በባህርዳር ፖሊሶች አንዷን እስረኛ ከእስር ቤት አውጥተው ደፈሯት (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) በባህር ዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ እመቤት አዳነ የተባለች በጥርጣሬ የታሰረችን እስረኛ የምሽት ተረኛ ጠባቂዎች ከእስር ቤት በማውጣት አስገድደው ደፍረዋታል። እስረኛዋ ለጣቢያው የምርመራ ክፍል ሃላፊ ም/ኢንስፔክተር ፋጡማ ማሩ ብታመለከትም ኢንስፔክተሯ ድርጊቱ የፖሊስን ገጽታ የሚያበላሽ ነው በማለት ተራኛ ፖሊሶቹ በህግ እንዳይጠየቁ ለማድረግ እየተከላከለች እንደምትገኝ ታውቋል። አቤቱታው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በጅቡቲ ወደብ የሚገኙት የቻይናና አሜሪካ ሰራዊት እየተወዛገቡ ነው
በጅቡቲ ወደብ የሚገኙት የቻይናና አሜሪካ ሰራዊት እየተወዛገቡ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 26 ቀን 2010 ዓ/ም) በጅቡቲ ሊሞኒየር ወደብ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ጄቶች ከቻይና የጦር ሰፈር በሚለቀቁ ጨረሮች እየተጠቁ መሆኑን አሜሪካ ስታስታውቅ ቻይና በበኩሏ ክሱ መሰረተ ቢስ ነው ብላለች። ፋይናንሻል ታይምስ እንደዘገበው ቻይና ባለፈው ነሃሴ ወር በጅቡቲ ወደብ የጦር ካምፕ ከመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ በሁለቱ ሃያላን መንግስታት መካከል የተጀመረው ውዝግብ ቀጥሎአል። ቻይና ...
Read More »በሕንድ አቧራን የቀላቀለው አውሎ ንፋስ የ100 ሰዎችን ሕይወት አጠፋ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2010)በሕንድ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተው አቧራን የቀላቀለው አውሎ ንፋስ የ100 ሰዎችን ሕይወት አጠፋ። በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ያሉ ከተሞችን መታ የተባለው ይሄ አውሎ ንፋስ ሰዎች በተኙበት መከሰቱ ደግሞ አደጋውን የከፋ አድርጎታል ተብሏል። አቧራ የቀላቀለው አውሎ ንፋስ ቤቶችን አፍርሷል፣የኤሌክትሪክ አገልግሎትን አቋርጧ ሌሎች ጉዳቶችንም አድርሷል ብሏል ዘገባው። በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት አውሎ ንፋስ እንደሚከሰት ቢታወቅም በዚህን ያህል ደረጃ የሰው ...
Read More »በሊባኖስ አንዲት መንገድ ላይ ተጥላ መገኘቷ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2010) በሊባኖስ አንዲት ኢትዮጵያዊ ዛሬ በአሰሪዎቿ ክፉኛ ተደብድባ መንገድ ላይ ተጥላ መገኘቷ ተሰማ። ልጅቷን መንገድ ላይ ተጥላ ያገኛት አንድ ኢትዮጵያዊም ወደ ሆስፒታል ወስዷት ሕክምናዋን በማግኘት ላይ እንደምትገኝ በምስል ተደግፎ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አዊ ጉደታ የተባለችውና በሊባኖስ ጎዳና ላይ ተጥላ የተገኘችው ኢትዮጵያዊ የአምቦ አካባቢ ተወላጅ እንደሆነችና እድሜዋም ከሃያ አመት በታች እንደሆነም ታውቋል። እናም ኢትዮጵያዊቷ ሳራ በተባለች አሰሪዋ ተደብድባ በቤሩት ...
Read More »አለም አቀፉ የፕሬስ ነጻነት ቀን ተከበረ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2010) አለም አቀፉ የፕሬስ ነጻነት ቀን ዛሬ በመላው አለም ተከበረ። በቅርቡ ከወህኒ የወጣው ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ለማክበር በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ግብዣ በኬንያ ናይሮቢ ተገኝቷል። የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም እለቱን ምክንያት በማድረግ ባስተላልፉት መልዕክት መንግስታት ለመገናኛ ብዙሃን ደህንነት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። አይፌክስ የተባለው ሃሳብን በመግለጽ ነጻነት ዙሪያ የሚሰራው ተቋም ዛሬ የተከበረውን የፕሬስ ነጻነት ቀን ...
