(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 23/2010) የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ለማጽደቅ በተጠራው የፓርላማ ስብሰባ ድጋፍ የሰጡ የምክር ቤት አባላት ከ 2/3ኛ በታች መሆናቸው ታወቀ። ይህም በህገመንግስቱ መሰረት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ውድቅ መሆኑን ያሳያል ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ገልጸዋል። ሆኖም የመንግስት እና የፓርቲ መገናኛ በዙሃን የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ጸድቋል ሲሉ ዘግበዋል። ጸድቋል በሚል ይፋ ያደረጉት ቁጥር ከሚጠበቀው በታች በመሆኑ ከሰዓታት በኋላ ቁጥሩን ለመቀየር ተገደዋል። የአስቸኳይ ግዜ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአድዋ ድል በአል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
የአድዋ ድል በአል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ (ኢሳት ዜና የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ/ም)122ኛው የአድዋ ድል በአል በአዲስ አበባና በአድዋ ተራሮች ላይ በድምቀት ተከብሯል። በአዲስ አበባ የተለያዩ ወጣቶች በአሉን በተለያዩ የጥበብ ስራዎችን አድምቀውት ውለዋል። ወጣቶቹ አባቶቻቸው የሰሩት አኩሪ ታሪክ እነሱም ጭቆና በማስወገድ እንደሚደግሙት ሲናገሩ ተሰምተዋል። በቅርቡ ከእስር የተለቀቁ ወጣቶች በስፍራው መገኘታቸውን ተከትሎ በርካታ ፖሊሶች ወጣቱን ለአመጽ ለማነሳሳት እየቀሰቀሳችሁ ነው በሚል አግተዋቸው ...
Read More »ከ100 በላይ የፓርላማ አባላት ባልተገኙበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጸደቀ
ከ100 በላይ የፓርላማ አባላት ባልተገኙበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጸደቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ/ም)ኢትዮጵያውያን እና የውጭ አገር መንግስታት በእያቅጣጫው አፋኙን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እየተቃወሙ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ዛሬ የተሰበሰው ፓርላማ፣ አዋጁን በ346 ድምጽ አጽድቆታል። በስብሰባው ላይ 106 የፓርላማ አባላት አልተገኙም። ከተገኙት መካከልም 88 የፓርላማ አባላት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል። 7 አባላት ደግሞ ድምጸ ተቃውሞ አድርገዋል። በህገ መንግስት አንቀጽ 93 ንዑስ ...
Read More »በግብጽ የመገናኛ ብዙሀን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ ታዘዘ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 22/2010) በግብጽ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ታወቀ። የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋም የሆነው ሲ ፒ ጄ ባወጣው ሪፖርት እንዳመልከተው ከሆነ ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ትዕዛዙን ያስተላለፉት ለሃገሪቱ የህግ አካላትን መሆኑም ታውቋል። የሀገሪቱ ምርጫ አንድ ወር ብቻ በቀረበት በዚህ ወቅት የሀሰት ዜናን ያሰራጫሉ በሚል መገናኛ ብዙሃንን ለማፈን ያደረገው ተግባር እንዳሳሰበውም በሪፖርቱ አስፍሯል። በግብጹ ...
Read More »የአድዋ ድል በአል እየተከበረ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 22/2010) 122ኛው የአድዋ ድል በአል ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። በአሉ ነገ አርበኞችና በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሮ እንደሚውልም ተገልጿል። በዚህ በዩናይትድ ስቴትስም የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር በአሉን ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።
Read More »የሙስና ደረጃን የሚያሳየው አመታዊ ሪፓርት ይፋ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 22/2010) ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የሙስና ደረጃ የሚያሳየውን አመታዊ ሪፓርት ይፋ አደረገ። በሕውሃት/ኢህአዴግ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት በሙስና ከተዘፈቁት ሃገራት አንዱ መሆኑን ሪፓርቱ ገልጿል። የሚዲያ ነፃነት አለመኖርና መንግስታዊ ያልሆኑ ሲቪክ አደረጃጀቶች አለመጠናከራቸው ሙሰኝነት እንዲባባስ አስተዋፅኦ አበርክቷል። መቀመጫውን ጀርመን በርሊን ከተማ ያደረገው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በየአመቱ የሃገራትን የሙስና ደረጃ በማውጣት ይታወቃል። ይህ ከመቶ በላይ ቅርንጫፎችን በመላው አለም በማቋቋም የአገራትን የሙስና ኢንዴክስ የሚያወጣው ተቋም ...
Read More »የስልጣን ገደብ በሌላቸው ሃገራት ግጭቶች እንደሚባባሱ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 22/2010) በሕገመንግስታቸው ፕሬዝዳንታዊ የስልጣን ገደብ በሌላቸው ሃገራት ግጭቶች እንደሚባባሱና የተረጋጋ አስተዳደር እንደሌለ አንድ ጥናት አመለከተ። አፍሪካ የስትራቴጂክ ጥናት ማዕከል የተባለ ተቋም ባካሄደው ጥናት እንደተገለጸው በሕገመንግስት ፕሬዝዳንታዊ የስልጣን ገደብ ከሌላቸው ሀገራት ብዙዎቹ በአፍሪካ ቀንድና በማዕከላዊ አፍሪካ የሚገኙ ናቸው። አንዳንድ የአፍሪካ ሃገራት ፕሬዝዳንቶች ደግሞ ሕገመንግስት በማሻሻል ገደቡን እንደሚጥሱም በጥናቱ ተመልክቷል። በአፍሪካ ሃገራት የመሪዎችን ስልጣን ሕገመንግስታዊ በሆነ መንገድ ለመገደብ ሙከራ ያደረጉ ...
Read More »የቀድሞዎቹ የህወሃት መሪዎች ለአሜሪካ ባለስልጣናት ማስተባበያ ሰጡ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 22/2010) የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በኢትዮጵያ የታወጀው ወታደሩ ስልጣን እንዳይወስድ ለመከላከል ነው ሲሉ የቀድሞዎቹ የህወሃት መሪዎች ለአሜሪካ ባለስልጣናት ተናገሩ። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በተመለከተ ማብራሪያ ለመስጠት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ጥያቄ ያቀረቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተቀባይነት አለማግኘታቸውንም የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል። ከሳምንታተ በፊት በዩ ኤስ አሜሪካ በዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ላይ የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሊታወጅ ነው የሚለውን ...
Read More »ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ክፍል በኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል
ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ክፍል በኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል (ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ኮማንድ ፖስት የተባለው ቡድን ተቃውሞ በነበረባቸው የኦሮምያ ክልል አካባቢዎች የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል። ትናንት የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ በኮማንድ ፖስት አባላት ከታሰሩ በሁዋላ ዛሬ ደግሞ ምክትል ከንቲባው ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። ሁለቱም ባለስልጣናት ቄሮ እየተባለ ከሚጠራው ...
Read More »በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መመልከታቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይ ተናገሩ
በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መመልከታቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይ ተናገሩ (ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በቅርቡ ከእስር ቤት ተፈተው ኖርዌይ ገቡ በሁዋላ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በእስር ቤት ውስጥ ብልታቸው የተኮላሸ፣ በድብደባ ብዛት መራመድ የማይችሉ እንዲሁም በደረሰባቸው ጥቃት ራሳቸውን ስተው ያበዱ ሰዎች መኖራቸውን ተናግረዋል። በአርበኞች ግንቦት7 አባልነት ተከሶ ...
Read More »