(ኢሳት ደሲ–የካቲት 6/2010) የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርና የሕወሃቱ ነባር ታጋይ አቶ ዘርአይ አስገዶም ባለቤት ኮለኔል ትርፉ አስፋው በጋምቤላ ባለሶስት ኮከብ ሆቴል ባለቤት መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለጹ። ኮለኔሏ የመከላከያ ጨረታዎችን በመውሰድ ከፍተኛ ሃብት ያካበቱ መሆናቸውም ይነገራል። የአቶ ዘርአይ አስገዶም ልጆችም በአሜሪካ ውድ ትምህርት ቤቶች በመማር ላይ መሆናቸውም ታውቋል። የአሁኑ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካቲንግ ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጅ ዘርአይ አስገዶም ከተራ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለው ግድያና የፖለቲካ ቀውስ አሳስቦኛል አለች
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2010) በኢትዮጵያ ያለው ግድያና የፖለቲካ ቀውስ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው በሐገሪቱ በቅርቡ የተሾሙት የአሜሪካ አምባሳደር ገለጹ። አምባሳደር ማይክል ሬይነር የመከላከያ ሃይል የሕዝብን ሕይወት መጠበቅ እንጂ በሰልፈኞች ላይ ተኩስ መክፈት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል። አምባሳደሩ እንዳሉት በኢትዮጵያ ያለውን ችግር ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን አስተዋጾ ማድረግ ይጠበቅበታል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር በአዲስ አበባ ከተሾሙ ገና 4 ወር ተኩል ጊዜ ብቻ ነው። እናም በዚህ ...
Read More »የኦፌኮ አመራሮች ከእስር ተለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2010) አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሰባት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/አመራሮች ከእስር ተለቀቁ። አመራሮቹ ከእስር እንዲለቀቁ የተደረጉት ክሳቸው ተቋርጦና በይቅርታ መሆኑን ጠቅላይ አቃቢ ሕግ ገልጿል። ተከሳሾቹ ችሎት በመድፈር የተፈረደባቸው በመሆኑም ጉዳዩ ወደ ይቅርታ ቦርድ ሄዶ በሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ መለቀቃቸውን በሀገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የእነ አቶ በቀለ ገርባ በተፋጠነ ሁኔታ ከእስር እንዲለቀቁ የተደረጉት በኦሮሚያ የተጀመረው ሕዝባዊ ...
Read More »በኦሮሚያ የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2010) በኦሮሚያ ክልል የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል። ትላንት ያልተሳተፉ ከተሞች ዛሬ ተቀላቅለዋል። በጅማ ሁለት የሰላም ባስ አውቶቡሶች መቃጠላቸውን የደረሰን መረጃ ያስረዳል። በፍቼ የአጋዚ ወታደሮች በአንድ ትምህርት ቤት ላይ በወሰዱት ርምጃ አራት ተማሪዎች ክፉኛ ተጎድተዋል። በደብረዘይትና ጅማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ አደባባይ በመውጣት በስልጣን ላይ ያለውን ስርአት አውግዟል። ከምዕራብ ሃረርጌ አሰቦት-ጭሮ-መኢሶ አብዛኞቹ ከተሞች ...
