.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ኢሳያስ ጅራን ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 27/2010)የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኦሮሚያ ክልል የተወከሉትን አቶ ኢሳያስ ጅራን ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ፡፡ የ46 ዓመቱ አቶ ኢሳያስ ጅራ ከጠቅላላው 145 ድምፅ 87 በማግኘት በአፋር ሰመራ በተካሄደው ምርጫ ሲያሸንፉ አቶ ተካ አስፋው ደግሞ ምርጫውን በሁለተኝነት አጠናቀዋል። በውድድሩ የተካፈሉት ተሰናባቹ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻና አቶ ተስፋይ ካሕሳይ ከሁለተኛው ዙር ምርጫ ቀድመው ራሳቸውን ማግለላቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ...

Read More »

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ሊያደርግ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 27/2010) የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፓርቲው ሊቀመንበር ከሆኑ ወዲህ የመጀመሪያውን ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑ ተገለጸ። ውስጣዊው ክፍፍል እየተባባሰ መሄዱ እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የተጠራው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑም ተመልክቷል። ነገ ማክሰኞ የሚጀምረውና ለሁለት ቀናት የሚካሄደው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሜቴ ስብሰባ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንደተገለጸው የ2አመት ተኩል የትራንስፎርሜሽን እቅድን ለመገምገም ነው። ...

Read More »

ከሀና ማርያም የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አቤቱታ ሲያቀርቡ ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 27/2010) ከሀና ማርያም የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በመሄድ አቤቱታ ሲያቀርቡ መዋላቸው ተገለጸ። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ጀምረው፣ወደ ማዘጋጃ ቤትና አሜሪካን ኤምባሲ ዛሬም በድጋሚ  ያመሩት ተፈናቃዮቹ፡ ቤተመንግስት ሲደርሱ ከፖሊስ ጋር መጋጨታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በርካታ ተፈናቃዮች ከፖሊስ ጋር በነበረው ግጭት ጉዳት እንደደረሰባቸውም ታውቋል። በሌላ በኩል ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ ተጨማሪ 250 የአማራ ተወላጆች ወደ ባህርዳር በመጓዝላይ መሆናቸውን ...

Read More »

በጉጂና ጌዲዮ ብሄረሰቦች መካከል ግጭት ዳግም አገረሸ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 27/2010) በጉጂና ጌዲዮ ብሄረሰቦች መካከል ጋብ ብሎ የቆየው ግጭት ለሶስተኛ ግዜ ዳግም አገረሸ። ትላንት ምሽት በተቀሰቀሰው ግጭት በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ወደ ሞያሌ የሚወስደው ዋናው መንገድ ገደብ የተሰኘች ከተማ ላይ በመዘጋቱ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መቋረጡ ታውቋል። እንደገና በተቀሰቀሰው ግጭት የደረሰው ጉዳት በዝርዝር ባይታውቅም በንብረት ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈጸሙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በእስካሁኑ ግጭት ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ...

Read More »

የቤተመንግስት ጠባቂዎችና የዶ/ር አብይ አጃቢዎች ተቀየሩ

የቤተመንግስት ጠባቂዎችና የዶ/ር አብይ አጃቢዎች ተቀየሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢህአዴግ ውስጥ የሚታየውን መከፋፈል እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ በቤተመንግስት ዙሪያ ጥበቃ የሚያደርጉ እንዲሁም ጠ/ሚኒስትሩን የሚያጅቡ ሰዎች እየተቀየሩ መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ከ20 አመታት በላይ የቤተመንግስት ዋና ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ገብረትንሳኤ ገብረሚካኤል ከስልጣናቸው ተወግደው በምትካቸው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት ወርቅነሽ ብሩ መተካታቸውን የተዘገበ ሲሆን፣ ገብረትንሳይ ከስልጣን ...

