.የኢሳት አማርኛ ዜና

ዮናታን ተስፋዬ ከወህኒ ወጣ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2010) የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረው ዮናታን ተስፋዬ ዛሬ ከወህኒ ተለቀቀ። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌንና የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ አስረኞች ግን አሁንም በወህኒ ቤት ይገኛሉ። በመንግስት ተግባራዊ በተደረገው የምህረት ርምጃ ለመፈታት ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት የተነገረው ዮናታን ተስፋዬ ይቅርታ አልጠይቅም በማለቱ ለሳምንታት በተጨማሪ እስር ቤት ቆይቷል። ፈርመህ ውጣ ተብሎ ሲጠየቅ “እኔ ወንጀል አልፈፀምኩም፣ የተፈረደብኝ በማምነውና ስወጣም በምሰራው ጉዳይ ...

Read More »

አቶ ለማ መገርሳ በሁላችንም ልብ ውስጥ ያሉ መሪ ናቸው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2010) አቶ ለማ መገርሳ በሁላችንም ልብ ውስጥ ያሉ መሪ ናቸው ሲሉ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ገለጹ። ዶክተር አብይ አህመድም የለውጥ ሰው ናቸው ያሉት ጄኔራል ባጫ ደበሌ ሁለቱ መሪዎች የማይለያዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ሲሉ ለሁለቱም ያላቸውን ድጋፍና አክብሮት ገልጸዋል። በሐገር መከላከያ ሚኒስቴር የምህንድስና መምሪያ ሃላፊ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በጡረታ ላይ የሚገኙት ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ከኦ ቢ ...

Read More »

ዘጠኝ የአገዛዙ ታጣቂዎች በአንድ የአካባቢው ሰው መቁሰላቸው ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2010) በምዕራብ ጎጃም በደቡብ አቸፈር ወረዳ ዱርቤቴ ከተማ ዘጠኝ የአገዛዙ ታጣቂዎች በአንድ የአካባቢው ሰው መቁሰላቸው ተሰማ። በዱርቤቴ ከተማ ነዋሪ የሆኑትና አቶ ደርቤ አየለ የተባሉ የአካባቢው ታዋቂ ሰው በፌደራል ሰዎች ተከበው እጅ እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተኩስ መጀመሩ ተነግሯል። አቶ ደርቤ በከበቧቸው የአገዛዙ ታጣቂዎች ላይ የአጸፋ ርምጃ በመውሰድ ከ9 በላይ ወታደሮች አቁስለዋል።ከቆሰሉት መካከል የሞቱ እንዳሉም ይነገራል። በመጨረሻም አቶ ደርቤ ...

Read More »

ለ3ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2010) ህገወጡን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቃወም ለ3ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ በመላው የኦሮሚያ ክልል በመካሄድ ላይ ነው። በአዲስ አበባ ዙሪያ በምዕራብ ሸዋ፣ በወለጋ፣ በሀረርጌ፣ በአርሲ፣ በባሌና በሌሎች አካባቢዎች ዛሬ የተጀመረው አድማ የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ማድረጉ ታውቋል። በአዲስ አበባ አውቶቦስ ተራዎች ጭር ብለው ውለዋል። ከጅማ ወደ አዲስ አበባ በወታደራዊ አጀብ እየመጣ ያለ የህዝብ ...

Read More »

በኦሮምያ እና ጉራጌ ዞኖች የመካሄደው የስራ ማቆም አድማ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርጓል

በኦሮምያ እና ጉራጌ ዞኖች የመካሄደው የስራ ማቆም አድማ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርጓል (ኢሳት ዜና የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመቃወም በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን ጨምሮ በብዙ የኦሮምያ ክልል ከተሞችና በጉራጌ ዞን በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች እንዲሁም በስልጤ ዞን በሚገኙት በስልጤና ቡታጅራ የተጠናከረ የስራ ማቆም አድማ በመደረግ ላይ ነው። አድማው በአሸዋ ሜዳ፣ አንፎ፣ ቀርሳ፣ ቡራዩ፣ ሰበታ፣ አለምገና ቢሾፍቱ፣ ...

