(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/ 2010) በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የሶማሌ ልዩ ሐይልን እንዲያፈርስ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። ተቋሙ ለጸረ ሽብር በሚል ሰበብ በሶማሌ የተቋቋመው ልዩ ሀይል ፈርሶ በህጋዊ የፖሊስ አባላት እንዲተካም ጠይቋል ። ልዩ ሃይሉ በሶማሌ መጠነ ሰፊ ጅምላ ግድያና ሰቆቃ በህዝቡ ላይ እየፈጸመ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል። የሶማሌ ልዩ ሃይል የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግን/ለመደምሰስ በሚል የተቋቋመ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በእንግሊዝ ለንደን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/ 2010) በቅርቡ ከእስር የተልቀቁት አቶ አንዳርጋጨው ጽጌ እንግሊዝ ለንደን ሲገቡ በአውሮፓና አካባቢው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለአራት ዓመታት በእስር ምክንያት ከተለያዩቸው ባለቤታቸውና ልጆቻቸው ጋር በሰላም መገናኘታቸውም ታውቋል። ኢትጵያውያኑ ላደረጉላቸው አቀባበልም ሆነ እርሳቸው ከእስር እንዲፈቱ ላደረጉት ጥረት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። ፍቺውን ለማስተጓጎል የተደረገው ሙከራ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መክሸፉንም አቶ አንዳርጋቸው ...
Read More »ከአለም ሕጻናት ከግማሽ የሚበልጡት በጦርነትና በድህነት እየተሰቃዩ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 23/2010) ከአለማችን ሕጻናት ከግማሽ የሚበልጡት በጦርነትና በድህነት በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ሴቭ ዘ ችልድረን የተባለው አለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ገለጸ። መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ሴቭ ዘ ችልድረን ትላንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት በትንሹ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአለማችን ሕጻናት ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል። 1 ቢሊየን ያህል ሕጻናት የሚኖሩት ድህነት በተስፋፋባቸው ሀገራት ነው። 240 ሚሊየን ሕጻናት ደግሞ ግጭት በቀጠለባቸው ሀገራት የሚኖሩ ...
Read More »የሀና ማርያም ነዋሪዎች በፖሊስ ተደበደቡ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 23/2010) በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ሀና ማርያም በተባለ አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ2ሺህ በላይ አባወራዎች በቤተመንግስት አቤቱታ ለማቅረብ ሄደው በፖሊስ መደብደባቸው ተገለጸ። ትላንት ማምሻውን ወደ ቤተመንግስት ያመሩት የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቤቱታ ለማቅረብ ያደረጉት እንቅስቃሴ በወከባና ድብደባ ተበትኗል። አቤት የምንልበት ቦታ አጣን በሚል በምሬት የሚገልጹት ተፈናቃዮቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ይድረስልንም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። የሃና ማርያም አካባቢ መኖርያ ...
Read More »በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ተቃውሞ አሰሙ
በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተመንግስት በመሄድ ተቃውሞ አሰሙ (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ከ3 ሺ የማያንሱ ቤታቸው የፈረሰባቸውና በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙት ዜጎች ወደ ቤተ መንግስት አምርተው ጉዳያቸውን ለጠ/ሚኒስትሩ ለማቅረብ ቢፈልጉም አልተሳካላቸውም። ይህን ተከትሎ በቀጥታ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ ሲያመሩ የፌደራል ፖሊሶች መንገድ ላይ በመጠባባቅ ሰልፈኞችን አግተው ውለዋል። ፖሊሶቹ በሰልፈኞች ላይ ያደረሱት ጉዳት የለም። ተፈናቃዮቹ ጥያቄያቸውን የሚሰማ አካል ...
Read More »የብሔራዊ ባንክ ገዢው ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ– ግንቦት 23/2010) የብሔራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መወሰኑን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ምክትል ገዢው ዶክተር ዮሃንስ አያሌው በይፋ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ታውቋል። በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ውስጥ የአፍሪካ ሃላፊ አቶ አበበ አዕምሮ ሥላሴ ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት መጠየቃቸውም ተሰምቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የሃገሪቱ መጠባበቂያ የውጭ ምንዛሪ ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚበቃ መሆኑም ተመልክቷል። የብሄራዊ ባንክ ገዢዎች ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በመወያዬታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አቶ አንዳርጋቸው ነገ ጧት ለንደን ይገባሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር በመወያዬታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አቶ አንዳርጋቸው ነገ ጧት ለንደን ይገባሉ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) የግንቦት 7 ዋና ጸሀፊና የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው ባለፉት አራት አመታት በእስር የቆዩት አቶ አንዳርጋቸው ትናንት ከቀትር በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለሁለት ሰዓታት የዘለቀ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ “መሰረታዊ ባሏቸው” ጉዳዮች ዙሪያ ስለደረጓቸው ...
Read More »የአብዲ ኢሌ የደህንነት አባላት በዱልሚዲድ አመራር ላይ ያደረጉት የአፈና እርምጃ ከሸፈ
የአብዲ ኢሌ የደህንነት አባላት በዱልሚዲድ አመራር ላይ ያደረጉት የአፈና እርምጃ ከሸፈ (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ትናንት ምሽት የአብዲ ኢሌን ፍጹማዊ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ በመቃወም ዱል ሚዲድ እየተባለ በሚጠራው በኢትዮ-ሶማሊ ተወላጆች የተቋቋመውን ድርጅት ከሚመሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑትን አቶ ካድር አዳንን ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ አፍኖ ለመውሰድ የተደረገው ሙከራ በፌደራል የደህንነት መስሪያ ቤትና በአሜሪካ ኢምባሲ አማካኝነት ሊከሽፍ ችሎአል። ...
Read More »የአፋር ክልል ገዥ ፓርቲ አብዴፓ አዲሱን የአቶ አብይ አህመድን አስተዳደር እንዳይቀበል በህወኃት በኩል አፍራሽ ተግባራት እየተፈጸሙ ነው ሲሉ በአውሮፓ የአፋር ማህበረሰብ ተወካይ ገለጹ።
የአፋር ክልል ገዥ ፓርቲ አብዴፓ አዲሱን የአቶ አብይ አህመድን አስተዳደር እንዳይቀበል በህወኃት በኩል አፍራሽ ተግባራት እየተፈጸሙ ነው ሲሉ በአውሮፓ የአፋር ማህበረሰብ ተወካይ ገለጹ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) ተወካዩ አቶ ገአስ አህመድ ዛሬ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ላለፉት 27 ዓመታት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅሙ ክፉኛ የደቀቀው የአፋር ህዝብ እውነተኛ ለውጥ እየጠየቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ገዥው የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ -ከህወኃት ...
Read More »የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት 1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲሆን ወሰነ።
የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት 1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲሆን ወሰነ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 23 ቀን 2010 ዓ/ም) የክልሉ ምክር ቤት ለክልሉ ፋይናንስ ክፍል በላከው ደብዳቤ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ህክምናቸውን በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ሲከታተሉ ቢቆዩም፣ ለውጥ ሊታይ ስላልቻለ ወደ ውጭ አገር ሄደው የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ 1 ሚሊዮን ...
Read More »