የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ ብስራት አቢ በእስር ቤት በደረሰባቸው ድብደባ የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ እንደሚገኝ ተገለጸ። (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዲስ አበባ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ የበሩት አቶ ብስራት አቢ በእስር ቤት ውስጥ በደረሰባቸው ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች ምክንያት የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በማእከላዊ እስር ቤት ክፍል ውስጥ በመርማሪዎች በተፈጸመባቸው ከፍተኛ ድብደባ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ለ 95 ክፍት የስራ ቦታ 13 ሺ ሰዎች አመለከቱ (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 95 ባለሙያዎችን ለመቅጠር ላወጣው ማስታወቂያ 13 ሺ ተወዳዳሪዎች ማመልከታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ባለሥልጣኑ ታኅሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም 95 ሰራተኞችን ለመቅጠር ያወጣውን ማስታወቂያ ተከትሎ ስራ ፈላጊዎች የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አጥለቅለቀው ሰንብተዋል ብሎአል ጋዜጣው። መስሪያ ቤቱ እንዲህ አይነት ብዛት ...
Read More »ቤተ እስራኤላዊያን በአዲስ አበባ የረሃብ አድማ አደረጉ
ቤተ እስራኤላዊያን በአዲስ አበባ የረሃብ አድማ አደረጉ (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ነዋሪነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን ወደ እስራኤል ለመግባት በሚጠባበቁበት ወቅት የአገሪቱ መንግስት ድጎማ ለማቋረጥ የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም ከዛሬ ረቡእ ጀምሮ በአዲስ በአበባ በሚገኙ ቤተመቅደሶች ሴናጎ ውስጥ በመገኘት የርሃብ አድማ አድርገዋል። ቤተ እስራኤላዊያኑ ከዘመዶቻቸው ጋር ለመገናኘት በጉጉት በሚጠብቁበት ሰዓት በጀት ለማቋረጥ መወሰኑ እንዳሳዘናቸው መግለጻቸውን፣ የረሃብ ...
Read More »የቀድሞዋ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት የጥፋተኛነት ውሳኔ ተላለፈባቸው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20 2018) በሙስና ተወንጅለው ወህኒ የወረዱት የቀድሞዋ የደቡብ ኮርያ ፕሬዚዳንት በዛሬው ዕለት የጥፋተኛነት ውሳኔ ተላለፈባቸው። ውሳኔውን ተከትሎም በ30 ዓመታት እስራት እንዲቀጡ ኣቃቤ ህግ ጠይቋል። የቀድሞዋ የደቡብ ኮርያ ፕሬዚዳንት ፓክ ሁን ሄ በሙስና ተወንጅለው ከስልጣናቸው የተባረሩት አምና በመጋቢት ወር ሲሆን ፣ወህኒ ከወረዱም አንድ ዓመት ያህል አስቆጥረዋል። የ66 ዓመቷ የቀድሞዋ የደቡብ ኮ ርያ ፕሬዚዳንት ፓክ ሁን ሄ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ያልተገባ ስጦታ ...
Read More »የአገዛዙ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላም ቢሆን ሕዝቡ ተቃውሞውን በመቀጠሉ የአገዛዙ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ መታዘዙን የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት ገለጸ። ኮማንድ ፖስቱ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴና ደምቢዶሎ የተካሄደውን የሕዝብ ተቃውሞ በመጥቀስ የአገዛዙ ታጣቂዎች የሕዝብ ሕይወት እንዳይጠፋ ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ርምጃ እንዲወስዱ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የፓርላማ አባላት አስቸኳይ ጊዜውን እንዳያጸድቁ በሕዝብ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑም ሕገ ወጥ ተግባር ነው ብሏል። የአስቸኳይ ...
Read More »በሶማሌ ከእስር ቤት በይቅርታ የወጡ እስረኞች ተመልሰው ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) በሶማሌ ክልል ከሚገኘው ጄል ኦጋዴን እስር ቤት በይቅርታ ተፈቱ የተባሉ ከ1500 በላይ እስረኞች ተመልሰው ወደ እስር ቤት እንዲገቡ መደረጉ ተገለጸ። ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን የሰጡት የፍቺ ዜና ሳምንት ሳይሞላው እስረኞቹ ወደ ጄል ኦጋዴን ገብተዋል ያለው የሶማሌ ክልል ተወላጆች የአክቲቪስቶች መረብ መገናኛ ብዙሃኑ በአስቸኳይ የሰሩትን ዜና እንዲያስተባብሉ ጠይቋል። እስረኞቹ መፈታታቸው ተገልጾ፣ ፎግራፍና ቪዲዮ ከተቀረጹና ዜና ከተሰራጨ በኋላ የዚያኑ ...
Read More »ደኢህዴን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በሁለተኛ ዙር ምርጫ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ። ይህ ዜና በዚህ መልኩ ተስተካክሎ ከመወጣቱ በፊት በድርጅቱ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውይፋ ሆኖ ነበር። የደኢሕዴን ፌስ ቡክ ደረገጽ የመጀመሪያው መግለጫ የ1 ኛ ዙር ወጤት ሰለነበር ሰህተቱ መፈጸሙን አምኗል። የደኢሕዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ በየጊዜው ሲቀያየር ቆይቶ ...
Read More »የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተራዘመ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) የፊታችን ሐሙስ የተጠራው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ ተራዘመ። የምክር ቤቱ ስብሰባ የኢሕአዴግን ሊቀመንበር ለመምረጥና ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነውን ግለሰብ ለመወሰን እንደነበርም ለመረዳት ተችሏል። በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች በተለይም በሕወሃትና በኦሕዴድ መካከል ያለው ፍጥጫ ለስብሰባው መራዘም ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረም ታምኖበታል። ከእያንዳንዱ አባል ፓርቲ 45 በአጠቃላይ 180 አባላት ያሉት የኢሕአዴግ ምክር ቤት በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ምትክ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርን ...
Read More »በነቀምት ውጥረቱ ተባብሷል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2010) በነቀምት ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ። ዛሬ ጠዋት አንድ ወጣት በአልሞ ተኳሽ ወታደር መገደሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂን በመጣስ ተቃውሞ እያደረጉ ባሉ የነቀምት ነዋሪዎች ላይ ተኩስ የከፈቱት የአገዛዙ ወታደሮች ከ20 በላይ ሰዎች ማቁሰላቸውም ታውቋል። ቤት ለቤት አፈሳ የተጀመረ መሆኑኑም ተመልክቷል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ አመራሮች በወለጋ ደጋፊዎቻቸውን ለማግኘት ቀጠሮ የያዙት ከአስቸኳይ አዋጁ ይፋ መሆን ቀደም ብሎ ...
Read More »በነቀምቴ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አንድ ሰው ሲሞት በርካታ ሰዎች ቆስለዋል
በነቀምቴ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ አንድ ሰው ሲሞት በርካታ ሰዎች ቆስለዋል (ኢሳት ዜና የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ከነቀምቴ ህዝብ ጋር ለመገናኛት ያደረጉት ሙከራ አዋጁ አይፈቅድም በሚል ሰበብ በወታደሮች እንዲገታ ከተደረገ በሁዋላ፣ ህዝቡ ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን፣ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 1 ሰው መገደሉንና 7 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የኦሮምያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ...
Read More »