ሀምሌ 2 ቀን 2007 ወደ እስር ቤት ተወርውራ የነበረችው ቀለብ ስዩም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈባትን ውሳኔ በመቃወም ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረበችው ይግባኝ መሠረት 4 ዓመት በእስር እንድትቆይ ተላልፎ የነበረው የእስር ቅጣት ተቀንሶ ወደ ሶስት ዓመት ከሶስት ወር ወርዶ ነበር። በዚሁ መሰረት ቀለብ ስዩም የእስር ጊዜዋን ጨርሳ ዛሬ ...
Read More »አቶ በቀለ ገርባ በጽኑ ታመሙ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በጽኑ መታመማቸው ተነገረ። የእስር ቤት ባለስልጣናትም አቶ በቀለ ገርባ ሕክምና ወደሚያገኙበት ሆስፒታል እንዳይሄዱ ማገዳቸውንም ለማወቅ ተችሏል። አቶ በቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ቢኖራቸውም መራመድ ባለመቻላቸው የፍርድ ሂደቱ ተስተጓጉሏል ተብሏል። ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባ ክሳቸው ከሽብር ወንጀል ሕገመንግስትን በሃይል ለማፍረስ በመምከር ወደሚል ቢቀየርላቸውም እስካሁን የዋስ ...
Read More »