.የኢሳት አማርኛ ዜና

  የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ 17 እስረኞችን አስለቀቀ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 29/2010)   የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በሰሜን ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኚት ከተማ በሚገኘው እስር ቤት ላይ ባደረሰው ጥቃት 17 እስረኞችን ማስለቀቁን ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታወቀ። አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ መገለጫ እንደሚያመልከተው ዘመቻ ነጻ ትውልድ በሚል መጠሪያ ማክሰኝት እስር ቤት ላይ በተፈጸመጥቃት ነው 17 እስረኞች ነጻ የወጡት። ትላንት ለሌት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር 9 ሰአት ላይ ፈጸምኩት ባለው ...

Read More »

በፈረንሳዩ የሽብር ድርጊት ተሳታፊ የነበረው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ

 (ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) በፈረንሳይ ፓሪስ ለ130 ሰዎች ዕልቂት ምክንያት በሆነው የሽብር ድርጊት ተሳታፊ የነበረው ተጠርጣሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረበ። ለዳኞቹ ምንም የምላችሁ ነገር የለም ዝምታዬ ለኔ የመከላከያ ማስረጃዬ ነው ማለቱም ተመልክቷል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ህዳር 13/2015 በፈረንሳይ ፓሪስ የሙዚቃ ዝግጅት በሚካሄድበት አዳራሽ፣በስታዲየምና በሆቴል ላይ በተሰነዘረው ተከታታይ የሽብር ጥቃት ለ130 ሰዎች ማለቅና በመቶዎች ለሚቆጠሩ መቁሰል ተጠያቂ ከነበሩት ተጠርጣሪ አሸባሪዎች አንዱ ...

Read More »

የኦፌኮ አመራሮች ለ2ተኛ ጊዜ ተፈረደባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ አራቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ አመራሮች ለ2ተኛ ጊዜ ተፈረደባቸው። ተከሳሾቹ በድጋሚ የ6 ወራት እስራት የተፈረደባቸው በችሎት ውስጥ በዳኛው ከመቀመጫቸው እንዲነሱ ታዘው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ተብሏል። ጠበቆቻቸው ግን እኛ ከተነሳን ተከሳሾች እንዲነሱ አይገደዱም ነበር ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመውታል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ ያሉትን ተከሳሾች አቶ ...

Read More »

የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎትን ለማዳረስ የተመደበው 445 ሚሊየን ብር በሕወሃት ተዘረፈ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2018) በአማራ ክልል በዚህ ዓመት የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎትን ከ10 በላይ ለሚሆኑ ከተሞችና ቀበሌዎች ለማዳረስ በሚል የተመደበው 445 ሚሊየን ብር በሕወሃት በመዘረፉ አገልግሎቱን ማግኘት እንደማይችሉ ተገለፀ ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ከሕዝብ በተለያዩ መንገዶች ማለትም ከአገልግሎት ፥ ከአዲስ መስመር ዝርጋታ ጥያቄዎች ፥ ከቅጣትና ከልዩ ልዩ ገቢዎች የሰበሰበው 445 ሚሊዮን ብር ለትግራይ ክልል መሰጠቱ ታውቋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሰሜን ...

Read More »

በኢትዮ ሳት ሳተላይት የግልም ሆነ የመንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በግዳጅ እንዲሰራጩ የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት አጣ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) የኢትዮጵያው አገዛዝ በሚቆጣጠረው ኢትዮ ሳት ሳተላይት የግልም ሆነ የመንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በግዳጅ እንዲሰራጩ በብሮድካስት ባለስልጣን የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት ማጣቱ ተገለጸ። በተለይ የኦሮሚያና የአማራ መገናኛ ብዙሃን በዚህ ሳተላይት በኩል እንዲሰራጩ የተደረገው ሙከራ ክልሎቹ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሊሳካ አልቻለም። “ኢትዮ ሳት” በኢንሳ በኩል ቁጥጥር የሚደረግበትና ከፈረንሳይ ኩባንያ አገዛዙ በውድ ዋጋ የተከራየው ሳተላይት ነው። በሳተላይቱ ከ35 በላይ ቻናሎች ሊሰራጩበት እንደሚችልም ነው ...

