.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢኮኖሚ ቀውሱ የህወሃትን አገዛዝ ለተፋጠነ ውድቀት ሊዳርገው ይችላል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2010) በኢትዮጵያ የተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ የህወሃትን አገዛዝ ለተፋጠነ ውድቀት ሊዳርገው እንደሚችል ተገለጸ። ኢሳት ያነጋገራቸው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚሉት የፖለቲካ አለመረጋጋት እየናጠው ያለው አገዛዝ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ መግባቱ ውድቀቱን እያፋጠነው ነው። ሀገሪቱ የገጠማት የኢኮኖሚ አደጋ አሁን በስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ አቅም የሚፈታ ባለመሆኑ ህዝባዊ አመጾች ሚነሱበት እድል ሰፊ ነው ሲሉ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። የአገዛዙ ደጋፊ መገናኛ ብዙሃንም የኢኮኖሚ ቀውሱን በመጥቀስ ከፍተኛ ...

Read More »

የሕወሃት አገዛዝ በማናቸውም ጥገናዊ ለውጥ ሊነሳ የማይችል ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ መንግስት ከእንግዲህ በማናቸውም ጥገናዊ ለውጥ ሊነሳ የማይችል ያበቃለት ቡድን መሆኑን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ገለጹ። አዲስአበባ ድረስ ታንክና መድፍ ይዘን የገባነው ለሁለቱ ህዝቦች ዘላቂ ጥቅም ስንል ነበር ሲሉም ተደምጠዋል። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት በኤርትራ ቴሌቪዥን በተላለፈው ቃለ ምልልሳቸው የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ በህወሃት አደፍራሽነት 25 አመታት የገጠማቸውን ኪሳራ የሚያስመልሱበት ግዜ ሩቅ እንዳልሆነም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ...

Read More »

የ528 ሰዎች ክስ ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2010) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የፖለቲካ እስረኞችን እፈታለሁ ያለው የሕወሃት አገዛዝ የ528 ሰዎችን ክስ ማቋረጡን ገለጸ። ከነዚሁ መካከል 413 ክሶች የተቋረጡት ከደቡብ ክልል በጌዲዮና ኮንሶ ዞኖች ሲሆን ቀሪዎቹ 115ቱ ደግሞ ከፌደራል ናቸው። ከሌሎቹም ክልሎች ጉዳያቸው ተጣርቶ ሲመጣ ክሳቸው ተቋርጦ የሚለቀቁ እንደሚኖሩ ተገልጿል። የፌደራል ዋና አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከእስር ክሳቸው ተቋርጦ የሚለቀቁት ...

Read More »

አቶ አዲሱ ለገሰ ሕዝብን የመከፋፈል ሴራቸውን ቀጥለዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 4/2010) አቶ አዲሱ ለገሰ በቅማንት ጉዳይ ላይ የጀመሩትን ሕዝብን የመከፋፈል ሴራ መቀጠላቸው ተነገረ ። የሕወሃትን ጉዳይ በማስፈጸም የሚታወቁት አቶ አዲሱ ለገሰ በጎንደር በተገኙበት ስብሰባ በብአዴን አባላት ሳይቀር ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ሕዝቡም ቁጣውን በመግለፅ አቶ አዲሱ የተገኙበትን ስብሰባ ረግጦ ወጥቷል ፡፡ አቶ አዲሱ ለገሰ ጥር 2/2010 ምሽት በነበረው በረራ ጎንደር በመግባት “የቅማንት ኮሚቴ ” ነን በማለት በህወሃት የተቋቋሙ ግለሰቦችን ...

Read More »

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተቃውሞ ገጠማቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 4/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ፣ የሃይቲና የኤልሳልቫዶር ሀገራትን በማንቋሸሽ መናገራቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ቀሰቀሰ። ትራምፕ ከአፍሪካ የመወሰኛ ምክር ቤት አባላትና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ሀገራቱን ቆሻሻ ወይንም ውዳቂ ሲሉ መጥራታቸው በሲ ኤን ኤን ከተዘገበ በኋላ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ተቀባብለውታል። የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የቀድሞው የሃይቲ ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ታሪክ ያልታየ ድንቁርና ሲሉ ትራምፕን አውግዘዋል። የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ...

