(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2010) የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ለአንድ ሳምንት መራዘሙ ተገለጸ። በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ላይ ውጤታማ የተባለውን ዘመቻ በሌሎች አካባቢዎችም ለማስፋፋት በሚል የተራዘመው ዘመቻ ሌሎች እንቅስቃሴዎችም በተጓዳኝ እንደሚኖሩት ታውቋል። በአንድ ሳምንቱ ዘመቻ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር የተቻለ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ነዳጅ ወደ ሀገር ቤት እንዳይገባ፣ በሀገር ውስጥም የነዳጅ ማመላለሺያ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርገውን ዘመቻ የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ ጋምቤላ ቤንሻንጉልና ሌሎች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሶማሊያ የሚገኙ ሁለት ጎሳዎች አለመግባባታቸውን ለማስወገድ ተስማሙ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) በሶማሊያ የሚገኙ ሁለት ጎሳዎች በመካከላቸው የቆየውን አለመግባባት ለማስወገድ መስማማታቸው ተሰማ። ሳዳ ዮኒስና በኢዶ በተባሉት ጎሳዎች መካከል ለረጅም አመታት የቆየውን የእርስ በርስ ግጭት ለማስቆም ሶስት ሳምንታትን የፈጀ ውይይት መደረጉም ታውቋል። ሳዳ ዮኒስና በኢዶ በተባሉት ጎሳዎች መካከል ለረጅም አመታት በቆየው ግጭት በርካቶች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ሲዘገብ ቆይቷል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ የጎሳ መሪዎቹ ለሶስት ሳምንታት ውይይት ማድረጋቸውንና በሰላም ለመኖር ከስምምነት ...
Read More »የእምቦጭ አረምን ለመከላከል 140ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010)ጤና ለጣና በሚል እምቦጭ አረምን ለመከላከል በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ በአንድ ቀን ብቻ 140ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ። በዝግጅቱ ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። በመድረኩ በርካታ ታዋቂ ድምጻውያንና ኮመዲያን ተገኝተው ለዝግጅቱ ድምቀት ሰጥተውታል። የዝግጅቱ አስተባባሪ አለም አቀፍ ትብብር የጣና መልሶ ማልማት ድርጅት ሰብሳቢ ዶክተር ሰለሞን ክብረት ጣናን ከጥፋት ለመታደግ የባለሙያዎች ቡድን የጥናትና የቴክኒክ እገዛ ማድረጉንና ...
Read More »በዋልድባ መነኮሳት ችሎት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተገኙ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) ዛሬ በዋለው የዋልድባ መነኮሳት ችሎት ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መገኘታቸው ታወቀ። አጋርነትን ለማሳየት በተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የዋልድባ አባቶች መደሰታቸውን በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል። በካቴና እጆቻቸው አንድ ላይ ታስረው የሚታዩበት ፎቶግራፍ በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨቱን ተከትሎ ቁጣ መነሳቱም ታውቋል። በችሎቱ አካባቢ ፎቶግራፍ አንስታችኋል ተብለው የታሰሩ እንዳሉም ተገልጿል። በአባቶቹ ላይ እየተፈጸመ ያለው ስቃይ እንዲቆም ...
Read More »የኢሕአዴግ ምክር ቤት ነገ ስብሰባውን ይጀምራል
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) የኢሕአዴግ ምክር ቤት ቀጣዪን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመምረጥ ከነገ ጀምሮ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው። በስብሰባው የግንባሩ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር እንደሚመረጥም ተነግሯል። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ማንን ለማስመረጥ እደወሰነ ግን የተገለጸና የታወቀ ነገር የለም። የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ ስለመጠናቀቁም የተሰጠ መግለጫ የለም። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያካሄደውን ስብሰባ ማጠናቀቁ ይነገራል። ስራ አስፈጻሚው ሰሞኑን ያካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ የግምገማ ...
