በእስር ቤት ውስጥ በሚፈፀምባቸው ድብደባ ለሕይወታቸው እንደሚሰጉ ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ ገለፁ (ኢሳት ዜና ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ/ም)ከቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በእነ አርጋው ሞገስ የክሰ መዝገብ የተከሰሱት አርጋው ሞገስና ቴዎድሮስ ዳንኤል ፍርድ ቤት ቀርበው እውነታውን በመናገራቸው ብቻ በቂሊንጦ እስር ቤት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ለፍርድ ቤቱ ገለጹ። ተከሳሾቹ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የፕሬስ ድርጅት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንቅስቃሴዎች ሽፋን እንዳይሰጥ እያደረጉ ነው ተባለ።
የፕሬስ ድርጅት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንቅስቃሴዎች ሽፋን እንዳይሰጥ እያደረጉ ነው ተባለ። (ኢሳት ዜና ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) ይህን ያሉት፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሠራተኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ግልጽ የአቤቱታ ደብዳቤ ላይ ነው።በአዲስ ዘመን፣ በኢትዮጵያን ሄራልድ፣ በበሬሳ፣ በአል ዓለም ጋዜጦችና በዘመን መጽሄት የሚሠሩ በርካታ ጋዜጠኞች “በድርጅታችን ውስጥ የሚካሄደውን ዓይን ያወጣ ጥላቻና ሳቦታጅ ስለመጠቆም” በሚል ርዕሰ ለዶክተር አብይ አሕመድ ...
Read More »የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ሰሞኑን በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ለጠፋው የሰው ህይወትና ለወደመው ንብረት ይቅርታ ቢጠይቅም፣ አሁንም የለውጥ እንቅፋት የሆኑ የክልሉ መስተዳድር አካላት ሕዝቡን እያማረሩ መሆናችው ተገለጸ።
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ሰሞኑን በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ለጠፋው የሰው ህይወትና ለወደመው ንብረት ይቅርታ ቢጠይቅም፣ አሁንም የለውጥ እንቅፋት የሆኑ የክልሉ መስተዳድር አካላት ሕዝቡን እያማረሩ መሆናችው ተገለጸ። (ኢሳት ዜና ሰኔ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ደሴ ዳልኬ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሀዋሳ ከተማና አከባቢዋ፣ እንዲሁም በለኩ፣ በይርጋለም ፣ በወንዶ ገነት ፣ በሻመና፣ በወልቂጤ፣በአማን፣ በአማሮ፣በቡረጅ እና በጉጅ ዞን ...
Read More »ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአፋር ክልል ከህዝቡ ጋር ተወያዩ። የተወሰኑ የአፋር ምሁራንና ወጣቶች ተነጥለው በውይይቱ እንዳይገኙ ከመደረጋቸውም ባሻገር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ታወቋል።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአፋር ክልል ከህዝቡ ጋር ተወያዩ። የተወሰኑ የአፋር ምሁራንና ወጣቶች ተነጥለው በውይይቱ እንዳይገኙ ከመደረጋቸውም ባሻገር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ታወቋል። (ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ሕዝባዊ ውይይት አደርገዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን መምጣት ተከትሎ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የሆነው የአፋር ሕዝብ ዴሞክራሲያ ፓርቲ (አ.ብ.ዴ.ፓ.) የፓርቲውን አባላትና ደጋፊዎችን ከተለያዩ ከተሞች ...
Read More »በኢትዮ-ሶማሊ ክልል ነዳጅ የማውጣት ስራ ቢጀመርም፣ የሶማሊ ክልል ተወላጆች ቅሬታ እንዳላቸው እየገለጹ ነው።
በኢትዮ-ሶማሊ ክልል ነዳጅ የማውጣት ስራ ቢጀመርም፣ የሶማሊ ክልል ተወላጆች ቅሬታ እንዳላቸው እየገለጹ ነው። (ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጹት የአገራችንን ሃብት መጠቀም መጀመሩ ጥሩ ቢሆንም፣ በአካባቢው ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ትኩረት አለማግኘቱን፣ በበቂ ሁኔታ የአካባቢ ጥበቃ አለመደረጉ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ህዝቡ ውይይት እንዲያደርግበት አለመጋበዙ ቅር አሰኝቶናል ብለዋል። ከድፍድፍ ማውጫ ግንባታው ጋር በሽላቦ አካባቢ ከፍተኛ የግጦሽ መሬት ...