Read More »ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የሞ ኢብራሔም ፋውንዴሽንን ሽልማት አሸነፉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የሞኢብራሔም ፋውንዴሽንን የ5 ሚሊየን ዶላር የመሪነት ሽልማት አሸነፉ። በአለም ላይ ከፍተኛ የሆነውንና ከኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች የበለጠ የገንዘብ ስጦታ የሚያስገኘውን የአፍሪካ የመሪነት ሽልማት ከሞኢብራሒም ፋውንዴሽን በማግኘት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ 5ኛ ሆነዋል። ሰርሊፍ የመጀመሪያዋ በምርጫ ስልጣን የያዙ እንስት የአፍሪካ መሪ መሆናቸውም ይታወቃል። በባለጸጋው ሙሐመድ ኢብራሒም የሚመራው የሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን የሽልማት ኮሚቴ ላለፉት 2 ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እስከ 16 አመታት የሚደርስ የእስር ቅጣት ተወሰነባቸው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) አራት የመከላከያ አባላትን በመግደል አስር አቁስለዋል የተባሉ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት እስከ 16 አመታት የሚደርስ የእስር ቅጣት ተወሰነባቸው። ድርጊቱን የፈጸምነው ለትልቅ ሃገራዊ አላማ እንጂ ለግል ጥቅማችን አይደለም ሲሉም ተከሳሾቹ በችሎት ውስጥ መናገራቸው ተመልክቷል። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የቀረቡትና የቅጣት ውሳኔ የተሰጠባቸው 8 ተከሳሾች ሰኔ 25ና ሰኔ 26/2007 በትግራይ ክልል ልዩ ሃይል እንዲሁም በሚሊሺያና ...
Read More »የኦፌኮ አመራሮች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 7 የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ አመራሮች ክሳቸው እንዲቋረጥ መወሰኑን የፌደራል አቃቢ ሕግ አስታወቀ። በዚሁም መሰረት አቶ በቀለ ገርባ፣ጉርሜሳ አያና፣አዲሱ ቡላላ፣ደጀኔ ጣፋ፣ጌቱ ጋሩማ፣ተስፋዬ ሊበንና በየነ ሩዳ ክሳቸው ተቋርጧል። የእነ አቶ በቀለ ገርባ ክስ በዚህ መልኩ ተቋርጧል ቢባልም በፍርድ ቤት ችሎት መድፈር በሚል ሁለት ጊዜ የ6 ወራት እስር ስለተወሰነባቸው ከእስር ቤት የመውጣታቸው ነገር አጠራጣሪ ነው ...
Read More »የአገዛዙ ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ ከ4 በላይ ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) በሐረር ከተማ በሃማሬሳ የስደተኞች ጣቢያ በሰፈሩ ሰዎች ላይ የአገዛዙ ታጣቂዎች በወሰዱት ርምጃ ከ4 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። በጥቃቱ በአጋዚ ታጣቂዎች ከተገደሉት መካከል አንድ የኦሮሚያ የጸጥታ ፖሊስ እንደሚገኝበትም ታውቋል። ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች እስከ 1 ሚሊየን እንደሚጠጉ በቅርቡ የወጡ አለምአቀፍ ሪፖርቶች ይጠቅሳሉ። ከነዚሁ ተፈናቃዮች መካከል በሐረር ከተማ አማሬሳ የስደተኞች ጣቢያ የተጠለሉ ይገኙበታል። የካቲት 4/2010 እሁድ በአማሬሳ የተፈናቀሉ ...
Read More »በአገዛዙ የፖሊስና የሚሊሺያ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 5/2010) በጎንደር ጯሂት በአገዛዙ የፖሊስና የሚሊሺያ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ መወሰዱ ተገለጸ። 10 የአገዛዙ ሃይሎች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ካለው የስራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ከባህርዳር ወደ ኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሺያ አውቶቡሶች ስራ አቁመው መዋላቸው ታውቋል። ዛሬ ጠዋት እስከ ቀትር ድረስ ከጎንደር አምባጊዮርጊስ ...
Read More »በኦሮሚያ ለሶስት ቀናት የተጠራው አድማ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 5/2010) በኦሮሚያ ክልል ለሶስት ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ተጀመረ። በአብዛኞቹ የክልሉ ከተሞችና የገጠር አካባቢዎች አድማው በተሳካ ሁኔታ በመካሄድ ላይ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች አድማው ተጠናክሮ ሲካሄድ ከአዲስ አበባ የሚወጡ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች መንቀሳቀስ አልቻሉም። በአምቦ በሻሸመኔ በጂማ ከአድማው ባሻገር ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች መደረጋቸው ታውቋል። የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱና ...
Read More »