የጎሳ ግጭቶችን ተከትሎ በኢትዮጵያ አዲስ የርሃብ አደጋ እያንዣበበ መሆኑን ዓለም አቀፍ የቤተክርስቲያናት ህብረት አስታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በአሁኑ ወቅት ያለው የድርቅ ሁኔታ ካለፈው ዓመት 2017 እ.ኤ.አ. ጋር ሲነጻጸር በከፋ ደረጃ ላይ ይገኛል የሚለው ህብረቱ፣ በተለይም በአፋር፣ በሶማሊያና በኦሮሚያ ክልሎች የሚገኙ አርብቶ አደሮች በድርቁ ክፉኛ ተጠቅተዋል ። በኢትዮጵያ ካለፉት አርባ ዓመታት ጀምሮ በተደጋጋሚ ጊዜያት ረሃብ እየተከሰቱ ነው። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የትምህርት ስርዓቱ ችግር ከሃያ ስድስት ዓመታት በኋላም እንዳልተስተካከለ መምህራን ተናገሩ፡፡
የትምህርት ስርዓቱ ችግር ከሃያ ስድስት ዓመታት በኋላም እንዳልተስተካከለ መምህራን ተናገሩ፡፡ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በትምህርት ጥራት ዙሪያ መደረግ ስላለበት የማስተካከያ እርምጃ የክልሉን መምህራን እየተዘዋወረ ሲያነጋግር ለነበረው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራር ቡድን አስተያየታቸውን የሰጡት መምህራን፣ በክልሉ ተማሪዎች ዕውቀት ላይ ከፍተኛ ቀልድ እየተፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የክልሉ ህልውና የተቀመጠው በተማረው የሰው ኃይል ላይ ቢሆንም፣ በየጊዜው የሚወጡ ውጤታማ ያልሆኑ ...
Read More »የስራ ማቆም አድማው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ሲውል፣በቀብሪደሀር የህወኃት የጦር መኮንን በኦሮሚያ ፖሊስ እንደተገደሉ ተዘገበ።
የስራ ማቆም አድማው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ሲውል፣በቀብሪደሀር የህወኃት የጦር መኮንን በኦሮሚያ ፖሊስ እንደተገደሉ ተዘገበ። (ኢሳት ዜና የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ለሶስት ቀናት የተጠራው የስራ ማቆም አድማ ዛሬም በተለይ በኦሮምያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተግባራዊ ሆኗል። የፌደራል ፖሊሶችና የአጋዚ ወታደሮች በብዛት በመውጣት እንደተለመደው የንግድ ድርጅቶችን ሲያሽጉ ውለዋል። በድርጅቶቻቸው አቅራቢያ የተገኙ ነጋዴዎችም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። አድማውን ያስተባብራሉ የተባሉ የመንግስት ሰራተኞች፣ የወረዳና የዞን ...
Read More »በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 28 አገራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ ጠየቁ።
በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ 28 አገራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ ጠየቁ። (ኢሳት ዜና የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ተፈጥሮ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረትም ጠይቀዋል። ፓርቲዎቹ ባወጡዋቸው 5 የአቋም መግለጫዎች፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ፣ የዜጎች መፈናቀል በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት እውን እንዲሆንና የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲከፈት፣ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ እንዲደረግና ከመቀባበር ፖለቲካ ወደ ሰለጠነ ህገመንግስታዊ የሽግግር ስርዓት ሽግግር ...
Read More »በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መምጣቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መምጣቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። (ኢሳት ዜና የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) በመላው ኢትዮጵያ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ እና የዋጋ ግሽበቱ ባስከተሉት ጫናዎች ምክንያት የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ፍጥነት እየናረ እንደሚገኝ ተነገረ። የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ዛሬ ባወጣው ወርሃዊ የዋጋ ንረት ልኬት ቀመር መሰረት በየካቲት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በ15 ነጥብ 6 በመቶ ከፍ ማለቱን ገልጿል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ምግብና ...