Read More »ጄኔራል ማሾ በየነ ከምስራቅ አዛዥነት ስልጣናቸው ተነሱ
ጄኔራል ማሾ በየነ ከምስራቅ አዛዥነት ስልጣናቸው ተነሱ (ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሶማሊው ክልል ፕሬዚዳንት ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ማዕሾ በየነ ደስታ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ታውቋል። ጄኔራሉ ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው መሄዳቸውንም ምንጮች ተናግረዋል። በሶማሊ ክልል ከፍተኛ የሆነ የሙስና ሰንሰለት የዘረጉት ጄኔራል ማዕሾ ከክልሉ መነሳታቸው፣ ለአብዲ አሌ አገዛዝ መልካም ዜና አይደለም ተብሏል። ...
Read More »በተደራጀ ሁኔታ ሽብር የሚፈጽሙ፣ መብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ የሚያጠፉ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ኃይሎች መኖራቸውን መንግስት አስታወቀ
በተደራጀ ሁኔታ ሽብር የሚፈጽሙ፣ መብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ የሚያጠፉ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ኃይሎች መኖራቸውን መንግስት አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጀመሩትን አገራዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል በተደራጀ ሁኔታ የሚሰሩ ኃይሎች መኖራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታወቀ። እነዚህ ቡድኖች በአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ ከተፈጸመው የቦንብ ጥቃት በተጨማሪ መብራትና የቴሌኮም ኔትወርክ ማጥፋት፣ የኢኮኖሚ አሻጥር ...
Read More »የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ከስልጣናቸው ሊነሱ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010)የደቡብ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ከስልጣናቸው እንደሚነሱ ተገለጸ። ሰሞኑን የድርጅቱ አመራር ሆነው የተመረጡት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምትካቸው እንደሚመረጡም ተመልክቷል። የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱና በሌላ የደኢሕዴን አባል እንደሚተኩ የዘገበው በሀገር ቤት የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው። አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ተክተው ከሐምሌ 6/2005 ጀምሮ ላለፉት 5 አመታት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ሲሰሩ የቆዩት አቶ ደሴ ዳልኬ በአቶ ...
Read More »በአማራ ክልል በግጭት ለሞቱና ለቆሰሉ ወገኖች ካሳ ሊከፈል ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010) በአማራ ክልል ላለፉት አመታት በተካሄደው ግጭት ለሞቱና ለቆሰሉ ወገኖች የክልሉ መንግስት ካሳ ለመክፈል መወሰኑን አስታወቀ። የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የክልሉ መንግስት ለሰለባዎቹ አጋርነቱን ለመግለጽ ያህል የካሳ ክፍያ እንደሚፈጽም አረጋግጠዋል። በዚህም መሰረት ሰለባ ለሆኑ ወገኖች ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 75 ሺ ብር እንደሚከፈል ተገልጿል። አካላቸው ጎሎ መስራት ለማይችሉ ወገኖች ደግሞ ...
Read More »የቦምብ ፍንዳታው የሚመረመረው በስድስት ቡድን በተከፈሉ ባለሙያዎች ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 21/2010) በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 16/2010 በመስቀል አደባባይ የተከሰተውን የቦምብ ፍንዳታ ለመመርመር ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የአሜሪካ የምርመራ ቢሮ ባለሙያዎች በስድስት ቡድን የተከፈሉ መሆናቸውን ምንጮች ገለጹ። ይህ በእንዲህ እንዳለም ከቦምብ ጥቃቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ከታሰሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር በተጨማሪ ስድስት ኮማንደሮችም በተመሳሳይ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የዋስትና መብት የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ...
Read More »