Read More »

የተሰጠው ወታደራዊ ማዕረግ በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ብሶትና ምሬት ለማዳፈን ያለመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) ለ61 ወታደራዊ መኮንኖች የተሰጠው ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ብሶትና ምሬት ለማዳፈን ያለመ ነው ተባለ። ኢሳት ያነጋገራቸው ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሙያዎች እንደገለጹት ያለዕውቀትና የውጊያ ልምድ በብሄር ኮታ የታደለው ወታደራዊ ማዕረግ የሃገሪቱን ኢኮኖሚም ሆነ የመከላከያ ሰራዊት አቅምን ከግምት ያላስገባ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው። ባለፈው ዓርብ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ህወሃት የሚመራው መንግስት 4 የሙሉ ጄነራል፣ የ3ሌተናል ጄነራል፣ ...

Read More »

ኦህዴድ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ኦሕዴድን ከሚወክሉ 45 አባላት አስሩን አባረረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 28/2010) የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ውስጥ ኦህዴድን ከሚወክሉ 45 አባላት አስሩን ማባረሩ ታወቀ። ማዕከላዊ ኮሚቴው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በመንግስት የተነፈጋቸውን ጥቅማ ጥቅም ኦህዴድ እንደሚያሟላም ቃል ገብቷል። በውጭ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከተቃዋሚዎች ጋር ጭምር ተባብሮ ለመስራትም ውሳኔ ማሳለፉ ተመልክቷል። በአዳማ በመካሄድ ላይ ያለው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ቀጥሏል። በግል ተወዳድረው የፓርላማ ...

Read More »

በኤርትራውያንና በአፍጋኒስታውያን መካከል በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ቆሰሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 25/2010) በፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካሌይ በኤርትራውያንና በአፍጋኒስታውያን መካከል በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ታወቀ። የጦር መሳሪያ ድንጋይና የብረት ዱላ በጨመረውና ትላንት በተከሰተው በዚህ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች መጎዳታቸው የተገለጸ ሲሆን ቢያንስ አራቱ በጥይት መቁሰላቸውም ተመልክቷል። ግጭቱ ከአካባቢው የፖሊስ ሃይል በላይ በመሆኑ ተጨማሪ የፈረንሳይ የፖሊስ ሃይል ወደ አካባቢው መሰማራቱም ታውቋል። በፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካሌይ ትላንት የተከሰተው ግጭት መነሻ በትክክል ...

Read More »

ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከስልጣን መባረራቸውን ያወቁት በጥበቃ ሰራተኛ ሲታገዱ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2010) በቅርቡ ከሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የተባረሩትና ከኤፈርት ሃላፊነታቸው የተነሱት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከስልጣን መባረራቸውን ያወቁት ወደ ቢሮአቸው እንዳይገቡ በጥበቃ ሰራተኛ ሲታገዱ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በአቶ ስብሃት የሚደገፈው የሕወሃት አመራር ለወይዘሮ አዜብ ደብዳቤ ሳይደርሳቸው ትዕዛዙን ለጥበቃ ሰራተኛው አስቀድሞ ያስተላለፈው ሞራላቸውን ለመንካት እንደሆነም ምንጮቹ ይናገራሉ። ወይዘሮ አዜብ ተሽከርካሪያቸውንም ጭምር ድንገት ተነጥቀው በሰው መኪና ወደ ቤታቸው መመለሳቸውም ታውቋል። ...

Read More »

የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በአጋዚ ወታደር ተደበደበች

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 25/2010) በአዳማ ዩኒቨርስቲ አንዲት የ4ኛ አመት የስነ ሕይወት ሳይንስ ተማሪ የመኝታ ክፍሏ ተሰብሮ በአንድ የአጋዚ ወታደር መደብደቧንና ጾታዊ ትንኮሳ እንደደረሰባት ዘገባዎች አረጋገጡ። በዩኒቨርስቲው የሚገኙ ሴት ተማሪዎች በመከላከያ ወታደሮች በሃይል ተገደው እንደሚሳሙም በተቋሙ ጉዳዩን ያጣሩት አካላት አረጋግጠዋል። በአዳማ ዩኒቨርስቲ የጾታ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሃና ተፈራ ጉዳዩን አጣርተው ለቦርድ በማቅረባቸው በአንድ የመከላከያ ጄኔራል ትዕዛዝ ከስራ ተባረዋል። በአዳማ ዩኒቨርስቲ በአጋዚ ወታደር በመደብደብ ...

Read More »