.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአሶሳው ግጭት በገንዘብ በተገዙ ግለሰቦች የተፈጸመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010)በአሶሳ ከተማ ከማክሰኞ ጀምሮ የተፈጠረው ግጭት በገንዘብ በተገዙ ግለሰቦች የተፈጸመ መሆኑን የክልሉ ፕሬዝዳንት አስታወቁ። ገንዘቡን የከፈሏቸውና ለዚህ ድርጊት ያሰማሯቸው እነማን ናቸው የሚለው በምርመራ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል። በግጭቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 9 የደረሰ ሲሆን በግጭቱ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥርም 49 መድረሱ ይፋ ሆኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በአማራ ክልል በባቲና በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በባቲም ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተጀመሩ ለውጦችን ለማደናቀፍ የሴራ ፖለቲካ እየተካሄደ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010) በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት ለማደናቀፍ የቴሌኮም ኔትዎርክን ከመጥፋት ጀምሮ የተደራጁ ሥራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታወቀ። ይህንን የማደናቀፍ ሴራ የሚመረምሩ ኮሚቴዎች መዋቀራቸውም ተመልክቷል። አጥፊዎቹን ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ሂደት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ጠይቋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ሰኔ 16/2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ ...

Read More »

ብአዴን የሕወሃት ወኪሎችን የማጥራት ስራ እሰራለሁ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 27/2010)የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ በመጪው ሃምሌ በሚካሄደው የድርጅቱ ጉባኤ በማዕከላዊ ኮሚቴና በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ የሚገኙ የሕወሃት ወኪሎችን የማጥራት ስራ እንደሚሰራ ምንጮች ገለጹ። አቶ በረከት ስምኦንን ጨምሮ በለውጥ ሒደቱ እንቅፋት ሆነው የቆሙትን ብአዴኖች ሙሉ በሙሉ ከድርጅት አመራርነት ለመጥረግ መዘጋጀቱም ተመልክቷል። እንደ ኢሳት ምንጮች ገለጽእ ብአዴን በአሁኑ ወቅት ካሉት 65 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የለውጡ እንቅፋትና የሕወሃት ድጋፊ ተብለው የሚታወቁት ...

Read More »

የጎንደር ሕዝብ የወልቃይትን ጉዳይ የማንሳት መብት የለውም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 19/2010) የጎንደር ሕዝብ የወልቃይት ጉዳይን የማንሳት መብት እንደሌለው የሕወሃቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል ገለጹ። የወልቃይት ነዋሪዎች ጎንደሮችን የሚያስታግስልን መንግስት አጣን እያሉን ነው ሲሉ ዶክተር ደብረጺዮን አማረዋል። ድንበራችን ተከዜ ነው የሚሉት ጎንደሮች ሀሳባቸው ኋላቀር ቢሆንም ሕገመንግስቱ ግን ሌላ ነው ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ስለወልቃይት የጻፉት ደብዳቤም የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ...

Read More »

አንድ አማራ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጥሪ ተቀብያለሁ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 20/2010)የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በውጭና በሃገር ውስጥ ለሚገኙ በአማራ ስም ለሚንቀሳቀሱ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚቀበለው አንድ አማራ የተሰኘው ድርጅት አስታወቀ። በቅርቡ የተመሰረተውና መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው አንድ አማራ ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው ያቀረቡትን የአብረን እንስራ ጥሪ በቅን ልቦና መቀበሉን አስታውቋል። ምንም እንኳን የአካሄድ ልዩነቶች ቢኖሩንም ስለሕዝባችን ህልውና አንድ አማራ ከብአዴን ጋር በጋራ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት ያረጋግጣል ...

Read More »

በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 20/2010) በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት በመደገፍ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ሰልፎች መቀጠላቸው ታወቀ። ዛሬ በሆሳዕና በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ህወሃት ከደኢህዴን ላይ እጁን እንዲያነሳ ተጠይቋል። ነገ በወልቂጤ ከተማ ተመሳሳይ ዓላማ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ነዋሪው ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በባህርዳርም ለፊታችን እሁድ የድጋፍ ሰልፍ የተጠራ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል። በተያያዘ ዜናም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት እየታየ ...

Read More »

ኢ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ስርጭቱን ሊያቋርጥ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 20/2010)  ኢ ኤን ኤን  የተባለው ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሀምሌ አንድ  ጀምሮ ስርጭቱን ሊያቋርጥ መሆኑ ተሰማ። በመጪው አርብ 110 የሚሆኑ ቋሚ ሰራተኞቹን በይፋ ሊያሰናብት መዘጋጀቱም ታውቋል። ጣቢያው በሕወሃቱ ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ቦርድ ሰብሳቢነት ሲመራ መቆየቱ ይታወሳል። የኢ ኤን ኤን ከስርጭት መውጣት ምክንያት የመንግስት መስሪያቤቶች መረጃ ለጣቢያው መስጠት በማቆማቸው መሆኑ ይነገራል። ለጣቢያው  ስፖንሰር የሆኑት ኢትዮ ቴሌኮም እና ንግድ ባንክ በድንገት ...

Read More »

በአሶሳ ከተማና አካባቢው ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 20/2010) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማና አካባቢው ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ። የግጭቱ መንስኤ በውል ባይታወቅም ችግሩ ከማንነት ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል። በግጭቱ ሰባት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊጨምር ይችላል ብለዋል የኢሳት ምንጮች ከስፍራው። በክልሉ ማኦ ኮሞ ወረዳ በቶንጎ ከተማም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ለመደገፍ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ ፖሊስ በከፈተው ተኩስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። በቤንሻንጉል ጉምዝ አሶሳ ...

Read More »

በተለያዩ አካባቢዎች ግጭት ለማስነሳት ትንኮሳ የሚያደርጉ ሃይሎች እና ጠ/ሚኒስትሩን ለመግደል የሞከሩ ሃይሎች አንድ መሆናቸውን መንግስት አስታወቀ

በተለያዩ አካባቢዎች ግጭት ለማስነሳት ትንኮሳ የሚያደርጉ ሃይሎች እና ጠ/ሚኒስትሩን ለመግደል የሞከሩ ሃይሎች አንድ መሆናቸውን መንግስት አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ በህዝቡ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከሩ ሃይሎች በተለያዩ ቦታዎች የትንኮሳ ድርጊቶችን ሊፈጽሙ እንደሚችሉና ጥንቃቄ እንዲደረግ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል። እነዚህ ሃይሎች በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ትንኮሳዎችን ይፈጽማሉ የሚል ...

Read More »

በሆሳዕና ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ። ባህር ዳር የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት በ3 አቅጣጫዎች ሊገቡ የነበሩ ቦንቦች ተይዘዋል። በሃረር ከተማ ደግሞ የድጋፍ ሰልፍ እንዳይካሄድ ክልከላ ተደርጓል።

በሆሳዕና ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ። ባህር ዳር የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት በሚደረግበት ወቅት በ3 አቅጣጫዎች ሊገቡ የነበሩ ቦንቦች ተይዘዋል። በሃረር ከተማ ደግሞ የድጋፍ ሰልፍ እንዳይካሄድ ክልከላ ተደርጓል። (ኢሳት ዜና ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የጀመሩትን የለውጥ እንቅስቃሴዎች በመደገፍ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ዛሬም በሆሳና ከተማ ቀጥሎ ውሎአል። የከተማዋ ነዋሪዎች በሆሳና ስታዲየም በነቂስ በመውጣት ለጠቅላይ ሚንስትሩ ያላቸውን አጋርነት ...

Read More »