Read More »

የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ለህወሃት አስደንጋጭ ሆኗል ተባለ  

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 4/2010) ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦን በተመለከተ በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ ይፋዊ ምላሽ መስጠቱ ሁኔታው ያስደነገጠው መሆኑን እንደሚያሳይ የዘመቻው አስተባባሪ ገለጸ። አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የውጭ ምንዛሪ እቀባ ዘመቻው ዋነኛ አላማ የሕወሃትን አገዛዝ በማዳከም የኢኮኖሚና የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ መክተት ነው። የአገዛዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የውጭ ...

Read More »

የተበላሸው ብድር 3.6 ቢሊየን ብር ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 4/2010) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰፋፊ እርሻዎች ካበደረው 5.6 ቢሊየን ብር ውስጥ 3.6 ቢሊየን ብር የተበላሸ ብድር ሆኗል ሲል አረጋገጠ። ልማት ባንኩ ለሰፋፊ እርሻዎች መቀበል የጀመረውን የብድር ጥያቄም ማቆሙን አስታውቋል። በአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች ለተሰማሩበት የጋምቤላ የእርሻ ልማት የተሰጠው ብድር ከ63 በመቶ በላይ የተበላሸ ተብሎ የተሰረዘው ባለሀብቶቹ ተጠያቂ እንዳይሆኑ በሚል መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ይገልጻሉ። የኦክላንድ የምርምር ተቋም በጋምቤላ ...

Read More »

4 የህግ ታራሚዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 4/2010) በሲዳማ ዞን ይርጋለም ከተማ 4 የህግ ታራሚዎች በፖሊስ በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገለጸ። ፖሊስ ሊያመልጡ ሲሉ ነው የተገደሉት ይላል። የሲዳማ ሀርነት ንቅናቄ በግፍ ተገድለዋል ሲል ለኢሳት ገልጿል። የሲዳማ ወጣቶች መብታቸውን በመጠየቃቸው በጅምላ እየታፈሱ መሆኑም ተገልጿል። በሌላ በኩል በሲዳማና በወላይታ ወሰን ላይ ግጭት ለመፍጠር በህወሃት አገዛዝ የሚደረገውን ቅስቀሳ ህዝቡ እንዲያከሽፈው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ጥሪ አድርጓል። ግድያው የተፈጸመው ታህሳስ 30 ...

Read More »

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የ45 ሰዎች ሕይወት አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ርዕሰ መዲና ኪንሻሳ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ45 ሰዎች ሕይወት አለፈ። በአደጋው ከሞቱት ውስጥ አምስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸው ታውቋል። ከአፍሪካ ከተሞች በሕዝብ ብዛት በሶስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘውና 12 ሚሊየን ያህል ሕዝብ የሚኖርባት የኮንጎዋ ርዕሰ መዲና ኪንሻሳ ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ የሆኑት ለ5 ቀናት ያህል ሳያቋርጥ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እንደሆነም ታውቋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ...

Read More »

የውጭ ጉዲፈቻ ታገደ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 3/2010) ኢትዮጵያ ሕጻናትን በጉዲፈቻ ወደ ውጭ ለመውሰድ የሚፈቅደውን ሕግ በፓርላማ በኩል አገደች። ሕጉ የታገደው በጉዲፈቻ ስም በውጭ ዜጎች ከኢትዮጵያ የሚወሰዱ ሕጻናት ለበርካታ ጊዜያት በአሳዳጊዎቻቸው ከፍተኛ በደል እንደሚደርስባቸው በመታወቁ ነው ተብሏል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በጉዲፈቻ መልክ ከኢትዮጵያ የሚወሰዱ ሕጻናት ብዙዎቹ ደብዛቸው ሲጠፋ አንዳንዶቹ ደግሞ እስከመገደል ደርሰዋል። ሕጻናትን በጉዲፈቻ ለማሳደግ በሚል ከኢትዮጵያ በርካታ ልጆች ከሀገር እንዲወጡ ተደርጓል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1999 ...

Read More »