.የኢሳት አማርኛ ዜና

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት ከፖለቲካ ወገኝተኝነት ተላቆ ይሰራል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 12/2010) የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አግልግሎት ከፖለቲካ ወገኝተኝነት ተላቆ ሕዝብን የሚያገለገል ተቋም እንደሚሆን አዲሱ የተቋሙ ዋና ዳየሬክተር ገለጹ። በቅርቡ በጠቅላይ ሚንስትር አብየ እህመድ የተሾሙት የቀድሞው የአየር ሐይል አዣዥ ጄኔራል አደም መሀመድ እንደገለጹት ተቋሙ የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ በመደራጀት ማሻሻያ ይደረግበታል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ትናንት ለፓርላማው ባደረጉት ገለጻ ደሕንነትና መከላከያው የፖለቲካ ወገንተኞችና የአፈና መሳሪያ ሆነው መቆየታቸውን መናገራቸው ይታወሳል። ...

Read More »

የብሄራዊ ባንክ ገዢው ከሥልጣን ተነሱ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 12/2010)የብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ከሥልጣን ተነሱ በምትካቸው የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነሩ ዶክተር ይናገር ደሴ ተሹመዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ተመልክቷል። አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ሹመቱ ያልተጠበቀ እና ከሙያው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ለሌላቸው የተሰጠ ሲሉ ተችተዋል። ከ10 ዓመታት በላይ በብሄራዊ  ባንክ ገዢነት የቆዩትና አሁን ከሃላፊነት የተነሱት  አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ...

Read More »

በአርጎባና የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጆች መሃከል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ደረሰ

በአርጎባና የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወላጆች መሃከል በተፈጠረ ግጭት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ደረሰ (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ በአርጎባ ማህበረሰብ ተወላጆችና በፈንታሌ ወረዳ ውስጥ በሚኖሩ የከረዩ ማህበረሰቦች መካከል ከመሬት ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ። ትናንት በነበረው ግጭት ቢያንስ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 7 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የአካባቢው ...

Read More »

የወላይታ ህዝብ በህዝብ ላይ ለደረሰው ሞት የክልሉን መሪን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን ተጠያቂ አደረገ

የወላይታ ህዝብ በህዝብ ላይ ለደረሰው ሞት የክልሉን መሪን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን ተጠያቂ አደረገ (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሰሞኑን በሲዳማ እና በወላይታ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዛሬ በጉታራ አዳራሽ የወላይታ ከተማ ነዋሪዎችን ባወያዩበት ወቅት ፣ ህዝቡ ግጭቱን ያስነሱት የደቡብ ክልል ባለስልጣናት ናቸው ብሎአል። ህዝቡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከስብሰባ አዳራሽ እንዲወጡ ቢጠየቁም እርሳቸው ግን ስብሰባውን ...

Read More »

ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ተዘጋጀ

ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ተዘጋጀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍና ለማበረታታት የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ይደረጋል። አስተባባሪዎቹ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰልፉ አላማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰዷቸውን ጅምር የማሻሻያ ሀሳቦች ለመደገፍ፣ለማመስገንና ይበልጥ ለማበረታታት ነው። ከዚህ በተረፈ ሰልፉ የማንንም ፓርቲ አጀንዳ አያስተናግድም ብለዋል ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት አቶ ጉደታ ገላልቻ። በሀገሪቱ ህገ ...

Read More »

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ግልጽነት የተሞባለትና በብዙዎች የተወደሱበትን የመጀመሪያ ሪፖርት አቀረቡ

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ግልጽነት የተሞባለትና በብዙዎች የተወደሱበትን የመጀመሪያ ሪፖርት አቀረቡ (ኢሳት ዜና ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ከፓርላማ አባላት ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን፣ ትንተናዎቻቸውና ገልጽነታቸው ንግግሩን በስሜት ያዳምጡ በነበሩ የማህበራዊ ሚዲያ ታዳሚዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል። ዶ/ር አብይ ከዚህ በፊት የነበሩ ሁለት ጠ/ሚኒስትሮች ያደርጉ እንደነበረው ከፓርላማ ወንበራቸው ላይ ሆነው ሳይሆን፣ ሚኒስትሮችና የመምሪያ ሃላፊዎች መልስ ሲሰጡ ...

Read More »

በለኩ በነበረው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ደረሰ

በለኩ በነበረው ጥቃት ከፍተኛ ውድመት ደረሰ (ኢሳት ዜና ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ቅዳሜ ከሃዋሳ 25 ኪሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ለኩ ከተማ ፣ የአብይ አህመድን አስተዳደር ያልተቀበሉ የደቡብ ክልል መሪዎች እንዳስነሱት በሚነገረው ግጭት በርካታ ጥፋት ደርሷል። የሲዳማ ወጣቶችን በማደራጀት በሌሎች ብሄሮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸምባቸው የተደረገ ሲሆን፣ በርካታ የንግድ ቤቶች ወድመዋል። የአካባቢው የፖሊስ ሃይል ድርጊቱን በዝምታ መመልከቱን የአካባቢው ተወላጆች በጽኑ ...

Read More »

በኬንያ 8 የሃገሪቱ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣናት ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) በኬንያ 8 የሃገሪቱ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣናት አልሻባብ ጥቃት መገደላቸው ተሰማ። ባለስልጣናቱ የተገደሉት በሃገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ይጓዙበት የነበረው ተሽከርካሪ ላይ የተጠመደው ቦምብ በመፈንዳቱ ነው። ጥቃቱን የፈጸመው በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው የአልሻባብ ቡድን በተደጋጋሚ ኬንያ ወደ ሶማሊያ የላከችውን የሰላም አስከባሪ ሃይል እንድታስወጣ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን ሮይተርስ በዘገባው አስፍሯል። ይህን ተከትሎም ተከታታይ ጥቃቶችን ሲፈጽም መቆየቱንም ዘገባው አመልክቷል። የኬንያ ፖሊስ ቃል አቀባይ ቻርለስ ...

Read More »

የመቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬ ተፈታ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) የመቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬ ከእስር ተፈታ። የመቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬ ከ13 አመታት በፊት በሕዝብ የሚደርሰውን ጭፍጨፋ በመቃወም ሔሊኮፕተር ይዘው ወደ ጅቡቲ ከጠፉት የበረራ ባለሙያዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል። ከአራት አመታት በፊት የታሰረው ሌላው የበረራ ባለሙያ የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤም በተመሳሳይ ከወህኒ ቤት ወጥቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በኤርትራ ወህኒ ቤት ታስረው የነበሩት ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህም በቅርቡ መፈታታቸው ታውቋል። ሰኔ ...

Read More »

በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የወሰነው አዲስ ነገር የለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 11/2010) በኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የተወሰነ ምንም አዲስ ጉዳይ የለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ። ሕዝብ ሳይወያይበት ለምን በአደባባይ ተገለጸ በሚል ሕወሃት ያቀረበውን ጥያቄ በተመለከተም ከእንግዲህ የመደበቅ ፖለቲካ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። አሰብን ስንሰጥስ ሕዝብን አወያይተናል ወይ በማለት ጥያቄውን በጥያቄ የመለሱት ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ ውጥረቱ ሊረግብ በድንበር ላይ ያለውም ሕዝብ እፎይ ሊል ይገባል ብለዋል። የኢትዮ-ኤርትራ ...

Read More »