.የኢሳት አማርኛ ዜና

በወልዲያ ተቃውሞ ዳግም ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010) የወልዲያው ተቃውሞ ዳግም ተቀሰቀሰ። መሀል ወልዲያ ዛሬ ጠዋት ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ሲደረግና የመንግስት ተቋማት ላይ ጥቃት ሲሰነዘር እንደነበርም ለማወቅ ተችሏል። ከቀትር በኋላ በቤት ውስጥ የመቀመጥ የስራ ማቆም አድማ የተመታ ሲሆን ወልዲያ ሁሉ ነገር ከእንቅስቃሴ ውጭ ሆኖ እንደዋለም ታዉቋል። ህዝባዊ አመጹ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው። የመርሳ ከተማ አስተዳዳሪ መገደላቸውም ታውቋል። በሲሪንቃ በርካታ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። መንገዶች ተዘግተዋል። የትራንስፖርት አገልግሎት ...

Read More »

የአቶ ካሳ ተክለብርሃን የቴሌ ኮንፈረስ ውይይት በሕዝብ ተቃውሞ ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010) በሕወሃት አገዛዝ በቅርቡ በአሜሪካ የኢሕአዴግ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አቶ ካሳ ተክለብርሃን በቴሌ ኮንፈረስ ሲያካሂዱት የነበረው ውይይት በሕዝብ ተቃውሞ ተቋረጠ። በአሜሪካ ከ11 ከተሞች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ተመርጠው ከአምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ጋር በስልክ ኮንፈረንስ ለመወያየት ታቅዶ ራሳቸውን ካስተዋወቁ በኋላ በጥያቄና መልስ ጊዜው ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። አቶ ካሳ ስለህዳሴና ልማት እንዲሁም ኢትዮጵያን ለውጠናል ሲሉ የስልክ ውይይት ተሳታፊዎቹ ግን መጀመሪያ ሕዝብን መግደል ...

Read More »

በአዲስ አበባ መንደሮች ሊፈርሱ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010) በአዲስ አበባ አምስት ነባር መንደሮች ሊፈርሱ ነው። ነባሮቹን መንደሮች ለማፍረስ ደግሞ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ታውቋል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲህ አይነቱ ስትራቴጂ የሕወሃት አገዛዝ አብሮ የኖረውን ሕዝብ በመበታተን ራሱ የሚፈልጋቸውን ሰዎች ለማስፈር በየጊዜው የሚነድፈው እኩይ እቅድ ነው ሲሉ እቅዱን አውግዘዋል። ሕብረተሰቡም እንዲህ አይነቱን እኩይ ተግባር በጋራ በመሆን ማስቆም ይገባዋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በቅርቡ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ...

Read More »

ዶክተር መረራ ጉዲና ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 21/2010)   በቅርቡ ከወህኒ የወጡት ዶክተር መረራ ጉዲና በአምቦና በጊንጪ ከተሞች ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው። በተለይ በአምቦ ስታዲየም በተካሄደው የአቀባበል ስለስርአት በመቶ ሺ የሚቆጠር ሕዝብ እንደታደመም ለማወቅ ተችሏል። ወደ አምቦ ባደረጉት ጉዞ በሌሎች የምዕራብ ሸዋ ከተሞች በተለይም በጊንጪ ከፍተኛ አቀባበል የጠበቃቸውና በአምቦ ስታዲየም የጀግና አቀባበል የተደረገላቸው ዶክተር መረራ ጉዲና ለሕዝቡ በተለይም ለወጣቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ትግሉ እንደሚቀጥል ቃል የገቡት ዶክተር ...

Read More »

በአንድ ሆስፒታል በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በትንሹ 37 ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) በደቡብ ኮሪያ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በትንሹ የ37 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካታ ሰዎች ቆሰሉ። ከደረሰው አደጋ ጋር በተያያዘ የሆስፒታሉ ባለቤትና ስራ አስኪያጁ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከሕሙማኑ በተጨማሪ የሕክምና ባለሙያዎችም በአደጋው ሕይወታቸው አልፏል። ከደቡብ ኮሪያ ርዕሰ መዲና ሴኡል በ270 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሚሪያንግ ከተማ በሚገኘው ሲአንግ ሆስፒታል ትላንት ምሽት የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ ባይታወቅም ...

