(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010)ጋምቤላ ውስጥ በመከላከያ ሰራዊቱ የተገደሉት የአኝዋክ ተወላጆች 2ሺ 500 ያህል እንደነበሩ የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ገለጹ። በሶስት ቀን ብቻ የተገደሉት 424 ወንዶች ሲሆኑ፣164 ሴቶች በመከላከያ ሰራዊት አባላት መደፈራቸውንም በቅርቡ ከወህኒ የወጡት አቶ ኦኬሎ አኳይ ዘርዝረዋል። በታህሳስ 1996 በጋምቤላ ጭፍጨፋ በተካሄደበት ወቅት የክልሉ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የወቅቱን ጭፍጨፋ በዝርዝር ተመልክተዋል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአብደራፊ ከተማ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በእሳት ተቃጠለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) በሰሜን ጎንደር አርማጮህ አብደራፊ ከተማ የሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በእሳት ተቃጠለ። ዛሬ ጠዋት 4ሰዓት ላይ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ እያሉ የተቀሰቀሰውን የእሳት ቃጠሎ የተነሳው የህወሃት ደጋፊ በሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆኑ ቢገለጽም ኢሳት የቃጠሎውን መንስዔ ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ ነው። በቃጠሎ የተጎዱ ተማሪዎች እንዳሉም ተገልጿል።
Read More »እነእስክንድር ነጋ ወደ እስር ቤት ተዛወሩ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) እነእስክንድር ነጋ ከነበሩበት የፖሊስ ጽሕፈት ቤት ወደ እስር ቤት መወሰዳቸው ተሰማ። ያልተፈቀደ ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል በሚል የታሰሩት እነእስክንድር ነጋ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ 48 ሰዓታት እንዳለፋቸውም ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል። ጉዳዩን በተመለከተ መግለጫ ያወጡት ዓለም አቀፍ ተቋማት ድርጊቱን በማውገዝ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ፖሊስ ጉዳዩን ለኮማንድ ፖስት አሳውቄ ምላሽ እየተጠባበኩ ነው ማለቱም ተገልጿል። ኮከብ የሌለበትን ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል ተብለው የታሰሩት እነእስክንድር ...
Read More »ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው
ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢህአዴግ ለሳምንታት ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ በመጨረሻም የኦህዴድ ሊ/መንበር የሆኑትን ዶ/ር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ይፋ አድርጓል። የህወሃት ደጋፊ የመገናኛ ብዙሃን ዶ/ር አብይ እንዳይመረጥ ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ቢከርሙም በመጨረሻ ዶ/ር አብይ ተመርጠዋል። ዶ/ር አብይ እንዲመረጡ ብአዴን ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተም ታውቋል። የዶ/ር ...
Read More »በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ በርካታ ዜጎች የዶ/ር አብይን መመረጥ ተከትሎ ደስታቸውን ወደ ጎዳና በመውጣት ገልጸዋል።
በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ በርካታ ዜጎች የዶ/ር አብይን መመረጥ ተከትሎ ደስታቸውን ወደ ጎዳና በመውጣት ገልጸዋል። (ኢሳት ዜና ማጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) በቦረናና ጉጂ ዞኖች ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት የደስታ ስሜቱን ሲገልጽ አምሽቷል። ዛሬም እንዲሁ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ ደስታውን ሲገልጽ ውሎአል። ህዝቡ “ወያኔ ቻው ቻው” የሚል መፈክር ያሰማ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ...
Read More »የሰሜን ኮሪያው መሪ ቻይናን ጎበኙ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በቻይና ጉብኝት ማድረጋቸው ተሰማ። በባቡር ቻይና መግባታቸውንና ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ ጋር መምከራቸውንም ሁለቱ ሃገራት ይፋ አድርገዋል። የሰሜን ኮሪያው መሪ የቻይና ጉብኝት ይፋ የሆነው ኪም ጆንግ ኡን ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በኋላ መሆኑ ታውቋል። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ስልጣን ከያዙበት እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር 2011 ጀምሮ የመጀመሪያ ነው የተባለውን ጉብኝታቸውን በቻይና ...
Read More »እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በርካታ ዜጎች ተጨናንቀው በሚገኝበት ክፍል ውስጥ መግባታቸው ታወቀ
እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በርካታ ዜጎች ተጨናንቀው በሚገኝበት ክፍል ውስጥ መግባታቸው ታወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ወታደራዊ እዙን ሳታስፈቅዱ ስብሰባ አድርጋችሁዋል፣ አርማ የሌለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተጠቅማችሁዋል በሚል ሰበብ በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት አቀንቃኞች ፣ ጎተራ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተጨናነቀ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል። የመብት ተሟጋቾቹ በተያዙ በመጀመሪያው ቀን ከ90 በላይ ሰዎች ...
Read More »የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) በኢትዮጵያ በቅርቡ በተቋቋመው ወታደራዊ ዕዝ /ኮማንድ ፖስት/በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት ሁለት የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተለቀቁ። ከሳምንት በፊት ከእስር የተለቀቁት የኦሕዴድ ባለስልጣናት የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ናቸው። በወታደራዊ እዙ ታስረው የነበሩት የኦሕዴድ አመራሮች የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሃብታሙ ቦረና እንዲሁም የነቀምት ከተማ ከንቲባ አቶ ካባ ሁንዴ ናቸው። እነዚሁ ባለስልጣናት በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ በየአካባቢያቸው ተከስቶ ከነበረው ...
Read More »የተፈናቀሉና የተሰደዱ ዜጎች ካሳ ተከፍሏቸው ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) ከሕገ መንግስታዊ ስርአት ውጪ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ዜጎች ካሳ ተከፍሏቸው ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱ መድረክ አሳሰበ። በማፈናቀሉ ሒደት የተሳተፉ አካላትም እስካሁን ተጠያቂ አለመሆናቸውን መግለጫው አስገንዝቧል። በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/፣ አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉአላዊነት/አረና/፣Yeኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ/ኢሶዴፓ/ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ ትላንት ጋዜጣዊ መግለጫውን ሰጥቷል። መድረክ በዚህ መግለጫው መንግስት በህገወጥ መንገድ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ማያውቋቸው አካባቢዎች ...
Read More »ዶክተር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንደሚሰየሙ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2010) ትላንት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶክተር አብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንደሚሰየሙ የኢሕአዴግ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለፓርቲና ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አቶ ደመቀ መኮንን ራሳቸውን ከምርጫው እንዳገለሉም አረጋግጠዋል። በተለያዩ ወገኖች ይፋ በሆኑ ተመሳሳይ መረጃዎች መሰረት ዶክተር አብይ አህመድ ከ170 መራጮች የ108ቱን ድምጽ በማግኘት መመረጣቸውም ታውቋል። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ...
Read More »