Read More »ነዳጅን የማስተጓጎሉ የመጨረሻ ቀን ዘመቻ ተካሄደ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተጠራው የማስተጓጎል ዘመቻ በመጨረሻ ቀኑ ዛሬም በመካሄድ ላይ ነው። በሰሜን ጎንደር ሸሃዲ አካባቢ በአንድ የነዳጅ ማመላለሺያ ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። በአንድ ሳምንት ግዜ ወስጥ የተቃጠሉ የነዳጅ ቦቴዎች ቁጥር ሶስት ደርሷል። በአዲስ አበባ የነዳጅ አቅርቦት ባለመኖሩ ጥቂት የማይባሉ ማደያዎች ዝግ ሆነው መዋላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በጎንደር ነዳጅ ለማግኘት ታክሲዎች ረጅም ሰልፍ ይዘው መቆየታቸውንም የደረሰን መረጃ ...
Read More »ወደ ሃገር ቤት የሚገባው ሕገወጥ መሳሪያ ጨመረ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2010) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ወደ ሃገር ቤት የሚገባው ሕገወጥ መሳሪያ መጨመሩን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ። የነዳጅ እቀባ ጥሪውን ተከትሎ ስጋት የገባቸው የነዳጅ ቦቴ ሾፌሮች በአንዳንድ ቦታዎች መቆማቸውንም የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ ለመንግስትና ለፓርቲ መገናኛ ብዙሃን አምነዋል። የሞያሌ ነዋሪዎች ወደ ኬንያ የተሰደዱት ደግሞ ኦነግ በነዛው ውዥንብር ነው ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የኮማንድ ፖስቱ ቃል አቀባይ ...
Read More »በአማራ ክልል የሚታየው የነዳጅ እጥረት የክልሉን ህዝብ ፈተና ውስጥ ከቶታል የዋጋ ንረቱም እያደር በመጨመር ላይ ነው
በአማራ ክልል የሚታየው የነዳጅ እጥረት የክልሉን ህዝብ ፈተና ውስጥ ከቶታል የዋጋ ንረቱም እያደር በመጨመር ላይ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በክልሉ የሚታዬው የነዳጅ እጥረት የህብረተሰቡን ኑሮ ማናጋት ጀምሯል። ነዳጅ ለማግኘት ለቀናት ወረፋ መያዝ ግድ እያለ ነው። በነዳጅ የሚሰሩ ፋብሪካዎች ስራ እያቆሙ ነው። የትራንስፖርት ዘርፉ በአጋጣመው የነዳጅ እጥረት የዋጋ ጭማሪ እያደረገ ነው። ይህን ተከትሎም የእቃዎች ዋጋ በአስደንጋጭ ሁኔታ ...
Read More »10 ሺ የሚጠጉ የሞያሌ ከተማ ተፈናቃዮች ስደት መጠየቃቸውን ተመድ አስታወቀ
10 ሺ የሚጠጉ የሞያሌ ከተማ ተፈናቃዮች ስደት መጠየቃቸውን ተመድ አስታወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ኬንያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር ባወጣው ዘገባ፣ እስካሁን 9 ሺ 700 ስደተኞች ከኦሮም ክልል ሞያሌ ከተማ ተፈናቅለው ኬንያ ገብተዋል። ስደተኞቹ 13 ሰዎች በወታደሮች መገደላቸውን እንደተናገሩ ተመድ አስታውቛል። በላይነሽ ታደሰ የተባሉ የ2 ልጆች እናት ፣ ጎረቤታቸው ከትምህርት ቤት የወላጆች ስብሰባ ሲመለስ በጥይት ...
Read More »መንግስት የአገሪቱን ችግር በሃይል ለመፍታት በመሞከሩ በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው ሲል ኦፌኮ ገለጸ
መንግስት የአገሪቱን ችግር በሃይል ለመፍታት በመሞከሩ በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው ሲል ኦፌኮ ገለጸ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ባወጣው መግለጫ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያገራችንን ችግር እያባበሰ ስለሆነ መንግስት አዋጁን አንስቶ ከሃቀኛ ተቃዋሚዎች ጋር ድርድር እንዲያካሂድና ብሄራዊ መግባባት እንዲፈጠር አሳስቧል። ከዚህ በፊት በአገሪቱ ታይቶ በማይታወቅ ዓይነት ከ700 ሺ በላይ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ተዘዋውሮ ...
Read More »