.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኦሮሚያ ባለስልጣናትን የማሰር ርምጃ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 30/2010) በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ ኮማንድ ፖስቱ የጀመረው ዘመቻ መቀጠሉና ወደ ዝቅተኛ ካድሬዎችም መሸጋገሩ ታወቀ። በሳምንቱ መጨረሻ በቁጥጥር ስር የዋሉት የምስራቅ ሃረርጌ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ጀማል አመዴ የሃማሬሳውን የመከላከያ ሰራዊት ጥቃት በማጋለጥ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የተናገሩ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል። የክልል፣የዞንና የወረዳ ባለስልጣናትን እንዲሁም በተዋረድ ያሉ ሃላፊዎችን ሙሉ በሙሉ ለማግለል የሚንቀሳቀሰውና በሕወሃት ጄኔራሎች የሚታዘዘው ወታደራዊ እዝ ከመካከለኛ ...

Read More »

የጦር መሳሪያ ለማስፈታት በተደረገ እንቅስቃሴ ሁለት ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 30/2010) በደቡብ ጎንደር ስማዳ ወረዳ የጦር መሳሪያ ለማስፈታት በተደረገ እንቅስቃሴ ሁለት ሰዎች ተገደሉ። በወረዳው ሙጃ ቀበሌ ከአንድ አርሶ አደር ላይ መሳሪያ ለመንጠቅ የተሰማሩ የአገዛዙ ታጣቂዎች ላይ ተኩስ መከፈቱ ታውቋል። በዚህም አርሶ አደሩና አንድ የሚሊሺያ ታጣቂ መገደላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አርሶአደሩ መሳሪያዬን አልሰጥም በማለት ከአገዛዙ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው አንድ ሚሊሺያ ገድለው መውደቃቸውን ለማወቅ ተችሏል። በአማራ ክልል መሳሪያ ...

Read More »

በሴራሊዮን ምርጫ እየተካሄደ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 29/2010)በሴራሊዮን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው። ሴራሊዮናውያንም አዲስ ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ድምጽ በመስጠት ላይ መሆናቸው ታውቋል። አዲስ የሚመረጠው ፕሬዝዳንት ያቺን ሃገር ከገባችበት የኢኮኖሚ ቀውስ ለማውጣት ብዙ ስራ ይጠብቀዋል ተብሏል። የሴራሊዮኑ ፕሬዝዳንት እርነስት ባይ ኮሮማ ላለፉት 5 አመታት በስልጣን በመቆየታቸው የሀገሪቱ ህገመንግስት ለድጋሚ ምርጫ እንዲወዳደሩ አይፈቅድላቸውም ያላል የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ፍራንስ 24። በምትካቸውም ኦል ፕዩፕልን የተባለውን የገዢው ፓርቲ በመወከል የውጪ ጉዳይ ...

Read More »

ኦብነግ ከህዋሃት ጋር ድርድር የይስሙላ ነው አለ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 29/2010) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/ በቅርቡ ከኢትዮጵያው አገዛዝ ባለስልጣናት ጋር ያካሄደው ድርድር የይስሙላና የማይጨበጥ መሆኑን የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ አባል ገለጹ። የኦብነግ ስራ አስፈጻሚ አባልና የኢንፎርሜሽን ዘርፍ ሃላፊው አቶ ሃሰን አብዱላሂ እንደገለጹት የኢትዮጵያው አገዛዝ በድርድር ስም የሚያካሄደው እንቅስቃሴ የውሸትና ለማስመሰል የሚደረግ ነው። እናም ኦብነግ ካለቀለት ስርአት ጋር ድርድር መቀጠል እንደማይፈልግ ሃላፊው ገልጸዋል። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ ስራ አስፈጻሚና ...

Read More »

ዊሊያም ዴቪሰን ከሀገር ተባረረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 29/2010) በኢትዮጵያ የብሉምበርግ ዜና ዘጋቢ ዊሊያም ዴቪሰን ከሀገር ተባረረ። ኢትዮጵያን ለቆ ወደ ቋሚ መኖሪያው ለንደን ከተመለሰ በኋላ በማህበራዊ ገጹ ባሰፈረው መልዕክት የተባረርኩበት ምክንያት ወይንም ጥፋት አልተነገረኝም ሲልም አስታውቋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2010 ጀምሮ ላለፉት 8 አመታት በአዲስ አበባ የብሉምበርግ ዘጋቢ ሆኖ መስራቱን የገለጸው ዊሊያም ዴቪሰን ካለፈው መስከረም ጀምሮ ችግር ሲያጋጥመው መቆየቱን ገልጿል። የመንግስትና የገዢው ፓርቲ መገናኛ ብዙሃንን ያህል ...