Read More »

በጅጅጋ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ መፈጠሩ ታወቀ

በጅጅጋ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ መፈጠሩ ታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 26 ቀን 2010 ዓ/ም) የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት የኦሮምያ ክልልና ህዝብ ማንኛውም አይነት የግብርና ውጤቶች ወደ ሶማሊ ክልል እንዳይገባ ማገዱን ተከትሎ፣ ጅጅጋ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እንደምትገኝና ህዝቡም ለችግር እንደተዳረገ ተናግረዋል። አቶ አብዲ ሙሃመድ የሚመራው የክልሉ መንግስት ችግሩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት ነዋሪወች ይናገራሉ። የምግብና ሌሎችን ሸቀጦች እየተወደዱ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በተለይ በጫት ...

Read More »

ሬክስ ቴሊርሰን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 23/2010) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴሊርሰን በመጭው ሳምንት ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 የአፍሪካ ሀገራትን እንደሚጎበኙ ተገለጸ። ሬክስ ቴሊርሰን በመጭው ረቡዕ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት በሃገሪቱ የፖለቲካ ቀውስ ዙሪያ ከሕወሃት/ኢሕአዴግ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ትብሏል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሬክ ቴሊርሰን ወደ አፍሪካ የሚያቀኑት ስልጣን ከያዙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዚሁም ጉዟቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ቻድን፣ጅቡቲን፣ኬንያንና ናይጄሪያን ይጎበኛሉ ነው የተባለው። በኢትዮጵያ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 23/2010) የኢትዮጵያው ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማጽደቁን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ። አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳለው ፓርላማው የሕዝቡን ድምጽ ከመስማት ይልቅ አፈናን ለማራመድ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማጽደቁ እጅግ የሚያበሳጭና ሃላፊነት የጎደለው ነው። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሐፊ ሳሊል ሸቲ የኢትዮጵያ ፓርላማ በዚህ አስቸጋሪና የፖለቲካ ቀውስ በተፈጠረበት ሁኔታ የሕዝቡን ድምጽ ሊሰማ ይገባ ነበር ብለዋል። አሁን የሚያስፈልገው የሕዝቡን ...

Read More »

በተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ ተከሰተ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 23/2010) በህገወጥ መንገድ አስቸኳይ አዋጁ በጸደቀበት ዕለት በተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ መከሰቱ ተሰማ። በአምቦ፣ በነጆ፣ በወሊሶና በአዲስ አበባ አስቸኳይ አዋጁን በመጣስ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ለአድዋ በዓል አደባባይ የወጡ ወጣቶች በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ የሚያወግዙ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ እንደነበር በቪዲዮ ተደግፎ ከመጣው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኪሎ በሚገኘው የፓርላማ ህንጻ በተሰበሰቡበት ሰዓት ፒያሳ ...

Read More »

122ኛው የአድዋ የድል በአል ተከበረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 23/2010) 122ኛው የአድዋ የድል በአል በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞችና ኢትዮጵያን በሚኖሩበት የተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በአሉ በድምቀት ተከብሮ ዋለ። በተለይ በአዲስ አበባ የነበረው አከባበር እጅግ ደማቅና ከሌላው ጊዜ የተለየ እንደነበር በምስል ተደግፎ ከተሰራጨው መረጃ መረዳት ተችሏል። የጣሊያን ወራሪ ሃይልን ለመመከት በአጼ ሚኒሊክ የተመራው የኢትዮጵያ ጦር የዛሬ 122 አመት አድዋ ላይ ኢትዮጵያን ነጻ አውጥቷል። ዳግማዊ አጼ ሚኒሊክ ወደ አድዋ ጦር ግንባር ...

Read More »