Read More »

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ለእስረኛ የተመደበውን ብር መከፋፈላቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) ከማረሚያ ቤት ለሚለቀቁ ታሳሪዎች የመጓጓዣና ሌሎች ወጪዎች የተመደበውን 78 ሺ ያህል ብር የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሀላፊዎች እንደተከፋፈሉት ከማረሚያ ቤት የተገኘው መረጃ አመለከተ። በፌደራል ደረጃ ይፈታሉ ተብሎ ስማቸው ከተዘረዘረው 115 እስረኞች ውስጥ አሁንም ማረሚያ ቤት የሚገኙት ታሳሪዎች ቁጥር ስድስት መድረሱ ታውቋል። ከሳምንታት በፊት ክሳቸው ተቋርጦ ይለቀቃሉ ከተባሉት የፌደራል እስረኞች መካከል 115 ያህሉ ተለቀዋል ቢባልም የተወሰኑት እስካሁን በእስር ላይ ...

Read More »

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) ነባር አመራሮችን ጨምሮ የድርጅቱን ሕልውና እየገመገመ ያለው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በተንጠባጠበ ሁኔታ ሲካሄድ ቆይቶ መቋረጡ ታወቀ። በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው 22 አባላት ሕወሃት ባስቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት በጥልቅ ተሃድሶው አፈጻጸም ላይ ውይይት ቢጀምሩም በወልዲያና በቆቦ የተፈጸመው ጅምላ ግድያ በመካከላቸው መከፋፈልን ፈጥሯል። የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በአቶ አዲሱ ለገሰና በአቶ በረከት ስምኦን አቅጣጫ ሰጭነት ለክልልና ለተወካዮች ምክር ቤት የማሟያ ምርጫ ...

Read More »

በኢትዮጵያውያን ላይ የቀጠለውን ግድያ የሃይማኖት ተቋማት አወገዙ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010)   በወልዲያና በቆቦ በኢትዮጵያውያን ላይ የቀጠለውን ግድያ በማውገዝ የሃይማኖት ተቋማት መግለጫ አወጡ። በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየአብያተክርስቲያናቱ ለሟቾች ጸሎተ ፍትሃት እንዲደረግ ወስኗል። ለመከላከያ ሰራዊቱም ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የወሎ ሕዝብ እየከፈለ ላለው መሽዋዕትነት አክብሮቱን ገልጿል። አለም አቀፍ የክርስቲያን ኢትዮጵያውያን እህቶች ህብረትም ንጹሃንን የገደሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ሲል ባወጣው መግለጫ ...

Read More »

የቃና ዘገሊላ በአል ላይ የመከላከያ ሰራዊት እንዳይገኝ ከስምምነት ተደርሶ ነበር

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) በወልዲያ የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በአል ላይ የመከላከያ ሰራዊት እንዳይገኝ ከተስማማን በኋላ ሰራዊቱ በበአሉ ስፍራ መገኘቱ ለግጭቱ መከሰት ምክንያት መሆኑን ብጹእ አቡነ ኤርሚያስ ገለጹ። ሆን ተብሎ የታቀደ ይመስላል ሲሉም ሲሉም ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል። የሰሜን ወሎና ከሚሴ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ኤርሚያስ ከግድያው ባሻገር ለንብረት ውድመቱም ምክንያት የሆነው የመከላከያ ሰራዊቱ መግባት እንደሆነ መናገራቸውን ሃራ ተዋህዶ ዘግቧል። ...

Read More »

በቆቦ ህዝባዊ አመጹ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 18/2010) በሰሜን ወሎ ቆቦ የተጀመረው ህዝባዊ አመጽ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉ ተገለጸ። የአጋዚ ወታደሮች ከተማዋን በማጥለቅለቅ ህዝቡ ላይ ጥቃቱን አጠናክረው ቀጥለዋል። የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ወድመዋል። ዛሬም በቆቦ ሰማይ ሄሊኮፕተር ሲመላለስ እንደነበር ነዋሪዎች ይናገራሉ። በሆስፒታል አድራሻቸው ያልታወቀ አስከሬኖች እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል። በቆቦ አቅራቢያ በምትገኘው ሮቢትም የህዝብ አመጽ መነሳቱ ታውቋል። የመከላከያ ሰራዊትን ግስጋሴ ለመግታት መንገዶች ተዘግተዋል። ህዝቡ በመንግስት ተቋማትና በአገዛዙ ደጋፊና ...

Read More »