በተወሰኑ ክሶች አቶ መላኩ ፋንታን ነጻ ያሉት ዳኞች ከደህንነቶች ማስፈራሪያ ደረሳቸው (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ አቶ መላኩ ፋንታ በተወሰኑ ክሶች ነጻ እንደተባሉ፣ ደህንነቶች ዳኞችንና የዳኞቹን ፕሬዝዳንት ጭምር በመሰብሰብ እንዳነጋገሯቸው፣ “ ለምንድነው ነፃ የላችሁት?” የሚል ጥያቄ እንደጠየቁዋቸው ምንጮች ገልጸዋል። ዳኞቹ “ ሰውየው ከታሰረ ረጅም አመት ነው፣ ክሱን በደንብ አይተን የሚያስፈርድበት ሆኖ አላገኘነውም” ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የካናዳ መንግስት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አስቸኳይ አዋጁን በማንሳት፣ እስረኞችን በመፍታት ሁሉን አቀፍ ለውጦች እንዲያደርጉ ጠየቀ
የካናዳ መንግስት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አስቸኳይ አዋጁን በማንሳት፣ እስረኞችን በመፍታት ሁሉን አቀፍ ለውጦች እንዲያደርጉ ጠየቀ (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የካናዳ ኤምባሲ የአዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድን ሹመት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። ለሁሉም የአገሪቱ ዜጎች ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ምኅዳሩን በማስፋት መልካም አስተዳደርን በማስፈን፣ ...
Read More »በዶ/ር አብይ አህመድ የሹሙት ስነስርዓት ላይ አንዳንድ እንግዳ ነገሮች ተፈጥረው እንደነበር ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ወገኖች ገልጹ
በዶ/ር አብይ አህመድ የሹሙት ስነስርዓት ላይ አንዳንድ እንግዳ ነገሮች ተፈጥረው እንደነበር ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ወገኖች ገልጹ (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) “አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ተመርጦ ከማየው ብሞት ይሻለኛል” ብለው አብይ አህመድ በተገኙበት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ የተናገሩት የመንግስት የፓርላማ ተጠሪው አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ በበአሉ ላይ መገኘታቸው ብዙዎችን አስገርሞ ነበር። የህወሃት ዋና ዋና የሚባሉ አመራሮች ...
Read More »የትግራይ ክልል ምሁር የዶክተር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተቃወሙ።
የትግራይ ክልል ምሁር የዶክተር አብይ አህመድን ጠቅላይ ሚኒስትርነት ተቃወሙ። (ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ጉዳዩን አስመልክቶ ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ፕሮግራም ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቃለ ምልልስ የሰጡት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ምሁር ፣ዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ብለው ፈጽሞ እንዳልጠበቁ በመጥቀስ በምርጫው ቅሬታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል። በህዝባዊ አመጹ ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሲደርስ አላወገዙም በማለት ዶክተር አብይን የከሠሱት እኚሁ ምሁር፣ ከዶክተር ...
Read More »በእስራኤል ከ16ሺ በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010) እስራኤል ወደ ሀገራቸው ልትመልሳቸው የነበሩ ከ16ሺ በላይ አፍሪካውያን ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ መወሰኗን አስታወቀች። ለደህንነታቸው ሰግተውና ከሃገራቸው ሸሽተው በእስራኤል ጥገኝነት ጠይቀው የሚገኙ ስደተኞች የኢኮኖሚ ስደተኞች ናቸው በሚል ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖ እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እንዳሉት ስደተኞቹን ወደ ሌላ ምዕራባውያን ሀገራት ለማስፈር እንደተወሰነ ገልጸዋል። አብዛኞቹ ስደተኞች ኤርትራውያን መሆናቸው የሚነገረው አፍሪካውያኑ ስደተኞች በግብጽ ...
Read More »ዊኒ ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)የደቡብ አፍሪካ የጸረ አፓርታይድ ታጋይና የቀድሞ የኔልሰን ማንዴላ ባለቤት ወይዘሮ ዊኒ ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። ዊኒ ማንዴላ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት በ81 አመታቸው መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። ኔልሰን ማንዴላ ከ27 አመታት በኋላ ከእስር ሲለቀቁ ዊኒ ማንዴላ ከነጻናአ ታጋዩ ጋር ግንኑነታቸው ስላልተቋረጠ ዝናቸው ከፍተኛ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል። በኋላ ላይ ግን ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ሲለያዩ በፖለቲካም ሆነ በማህበራዊ ሕይወታቸው ዝናቸው ...
Read More »አሜሪካ ለዶክተር አብይና መንግስታቸው ድጋፌን እሰጣለሁ አለች
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለተመረጡት ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት፣እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች የደስታ መግለጫ አስተላለፉ። ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ለዶክተር አብይና መንግስታቸው ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጣለች። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እንዲነሳ ጥሪዋን አቅርባለች። አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩልም ባወጣቸው መግለጫ በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት አፋጣኝ ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን እንዲያመጣ ድጋፍ እንደምትሰጥ የገለጸችው ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የአስቸኳይ ...
Read More »በኢትዮጵያ ዘረኝነትና መከፋፈልን ማጥፋት ይገባል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)በኢትዮጵያ ዘረኝነትና መከፋፈልን ማጥፋት እንደሚገባ በፓርላማ የሃገር መሪነትን ስልጣን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ። ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና ወደ እድልና መልካም አጋጣሚ መቀየር እንደሚገባ ዶክተር አብይ ለፓርላማው በስልጣን ርክክብ ስነስርአቱ ላይ ተናግረዋል። ካለፉት 27 አመታት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ኢትዮጵያን ከፍ በማድረግ ያወደሱት ዶክተር አብይ ሰብአዊነት ያለው ንግግር በማድረግ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፈዋል። ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ...
Read More »“ከልባችን ይቅር ተባብለን በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንሻገር” ሲሉ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ተናገሩ
“ከልባችን ይቅር ተባብለን በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንሻገር” ሲሉ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ተናገሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መንግስታዊ ስልጣኑን ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውን ከልባቸው ይቅር ተባብለው፣ የትናንትናውን ምዕራፍ ዘግተው በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣዩ አገራዊ ጉዞ እንዲሸጋገሩ ጥሪ አቅርበዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ይህን እውን ለማድረግ አንዳንድ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ቢናገሩም፣ ...
Read More »በኢትዮጵያ አፋጣኝ ዴሞክራሲያዊና ኤኮኖሚያዊ የለውጥ ተሃድሶ እንዲደረግ የአስቸኳይ አዋጁ እንዲነሳ ሲል የአሜሪካ ኤምባሲ ጠየቀ
በኢትዮጵያ አፋጣኝ ዴሞክራሲያዊና ኤኮኖሚያዊ የለውጥ ተሃድሶ እንዲደረግ የአስቸኳይ አዋጁ እንዲነሳ ሲል የአሜሪካ ኤምባሲ ጠየቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የዶ/ር ዓብይ አህመድን መመረጥ አስመልክቶ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪክ ኤምባሲ በመግለጫው እንዳለው መንግስታቸው የአዲሱን ጠቅላይ ሚንስትር መሾም በበጎ ጎኑ እንደሚያየውና ከዶ/ር አብይና የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ የጋራ ግንኙነት እንደሚቀጥል ገልጿል። በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት መሰረት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃ/ማሪያም ...
Read More »