(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በኢራን እየተካሄደ ያለውን ጸረ መንግስት ተቃውሞ የሀገሪቱ መንፈሳዊ መሪ በኢራን ጠላቶች የተቆሰቆሰ ነው ሲሉ ወነጀሉ። መንፈሳዊ መሪው አያቶላ አሊ ካሚኒ ባለፈው ሐሙስ ተቃውሞ ከተነሳ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ንግግር ጠላቶች ያሏቸውን አካላት በግልጽ አልተናገሩም። በኢራን እየተካሄደ ባለው ጸረ አገዛዝ ተቃውሞ ተጨማሪ ሕይወት መጥፋቱን መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው። መንፈሳዊ መሪው ኦፊሴላዊ በሆነው ድረገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት የተቃውሞው ጠንሳሾች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ተከሳሾች ዳኞችን በችሎት ላይ መናገራቸው ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በግንቦት 7 ስም በሽብር ወንጀል ተከሰው በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተከሳሾች ከሳሞራና አባይ ጸሃዬ በላይ ተጠያቂ ናችሁ ሲሉ ዳኞቹን በችሎት ላይ መናገራቸው ታወቀ። ፍርድ ቤቱም በተከሳሾቹ ላይ እስከ 16 አመታት የሚዘልቅ እስራት የወሰነ ሲሆን ተከሳሾቹም ለሀገራችን ስንል የምንከፍለው ዋጋ ነው ሲሉ በድርጊታቸው እንደሚኮሩ ገልጸዋል። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ችሎት የቀረቡትና ...
Read More »ከተድባበ ማርያም ገዳም ጽላት ተሰረቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በአማራ ሳይንት ከሚገኘው ተድባበ ማርያም ገዳም ጽላት መሰረቁን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በዚህም የአካባቢው ምዕመናን የተቃውሞ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ መሆናቸው ታውቋል። በሌላም በኩል በምዕመናን ተቃውሞ ሲቀርብባቸው የቆየው የአዲስ አበባው ሳህሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደብደበው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል። በደቡብ ወሎ አማራ ሳይንት ወረዳ የሚገኘው የጥንታዊው የተድባበ ማርያም ገዳም በስሩ ከሚገኙት 12 አብያተክርስቲያናት የአንደኛው የመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ጽላት መሰረቁ ...
Read More »ባሻምቡ ወለጋ ተቃውሞ ተካሄደ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል በመንግስት ላይ የተጀመረው ተቃውሞ አሁንም መቀጠሉ ተገለጸ። ዛሬ ባሻምቡ ወለጋ በኦሮምኛና በአማርኛ የተጻፉ መፈክሮችን ይዘው አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ አንድ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የኦሮሚያ ክልል መሪዎች ወደ ባህርዳር ያደረጉት ጉዞና የሁለቱን ክልሎች ትብብር መርህ አልባ ሲል ማውገዙ ይታወሳል። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ትብብሩን ባጣጣለ ...
Read More »ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 24/2010) በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ ዋለ። በኢንጪኒ አደአበርጋ ህዝብ አደባባይ በመውጣት የህወሀትን ስርዓት አውግዟል። በአዳማ ዩኒቨርስቲ 18 ተማሪዎች ተባረዋል። የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል። በምስራቅ ወለጋ በገሊላ የአጋዚ ወታደሮችና ህዝቡ ፍጥጫ ውስጥ እንዳሉም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል ትላንት በወልዲያ ተቀስቅሶ የነበረውን የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ በአካባቢው ተጨማሪ ሃይል መግባቱን ለማወቅ ተችሏል። ዛሬ ...
Read More »በቡኖ በደሌ የማፈናቀል ዘመቻ በመካሄድ ላይ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 14/2010) በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ገቺና ዲዴሳ ወረዳዎች በህወሀት መንግስት የተቀነባበረ የማፈናቀል ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ። ከደርግ መንግስት የስልጣን ዘመን ጀምሮ በአካባቢው የሰፈሩና በአብዛኛው ከአማራ የመጡ ኢትዮጵያውያን ሆን ተብሎ ለዘመናት ከሚኖሩበት ቦታ እንዲለቁ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በሌላ በኩል ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በምዕራብ ሀረርጌ ዳሮ ለቡ ወረዳ የሶማሌ ልዩ ሃይልና የአጋዚ ሰራዊት በጋራ ህዝቡን እያሸበሩት ...
Read More »በኢራን 12 ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2010) በኢራን እያሻቀበ ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቃወምና አገዛዙን ለማውገዝ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት ርምጃ እስካሁን 12 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የጀመረው ይህ ተቃውሞ ከአውሮፓውያኑ 2009 ወዲህ የተካሄደ ትልቁ ጸረ-አገዛዝ ተቃውሞ ነው ተብሏል። እየተባባሰ ያለውን የኑሮ ውድነትና የኢኮኖሚ ድቀት በመቃወም የተጀመረው ተቃውሞ ወደ አጠቃላይ ጸረ-መንግስት ትዕይንተ ሕዝብ እየተቀየረ መሆኑን የምዕራቡ አለም መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ...
Read More »ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2010) በሊቢያ ከ400 በላይ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ። አማጽያኑ በሚቆጣጠሩት ግዛት በስደት የገቡ ኢትዮጵያውያን በአንድ መጋዘን ውስጥ ታጭቀው በስቃይ ውስጥ እንደሚገኙም ታውቋል። በቅርቡ ብቻ 5 ኢትዮጵያውያን በድብደባና በበሽታ መሞታቸውንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግስት እንዲደርስልን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ምላሽ አላገኘንም ሲሉ በችግር ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ለኢሳት ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ወገን ይድረስልን ሲሉም ጥሪ አድርገዋል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሊቢያ የገቡት ...
Read More »የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ አልተመለሱም
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2010) በዩኒቨርስቲዎች በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ወደቤታቸው የሄዱ ተማሪዎች ጥሪ ቢደረግላቸውም መመለስ እንዳልቻሉ የመንግስት ሪፖርት አመለከተ። ሪፖርቱ እንዳመለከተው በዩኒቨርቲዎች ውስጥ ያለው ፖለቲካዊ ቀውስ ከባድ ደረጃ ላይ ይገኛል። እናም ችግሩ መፍትሄ ካላገኘ የባሰ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ሪፖርቱ ይገልጻል። በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ግጭት ተቀስቅሶ በነበረባቸው 19 ዩኒቨርስቲዎች በመዟዟር ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የመንግስት ግብረሃይል ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። የገብረ ሃይሉ አካል ...
Read More »በአምቦ ዘረፋና ድብደባ ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2010) የኦሮሚያ ክልል ፖሊስን የደንብ ልብስ በመዝረፍ በአምቦ ከተማ ዘረፋና ድብደባ ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውን የአምቦ ከተማ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃንም የግለሰቦቹን መያዝ በዘገባቸው ላይ አስፍረዋል። በሌላ በኩል የወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት ሶስቱም ዘራፊዎች የትግራይ ክልል ተወላጆች ሲሆኑ ስማቸውም ይፋ ሆኗል። አንዳንድ የፓለቲካ ተንታኞች እንደሚገምቱት ድርጊቱ ከተራ ዘረፋነቱ ይልቅ በሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት የተቀነባበረ ...
Read More »