(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በምዕራብ ጎጃም ፍኖተሰላም በተካሄደ ስብሰባ ህዝቡ በህወሀት ላይ ከፍተኛ ቁጣ ማሰማቱ ተገለጸ። ላለፉት 27 ዓመታት በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸምው ግፍና መከራ በህዝቡ በዝርዝር ተነስቶ የህወሀት አገዛዝ ላይ ውግዘት መቅረቡን ያገኘነው መረጃ ያምለክታል። በህዝብ ላይ ይሄ ሁሉ መከራ ሲደርስ ብአዴን የት ነበረ በሚል በአመራሮቹ ላይ ተቃውሞ መሰማቱን ለማወቅ ተችሏል። ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስተዳደር ድጋፍ ለማሳየትና ከለውጡ ለመጓዝ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት አምጽ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከትላንት ሌሊት ጀምሮ አምጽ መቀስቀሱ ተሰማ። በጥይትና በአስለቃሽ ጢስ በርካታ እስረኞች ተጎድተዋል። በዞን አራት የሚገኙ እስረኞች እንፈታ የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ተከትሎ የተጀመረው አመጽ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከፍተኛ ውጥረት ማንገሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአከባቢው መንገዶች መዘጋታቸው ተገልጿል። እስረኞች የድረሱልን ጩሀት እያሰሙ መሆኑም ታውቋል።በተመሳሳይ በደብረማርቆስ ማረሚያ ቤት በተቀሰቀሰ አመጽ ቤቶች መቃጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በአርባምንጭ እስር ...
Read More »በወለጋ ደምቢዶሎ አንዲት ነፍሰጡር ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በወለጋ ደምቢዶሎ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት አንዲት ነፍሰጡር ተገደሉ። ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልታወቁ ሰዎችም ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል። በባሌ ጎባ የተከሰተው ግጭት ዛሬም መቀጠሉን የገልጹት ነዋሪዎች መንግስት በአስቸኳይ ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አድርገዋል። በባቢሌ በጭናክሰን ውጥረቱ መባባሱን ያገነኘው መረጃ ያመልክታል። በተያያዘ ዜናም በደሴ ባልታወቁ ሃይሎች በተፈጸመ የስለት መሳሪያ ጥቃት በርካታ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
Read More »ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ መጡ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ። የእርቅ ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ የሁለቱም አባቶች የተገናኙበት የጋራ የጸሎት ስነስርአት ተካሂዶ አንደነበር ታውቋል። ከሐገር ቤት የመጡት አባቶች በውጪ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት የጸሎት ስነስርአት ላይ ሲገኙ የውጪ ሲኖዶሱ አባላት ደግሞ በሐገር ቤቱ ሲኖዶስ በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት ...
Read More »በካናዳ አንድ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ አንድ ሴትን ሲገል 13 ሰዎች ቆሰሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በካናዳ ሕዝብ በሚበዛበት አካባቢ አንድ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ አንድ ሴትን ሲገል 13 ማቁሰሉ ተገለጸ። የግለሰቡ ጥቃት ያነጣጠረው በሁለት ምግብ ቤቶች ላይ መሆኑ ደግሞ አነጋጋሪ አድርጎታል። ግለሰቡ በከፈተው ተኩስ ከቆሰሉት መካከል ሕጻናት እንደሚገኙበትም የተገለጸ ሲሆን ሕይወቷ አስጊ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሴትም መኖሯ ታውቋል። የ29 አመቱን ተጠርጣሪ ሞቶ መገኘቱንና ከዛ በፊት ግን ከፖሊስ ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲያደርግ እንደነበርም ተገልጿል። ...
Read More »ሕገ ወጥ የመሳሪያና የገንዘብ ዝውውር እየጨመረ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ ሕገ ወጥ የመሳሪያና የገንዘብ ዝውውር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ። ይህ በሃገሪቱ ሰላምና ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። የጦር መሳሪያዎቹ ከቱርክ ተነስተው በሱዳንና በጅቡቲ በኩል እየገቡ መሆናቸውንም ከኮሚሽነሩ መግለጫ መረዳት ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በጥቁር ገበያና በመደበኛ የሚመነዘረው የውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ተቀራራቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸው ታወቋል። በዶላር እስከ 10 ብር የነበረው ልዩነት ወደ ...
Read More »በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊጎትተው አይገባም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ የተከሰተው የፖለቲካ ሁኔታ ሰራዊቱን ሊጎትተው አይገባም ሲሉ ጠቅላይ ኢታማጆር ሹሙ አሳሰቡ። ኢታማጆር ሹሙ ጄኔራል ሰአረ መኮንን በኢትዮጵያ የታየው ለውጥ ከዘራችን ይልቅ በኢትዮጵያዊነታችን እናስብ የሚል ነው በማለትም ተናግረዋል። በፓርቲዎች ስኩቻ ውስጥ ግን አያገባንም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ከሐገር መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ጋር የተወያዩትና በመከላከያ ሰራዊቱ ፕሮግራም ላይ በተላለፈው መልዕክታቸው ሰራዊቱ ከፖለቲካ ነጻ ሆኖ ለሕገመንግስቱና ለሕገመንግስታዊ ስርአቱ እንደሚቆም አረጋግጠዋል። ...
Read More »ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ተደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቅ ጉባኤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ወደ አንድ ሲኖዶስ እንዲመጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ። በዚህም የቀድሞው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ የቤተክርስቲያኒቱን መንበር እንዲይዙ ይደረጋል ማለት ነው። አሁን በሃገር ቤት ባለው ሲኖዶስ ያሉት አቡነ ማቲያስ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን የአስተዳደር ስራ እንዲሰሩ ተወስኗል ተብሏል። ለሰላም ድርድሩ ተቀምጠው የነበሩት አባቶችም በጉዳዩ ዙሪያ ...
Read More »በባሌ ጎባ በተፈጸመው ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 16/2010) በባሌ ጎባ በማንነትና ከእምነት ጋር በተያያዘ የተፈጸመው ጥቃት ለበርካታ ሰዎች መገደል ምክንያት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። በአካባቢው የታጠቁ ሃይሎች በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ የመከላከያና የፌደራል ወታደሮች ቢገቡም የባሌ ጎባ ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ስጋት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ጥቃቱን ለመከላከል የመጡት የፌደራል ወታደሮች ቁጥራቸው ጥቂት በመሆኑ ተጨማሪ ሃይል ካልመጣ ከፍተኛ እልቂት ሊከሰት ይችላል።
Read More »በጅግጅጋ ወጣቶች በአብዲ ኢሌ አገዛዝ ላይ ተቃውሞ አደረጉ
በጅግጅጋ ወጣቶች በአብዲ ኢሌ አገዛዝ ላይ ተቃውሞ አደረጉ (ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወጣቶቹ ተቃውሞዋቸውን ያሰሙት የአብዲ ኢሌን ፍጹማዊ አገዛዝ በመቃወም እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ተጠርጥረው የተሳሩ ዜጎች እንዲፈቱ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እስር ቤቶች እንዲዘጉ ለመጠየቅ ነው። ወጣቶቹ ተቃውሞአቸውን በሚያሰሙበት ወቅት አብዲ አሌ ወታደሮቹን ልኮ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ማድረጉን አቶ አሊ አብዲ ሃሰን ከጅግጅጋ ገልጸዋል። በጥቃቱ እስካሁን የደረሰውን ...
Read More »