Read More »

ከቄለም ወረዳ ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠየቁ

ከቄለም ወረዳ ተፈናቅለው በቆቦ ከተማ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠየቁ (ኢሳት ዜና ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) በደርግ ዘመን በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ወረዳ ሰፍረው የነበሩ ከ400 በላይ የአማራ ተወላጆች በአካባቢው ባለስልጣናት ጫና እንዲፈናቀሉ መደረጉን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ቆቦ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ ሁሉም ዜጎች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። ተፈናቃዮች እንደሚሉት ካለፉት 7 ወራት ወዲህ የአካባቢው ወጣቶች፣ ፖሊሶችና ሌሎች ...

Read More »

በአዲ ረመጥ ከተማ ፌስቡክ ላይ ጽፋችሁዋል የተባሉ ወጣቶች ታሰሩ

በአዲ ረመጥ ከተማ ፌስቡክ ላይ ጽፋችሁዋል የተባሉ ወጣቶች ታሰሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) የኮማንድ ፖስት አባላት ነን ያሉ የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ወታደሮች በወልቃይት ወረዳ አዲ ረመጥ ከተማ ነዋሪ የሆነውን ወጣት ፈቃዴ አሰፋን ይዘው በማሰር፣ ለብሶት የነበረውን የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ማሊያን አስወልቀው በቅደድና በእግራቸው በመርገጥ በመጨረሻም ወደ እስር ቤት ልከውታል። ወጣቱ፣ የወልቃይትን ጉዳይ አንስቶ በድፍረት እንደሚጽፍ፣ በሚጽፋቸው ...

Read More »

ደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድሩን እንድትፈርም የአንድ ወር ቀነ ገደብ ተቀመጠላት

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/2010) የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ደቡብ ሱዳን ጦርነቱን አቁማ የሰላም ድርድሩን እንድትፈርም የአንድ ወር ቀነ ገደብ አስቀመጠ። ሃገሪቱ ያንን የማታደርግ ከሆነ ግን የከፋ ማዕቀብ ሊጠብቃት ይችላል ብሏል። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ ነበር ደቡብ ሱዳን በእርስ በርስ ጦርነት መታመስ የጀመረችው። ለአስር ሺዎች ሞትና ለሚሊዮኖች መፈናቀል ምክንያት የሆነው ይህ የእርስበርስ ጦርነት ለእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ሳይቀር አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል። ...

Read More »

ወደወህኒ የተጋዙ አራት አብራሪዎች አሁንም ከእስር አልተለቀቁም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/ 2010) የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ የነበሩና ሥርዓቱን በመቃወማቸው ወደወህኒ የተጋዙ አራት አብራሪዎች አሁንም ከእስር እንዳልተለቀቁ ታወቀ። የፖለቲካ እስረኞች እንዲሁም በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው የነበሩና የተፈረደባቸው ጭምር ከእስር በተለቀቁበት በአሁኑ ሰዓት አራቱ የበረራ ባለሙያዎች በዝዋይና በቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች ይገኛሉ። የመቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬ በ1997 ምርጫ ማግስት በአዲስ አበባ ከተማና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተካሄደውን ግድያ በመቃወም ሔሊኮፕተር ...

Read More »

ኤፈርት ከህግ ውጭ ከወጭ ሃገር ባንኮች ብድር ሲወስድ መቆየቱ ታወቀ

 (ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 24/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ንብረት የሆነው ኤፈርት ከህግ ውጭ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና ከወጭ ሃገር ባንኮች ብድር ሲወስድ መቆየቱ ታወቀ። ይህንን ሁኔታ በማመቻቸት ለንግድ ባንክ ሃላፊዎች ትዕዛዝ ሲሰጡ የቆዩት የብሄራዊ ባንክ ገዢው አቶ ተክለወልድ አጥናፉ መሆናቸውም ተመልክቷል። ይኽው ህገ ወጥ ድርጊት በመቀጠሉ የኤፈርት ንብረት የሆነው አልመዳ ጨርቃጨርቅ አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና መውሰዱ ታውቋል። ...

Read More »