(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) የሩሲያ የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ በሶሪያ ውስጥ መከስከሱ ተሰማ። በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት 26 መንገደኞችና 6ቱ የአውሮፕላን ሰራተኞች በሙሉ ማለቃቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። በሶሪያ የባህር ዳርቻ በምትገኘው ላታኪያ ከተማ ባለው የሩሲያ ወታደራዊ ጦር ሰፈር በማረፍ ላይ እያለ አውሮፕላኑ መከስከሱም ታውቋል። የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ሲሆን የቅድመ ምርመራ መረጃዎች አደጋው በቴክኒካል ችግር ሳይከሰስ እንዳልቀረ አመላክተዋል። ሆኖም እውነተኛውን የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራው ቀጥሏል ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገና ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ገለጸ። ኦፌኮ በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገበት ሁኔታና የጸደቀበት መንገድ ሕገወጥ በመሆኑ አንቀበለውም ብሏል። አዋጁ ሕገመንግስቱን በጣሰ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑም ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል ለማቅረብ መዘጋጀቱንም ኦፌኮ ገልጿል። የኦፌኮ መግለጫ እንደሚያመለክተው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ...
Read More »የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተደነገገና ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የሃገሪቱ ሰላምና አንድነት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ገለጸ። ኦፌኮ በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገበት ሁኔታና የጸደቀበት መንገድ ሕገወጥ በመሆኑ አንቀበለውም ብሏል። አዋጁ ሕገመንግስቱን በጣሰ መልኩ የተፈጸመ በመሆኑም ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል ለማቅረብ መዘጋጀቱንም ኦፌኮ ገልጿል። የኦፌኮ መግለጫ እንደሚያመለክተው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ...
Read More »ሃገሪቱን በጦር ማስተዳደር የማይቻል ነገር ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) ሃገሪቱን በጦር ማስተዳደር ለመንግስቱ ሃይለማርያምም አልበጀም ሲሉ የአባገዳዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር አባገዳ በየነ ሰንበቶ አሳሰቡ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የዋህና ለሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለሃይማኖት አባቶችና ለአባገዳዎች የሚታዘዝ በመሆኑ ኮማንድ ፖስቱ አያስፈልገውም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የኦሮሞ አባገዳዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር አባገዳ በየነ ሰንበቶ የወቅቱን ሁኔታ በተመለከተ በሀገር ቤት ከሚታተም ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ይሄ ኮማንድ ፖስት የሚባለውን ነገር አልወደውም”ሲሉ ...
Read More »በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው አድማ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2010) በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠራው አድማ በኦሮሚያ ክልል ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። አዲስ አበባ ዙሪያን ጨምሮ በምዕራብ ሸዋ፣ በወለጋ፣ በምዕራብ ሀረርጌ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በባሌና በአርሲ ለሶስት ቀናት የተጠራው አድማ ተጠናክሮ መቀጠሉን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል። ከአዲስ አበባ ወደተለያዩ ከተሞች የሚደረገው የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ተቋርጧል። በሆለታ አንድ ወጣት በአጋዚ ወታደር በጥይት መመታቱ ታውቋል። በመቱ አቅመ ደካማ ለሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች የዕለት ...
Read More »በኦሮምያና ጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል
በኦሮምያና ጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመቃወም በኦሮምያ ክልል እና በጉራጌ ዞን የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ቀጥሏል። አድማው በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረ ነው። በአዲስ አበባ ዛሬም ያልተከፈቱ የንግድ ድርጅቶች መኖራቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ በተለይ ከጠዋት ጀምረው ድርጅቶቻቸውን የሚዘጉና የሚከፍቱ ሰዎችን ለመሰለል ሰቪል ለብሰው ቁጥጥር ሲያደርጉ የዋሉት የደህንነት ...
Read More »የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት “መላ በሉን” እያሉ ነው
የመከላከያ እና የፖሊስ አባላት “መላ በሉን” እያሉ ነው (ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የፖሊስ አባላት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደማያውቁ እየገለጹ ነው። ከዚህ ቀደም ባልታዬ መልኩ የጸጥታ ሃይሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ መጋባታቸውን፣ የተደራጀ ሃይል ውስጥ ተቀላቅለው ትግሉን ማካሄድ ቢፈልጉም የመረጃ እጥረት እንደገጠማቸውና በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ እንደሚገኙ ፎቶግራፋቸውን ...
Read More »የኦሮምያ ክልል ፖሊሶች አባላት እንደሆኑ የተጠረጠሩ ወታደሮች 3 የአጋዚ ወታደሮችን ገደሉ
የኦሮምያ ክልል ፖሊሶች አባላት እንደሆኑ የተጠረጠሩ ወታደሮች 3 የአጋዚ ወታደሮችን ገደሉ (ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) ከአዲስ አበባ በቅርብ እርቀት ላይ በምትገኘዋ ጣፎ ከተማ ላይ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ የኦሮምያ ክልል ፖሊሶች 3 የአጋዚ ወታደሮችን መግደላቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ፖሊሶቹ ቀን ላይ አብረው በጥበቃ ላይ እንደነበሩ የገለጹት ምንጮች፣ ምሽት ላይ የደንብ ልብሳቸውን በመቀየርና ሲቪል ልብስ በመልበስ 3 ወታደሮችን ...
Read More »የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንደማይቀበለው አስታወቀ
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንደማይቀበለው አስታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 27 ቀን 2010 ዓ/ም) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ (ኦፌኮ) ገዥው ፓርቲ አስቸኳይ አዋጁን ያጸደቀበት ሁኔታ የሕግ አግባብን ያልተከተለ በመሆኑ እንደማይቀበለው አስታውቋል። በመላው ኢትዮጵያ ለተካሄደውን ሕዝባዊ አመጽ ምላሽ ለመስጠት ገዢው ፓርቲና አጋሮቹ የአገራችንን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ጥልቅ ተሃድሶ አካሄድን ካሉ በኋላ፣ የፖለቲካ እስረኞችን እንፈታለን፣ የእስረኞች ማሰቃያ ማእከል የሆነውን ...
Read More »የሱዳን ባለስልጣናት በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተይዘው የነበሩ 177 ሰዎችን አስለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2010) የሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተይዘው የነበሩ 177 ሰዎችን ማስለቀቃቸውን አስታወቁ። ከህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ እጅ እንዲወጡ ተደርገዋል የተባሉት እነዚህ ሰዎች ከካርቱም በስተምስራቅ ምስራቅ ናይል በተባለው ስፍራ ለ21 ያህል ቀናት ተይዘው መቆየታቸውንም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል ሲል የቻይናው የዜና ምንጭ ሽንዋ በዘገባው አስፍሯል። የካርቱም የፖሊስ አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ኢብራሒም አብዱል ራሂም እንዳሉት በከፍተኛ ቅንጅት በተካሄደው አሰሳ ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹን በቁጥጥር ስር ማዋል ...
Read More »