Read More »የአማራ ተወላጆች ወደ መጡበት ለመመለስ ፈቃደኛ አይደሉም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2010) ከቤንሻንጉልና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈናቀሉ ከ5 መቶ በላይ የአማራ ተወላጆች ወደ መጡበት ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገለጹ። የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ቢሮ ግን ተፈናቃዮቹ ወደ መጡበት ካልተመለሱ እነሱን ለማቋቋም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ የለም ብለዋል። ተፈናቃዮቹ ለመሞት ወደ ኋላ ተመለስን ወደ መጣንበት ቦታ አንሄድም በማለታቸው በኮማንድ ፖስት እየታሰሩ መሆናቸው ተሰምቷል። የአማራ ክልል ተወላጆችን ከተለያዩ አካባቢዎች ማፈናቀል የተለመደ ...
Read More »በጉጂ ዞን እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ተሸጋገረ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2010) የሜድሮክ ኮንትራት መራዘሙን በመቃወም በጉጂ ዞን እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም መሸጋገሩ ተሰማ። ከጉጂ ዞን በተጨማሪ በቦረና ዞን የወርቅ ዘረፋውን እናወግዛለን በሚል ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን በማሰማት ላይ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በጉጂ ዞንም ተቃውሞው ለአራተኛ ቀን መቀጠሉ ታውቋል። የተራዘመውን ኮንትራት በተመለከተ በመንግስት በኩል ምላሽ ተሰቷል። በሌላ በኩል በጅማና ሃሮማያ ዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞ መደረጉንም ለማወቅ ተችሏል። ካለፈው ...
Read More »በምዕራብና በምስራቅ ጉጂ ዞኖች የሚካሄደው ተቃውሞ ቀጥሎአል
በምዕራብና በምስራቅ ጉጂ ዞኖች የሚካሄደው ተቃውሞ ቀጥሎአል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሻኪሶ አካባቢ የሚካሄደው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ተቃውሞውን ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች ተደብድበው ሆስፒታል መግባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ድብደባ ተፈጽሞባቸው ሆስፒታል ከተኙት መካከል 6 የኮሌጅ መምህራንም ይገኙበታል። የተቃውሞው መነሻ የሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ኩባንያ የሆነው ሚድሮክ ኢትዮጵያ ለተጨማሪ 10 ...
Read More »በባህርዳር ቤተክርስቲያን ተፈናቃዮችን ከግቢዋ እንድታስወጣ ብትጠየቀም አሻፈረኝ አለች
በባህርዳር ቤተክርስቲያን ተፈናቃዮችን ከግቢዋ እንድታስወጣ ብትጠየቀም አሻፈረኝ አለች (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ከኦሮምያ ክልሎች ተፈናቅለው ባህርዳር በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የደህንነት አባላት ለቤተክርስቲያኗ ትእዛዝ ቢሰጡም፣ ቤተክርስቲያኗ ግን ተፈናቃዮችን ለማስወጣት ፈቃዳኛ አለመሆኗን ገልጻለች። የደህንነት ሰራተኞች የተፈናቃዮችን አመራሮች ይዘው በማሰር እና ተፈናቃዮች ወደ መጡበት ክልል ወይም ወደ ትውልድ አካባቢያቸው እንዲሄዱ እንዲያግባቡ ...
Read More »ሞያሌ መረጋጋት አለመቻሉዋን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ ከከተማዋ የተፈናቀሉት ዜጎች እስካሁን አለመመለሳቸውም ታውቋል
ሞያሌ መረጋጋት አለመቻሉዋን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ ከከተማዋ የተፈናቀሉት ዜጎች እስካሁን አለመመለሳቸውም ታውቋል (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በየጊዜው የሚፈጽሙት ግድያ ፣ ነዋሪዎችን አፍኖ የመውሰድ ድርጊት ሊቆም በለመቻሉ እንደ ልባቸው ወጥተው መግባት አልቻሉም። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አብዛኛው የከተማው ነዋሪዎች ቤታቸውን ዘግተው ለመቀመጥ መገደዳቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት መንገድ ላይ ...
Read More »