.የኢሳት አማርኛ ዜና

ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሽብር ድርጊት ሲፈጽም ቆይቷል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ራሱ በኢትዮጵያውያን ላይ የሽብር ድርጊት ሲፈጽም መቆየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ። መከላከያና ደህንነቱ ከፖለቲካ ፓርቲ ነጻ እንዲሆን ሕገ መንግስቱ ቢያዝም በተግባር ግን ይህ ሳይፈጸም መቆየቱንም ይፋ አድርገዋል። ግንቦት 7፣ኦነግና ኦብነግ ግዜ ካለፈበት የመሳሪያ ትግል ራሳቸውን አቅበው ወደ ሰላማዊ መድረክ እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዶክተር ብርሃኑ እኔን ገድለው ወይንም አስገድለው ...

Read More »

የኢድ አልፈጥር በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው

የኢድ አልፈጥር በመላ አገሪቱ እየተከበረ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) 1 ሺህ 439ኛው የኢድ አል ፈጥር በአል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነስርዓቶች በመከበር ላይ ሲሆን ሙስሊም ኢትዮጵያውያውን የተፈናቀሉ እና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ ዜጎችን እንዲያስቡ የሃይማኖቱ መሪዎች ጥሪ አቅርበዋል። በዓሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያለ ጸጥታ ችግር ተከብሯል። በጅጅጋ በአቶ አብዲ አሌ ትዕዛዝ በከተማው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢድ በአል በአደባባይ ...

Read More »

በወላይታ ሶዶ በተደረገው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት ጠፋ

በወላይታ ሶዶ በተደረገው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት ጠፋ (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዋሳ ከተማ የተካሄደውን የሲዳማ ማህበረሰብ አመታዊ የመን መለወጫ በአልን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት የተገደሉ ዜጎችን ድርጊት ለመቃወም ዛሬ በወላይታ ሶዶ በተካሄደው ተቃውሞ እስከ 5 የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን በርካታ የመንግስት መስሪያቤቶችና መኪኖች መውደማቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የሶዶ ከተማ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም፣ የዞኑ ባለስልጣናት ፈቃድ ...

Read More »

ህወሃት በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ታወቀ

ህወሃት በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ህወሃት የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ስምምነትን በተመለከተ ኢህአዴግ በቅርቡ የወሰነውን ውሳኔ ለመቃወም እንዲሁን በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር የተወሰዱ ምደባዎችን ለመቃወም የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ያደርጋል። ለሰለፉ ማካሄጃ ከፍተኛ ገንዘብ የተመደበ ሲሆን፣ በርካታ ሰዎች ከትግራይ ክልል በህወሃት ወጪ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በሰልፉ ላይ እንደሚሳተፉ ምንጮች ...

Read More »

300 የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እና በሌሎች ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩ ከእስር ተፈቱ

300 የሚደርሱ የፖለቲካ እስረኞች እና በሌሎች ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩ ከእስር ተፈቱ (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) በሽብር ወንጀል ተከሰው ሞት እና የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው 289 እስረኞች ዛሬ ከእስር ተፈተዋል። ከተፈቱት መካከል በእስር ቤት ውስጥ ጥፍሮቹ ተነቅለውና የተለያዩ የጭካኔ እርምጃዎች የተፈጸሙበት አበበ ካሴና ሌሎችም በአርበኞች ግንቦት7 ስም ታስረው የነበሩት ተለቀዋል። አበበ ካሴ በኢትዮጵያ ህዝብ ጸሎትና ትግል መፈታቱን ገልጾ ...

Read More »

ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንደሚመልሱ አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ

ከኦሮምያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ወደ ቦታቸው እንደሚመልሱ አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ/ም) የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው የለማ አስተዳደር የተፈናቀሉትን ዜጎች ወደ ነበሩበት ቀዬ ለመመለስ ስራዎችን እየሰራ ነው። አቶ ለማ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ባደረጉ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል። የኦሮምያ ክልል የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በባህርዳር ተገኝተው ከተፈናቀሉት ዜጎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የክልሉ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢን ዶክተር ይናገር ደሴ ሊተኳቸው ይችላሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ የሆኑትን አቶ ተክለውልድ አጥናፉን የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ደሴ ሊተኳቸው እንደሚችሉ ተዘገበ። በአዲስ አበባ የሚታተመው ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ አዲስ ፎርቹን  እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  ለብሔራዊ ባንክ ገዢነት  ዶክተር ይናገር ደሴን ይሾማሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀም ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተወስኗል። ሆኖም አቶ በቃሉ ዘለቀ ከንግድ ባንክ ...

Read More »

300 ያህል እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) በሽብር ወንጀል ተከሰው የተፈረደባቸው 300 ያህል እስረኞች እንዲፈቱ ተወሰነ። መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት እስረኞቹ ከዛሬ ጀምሮ ከወህኒ ቤት እንደሚወጡም ተመልክቷል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው እስረኞች በአጠቃላይ 304 ሲሆኑ ፣ከነዚህ ውስጥ ከአስራ አምስቱ  በቀር ሁሉም የአሽባሪነት ክስ ተመስርቶባቸው የተፈረደባቸው ናቸው። አበበ ካሴ እና ከለንደን ሄዶ አዲስ አበባ ላይ የታሰረው አበበ ወንድም አገኝ ...

Read More »

ለ10ኛው የብሔረሰቦች ቀን የምግብ መስተንግዶ 12 ሚሊዮን ብር መከፈሉ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8/2010) በጋምቤላ ክልል በ2008 ተካሂዶ ለነበረው 10ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የምግብ መስተንግዶ ወይዘሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ ለተባሉ የሆቴል ባለቤት ከክልሉ የመጠባበቂያ በጀት 12 ሚሊዮን ብር መከፈሉ ተገለጸ ። ገንዘቡ በበአሉ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት አቶ ማትዮስ ገለታ ስም ወጭ ተድርጎ ለወይዘሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ እንዲከፈል ትእዛዝ የሰጡት የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉክ ቱት  ናቸው። የጋምቤላ ምክር ቤት ታመው ...

Read More »

በየአካባቢው የተፈጠረው ግጭት የለውጥ ሂደቱ ባልተዋጠላቸው አካላት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8/2010) በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በየአካባቢው የተፈጠረው ግጭት በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ባልተዋጠላቸው አካላት ጠንሳሽነት እየተመራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት  ገለጸ። የፌዴራል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት  የመንግስትን አቋም በሚያመለክተው መግለጫው እንዳለው አካባቢያዊ ወሰንና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ ለግጭት የሚያነሳሱ ሴራዎች እየተስተዋሉ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለምበአዋሳ የተጀመረው ግጭት ግድያን ዘረፋን ጨምሮ  ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በወላይታ ሶዶ ግድያውን በማውገዝ በተካሄደ ትዕይንተ ...

Read More »