Read More »በጣሊያን የመጀመሪያው ጥቁር ሴናተር ተመረጡ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) አንድ ናይጄሪያዊ በጣሊያን የመጀመሪያው ጥቁር ሴናተር ሆነው ተመረጡ። ቶኒ ኢዎቢ የተባለው ናይጄሪያዊ በአውሮፓ ምድር የተመረጠ የመጀመሪያ ጥቁር ሴናተርም ሆኗል ሲል አወድሶታል ናይጄሪያን ፖለቲክስ የተባለው ድረገጽ። ቶኒ ኢዎቢ የኮምፒዩተር ሳይንስ ባለሙያና ኑሯቸውን ላለፉት 39 አመታት ያህል በጣሊያን ማድረጋቸውም ታውቋል። በማቶ ሳልቫኒ ፓርቲ ውስጥ ዘረኝነት ከምን ግዜውም በላይ እየታየ ነው በተባለበት በዚህ ሰአት መመረጣቸው ብዙዎችን አስገርሟል። የቶኒ ኢዎቢ በሴናተርነት ...
Read More »በአሲድ ጥቃት ቃጠሎ የደረሰባትን ኢትዮጵያዊት ለመርዳት እርዳታ እየተሰበሰ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት በአሲድ ጥቃት ቃጠሎ የደረሰባትን ኢትዮጵያዊት ለመርዳት የእርዳታ ማሰባሰብ መርሃ ግብር ተጀመረ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባልደረባ የነበረችውና አሜሪካ ከገባች ገና ሁለት አመት ብቻ ያስቆጠረችው ኢትዮጵያዊት የአሲድ ጥቃት የተፈጸመባት በደባልነት በሚኖር ግለሰብ እንደሆነም ኒውስ ፎር ቴሌቪዥን በዘገባው አመልክቷል። ሰላማዊት ተፈራ የተባለችውን ኢትዮጵያዊት ከሳምንት በፊት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የካቲት 24/2018 ከምሽቱ 1 ሰአት ከ30 አካባቢ ሰልፈሪክ አሲድ ...
Read More »በአለም የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ የሼህ መሃመድ አላሙዲን ስም አልሰፈረም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በአለም የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ የሼህ መሃመድ አላሙዲን ስም አለመስፈሩ ታወቀ። ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል በአለም በሃብት ግንባር ቀደም የሆኑት ቢልጌትም በአማዞኑ ባለቤት ጄፍ ቢዞ ተበልጠው ወደ ሁለተኛ ደረጃ መውረዳቸው ተሰምቷል። በአለም የሚገኙት ቢሊየነሮች ቁጥር 2 ሺ 208 መድረሱም ተመልክቷል። የባለጸጎቹን የሃብት መጠን በተመለከተ አመታዊ ሪፖርቱን ያወጣው ፎርብስ መጽሔት ይፋ ባደረገው የ2018 የሃብታሞች ዝርዝር ዚምባቡዌና ሃንጋሪ ቢሊየነሮቻቸውን አስመዝግበዋል። ...
Read More »የዋልድባ መነኮሳት እንዲፈቱና በእስር ቤት ውስጥ የሚፈጸምባቸው በደል እንዲቆም ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በወህኒ ቤት የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት እንዲፈቱና በእስር ቤት ውስጥ የሚፈጸምባቸው በደል እንዲቆም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት ጠየቀ። ሌሎች የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች እየተፈቱ ባሉበት ወቅት የዋልድባ መነኮሳትን በወህኒ ቤት ውስጥ ማገትና ማጎሳቆል የሕወሃት መንግስት ለቤተክርስቲያኒቱ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ ነው ሲልም ሕብረቱ አመልክቷል። “ወይባና አስኬማ የዋልድባ መነኮሳት ክብር” በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት ባወጣውና ለዋልድባ መነኮሳት አጋርነቱን በገለጸበት ...
Read More »አምስት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 28/2010) በኦሮሚያ ከተነሳው አድማ ጋር በተያያዘ አምስት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት መታሰራቸው ተነገረ። በኦሮሚያ የተጀመረው አድማ ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል። ባለስልጣናቱ የታሰሩት የስራ ማቆም አድማው እንዲካሄድ ቅስቀሳ አድርገዋል በሚል ነው። በኦሮሚያ ክልል በአገዛዙ የኮማንድ ፖስት አባላት የታሰሩት የኦሕዴድ የዞን ባለስልጣናት የምስራቅ ሃረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪን የሚጨመር ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አድማ ቀስቅሳችኋል ተብለው ከታሰሩት ...
Read More »