Read More »

ስዩም ተሾመ ታሰረ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 29/2010)በአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህርና በማህበራዊ ድረ ገጽ በለውጥ አራማጅነቱ የሚታወቀው ስዩም ተሾመ በኮማንድ ፖስት ተከቦ መታሰሩ ተነገረ። በበርካታ ወታደሮች ተከቦ የታሰረው ስዩም ተሾመ ቤቱ ተሰብሮ ብርበራ እንደተደረገበትና ያሉት መረጃዎች በሙሉ እንደተወሰዱበት ተነግሯል። በአምቦ ዩኒቨርስቲ የወሊሶ ካምፓስ መምህሩ ስዩም ተሾመ በአገዛዙ ላይ የሰላ ትችት በማቅረብ በማህበራዊ ሚዲያ ይታወቃል። መምህርና የለውጥ አራማጁ ስዩም ተሾመ በመከላከያና በፌደራል ወታደሮች ተከቦ መታሰሩ ቢነገርም ወዴት ...

Read More »

መሳሪያ ለማስፈታት ዝግጅት እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 29/2010) በአማራ ክልል መሳሪያ ለማስፈታት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ታወቀ። በሶስት ምዕራፎች በተከፈለ አሰራር በክልሉ መሳሪያ የታጠቁትን በሙሉ ለማስፈታት የሚያስችል ዝርዝር መመሪያ ነገ ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል። በተለይም በጎጃምና በሰሜን ጎንደር መሳሪያ ማስፈታቱ ትኩረት የተሰጠባቸው አካባቢዎች መሆናቸው ታውቋል። ማታለያና መደለያ ከማቅረብ አንስቶ በተለያዩ ዘዴዎች መሳሪያ ለመንጠቅ በአገዛዙ በኩል የሚከፈተውን ዘመቻ ለማክሸፍ ህብረተሰቡ ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ጥሪ ተደርጓል። አሁን በስልጣን ላይ ...

Read More »

ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል አመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው

ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል አመራሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ ራሱን ኮማንድ ፖስት ብሎ የሚጠራው ቡድን በኦሮምያ ክልል ፖሊሶችና አመራሮች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ቀጥሎበታል። እርምጃው በኦህዴድ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኖበታል። በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ በተለይን በለገጣፎ አካባቢ ተመድበው ይሰሩ የነበሩ የኦሮምያ ፖሊስ አባላት ምሽት ላይ ...

Read More »

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄው ነጻነትን ማስፋትእና ሁሉን አቀፍ ውይይት መደረግ ሲችል ነው አሉ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር መፍትሄው ነጻነትን ማስፋትእና ሁሉን አቀፍ ውይይት መደረግ ሲችል ነው አሉ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲሊርሰን እንዳሉት በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ስልጣንን የማሸጋገር ሂደት እንደግፈዋለን ያሉት ባለስልጣኑ፣ አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በጥብቅ መቃወሙዋንም ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን መብት እንደሚገድብ በተለይም ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እንደሚያፍን ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንደገለጹላቸው ሚኒስትሩ ...

Read More »

ወደ ውጭ የሚላከው እቃ በመጥፋቱ አብዛኛው የአየር መንገዱ የጭነት አገልግሎቱ ተቋርጧል ተባለ

ወደ ውጭ የሚላከው እቃ በመጥፋቱ አብዛኛው የአየር መንገዱ የጭነት አገልግሎቱ ተቋርጧል ተባለ (ኢሳት ዜና የካቲት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በኦሮምያ የሚካሄደውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ ከክልሉ የሚመጡና ወደ ውጭ አገር በኢክስፖርት ስም የሚላኩ እቃዎች በመቋረጣቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት በአብዛኛው ስራ ማቋረጡን ምንጮች ገልጸዋል። አመጹ ከመጀመሩ በፊት እረፍት ያልነበረው የአየር መንገዱ የጭነት አገልግሎት ፣ በአሁኑ ሰአት ሙሉ በሙሉ በሚባል ...

Read More »