ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “አገራችንን ከወድቀት ለማዳንና አንድነቷን አስጠብቆ ለማስቀጠል አሁኑ ተነስተን በጽናት እንታገል” ሲል አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ። “አገርን ከውድቀት መታደግ፤የወቅቱ አንኳር ጥያቄ ነው”በሚል ርዕስ አንድነት ባወጣው መግለጫ፤ “ከሦስት ሺህ ዓመታት በላይ በህልውናዋ ፀንታ የቆየችውን ይህችን አገር የዛሬዎቹ የኢህአዴግ ካድሬዎች ሲሸራርፏትና ለባዕዳን አሳልፈው ሲሸጧት ፤እጃችንን አጣምረን ዳር ቆመን ልንመለከት አይገባም” ብሏል። ኢህአዴግ የህልውናው እስትንፋስ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሙስሊም ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ያለውን መጅሊስ ለመታደግ፤ ኢህአዴግ “በሽምግልና” ስም ጣልቃ መግባቱ ተሰማ
ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሙስሊም ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ያለውን “የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት” (መጅሊስ) ለመታደግ፤ ኢህአዴግ “በሽምግልና” ስም ጣልቃ መግባቱ ተሰማ። በኢህአዴግ ሸምጋይነት በዛሬው ዕለት በመጅሊሱ መሪዎች እና ብዙሀኑን ምእመን በሚወክሉት ጊዜያዊ ወኪሎች መካከል ሊደረግ የነበረው ውይይት፤ ሳይካሄድ ቀርቷል። በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ በሽፈራው ወልደማርያም እና በሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ አወያይነት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ይህ ሽምግልና ሳይጀመር የቀረው በምን ...
Read More »የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሶማሊያን ጎበኙ
ጥር 24 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ዊሊያም ሄግ የሶማሊያ ዋና ከተማ በሆነቸው ሞቃዲሾ የተገኙት በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ነው። የአፍሪካ ህብረት አባል አገሮች በሶማሊያ መረጋጋት እንዲፈጠር ጦራቸውን እንዲልኩ ሚኒስትሩ አሳስበዋል። ከሁለት ሳምንት በሁዋላ እንግሊዝ በሶማሊያ ጉዳይ የሚመክር አንድ አለማቀፍ ውይይት አዘጋጅታለች። በውይይቱ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ ስለመገኘታቸው የተነገረ ነገር ባይኖርም የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያ እና የኬንያ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ...
Read More »አንድ ፖሊስ ጥር 21 ቀን የአስቴርዮ ማርያም ክበረ በዓል በሚከበርበት ዕለት በህዝቡ ላይ በተኮሰው ጥይት ጉዳት ደረሰ
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋሞጎፋ ዞን በጨንጫ ወረዳ አንድ የወረዳው ፖሊስ የአስቴርዮ ማርያም ክበረ በአል በሚከበርበት እለት በህዝቡ ላይ በተኮሰው ጥይት አንድ ሰው ወዲያውኑ ሲሞት ፣ በርካቶች በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸው ታወቀ የኢሳት የጋሞጎፋ ዞን ወኪል እንደዘገበው በጨንጫ ወረዳ የአስቴርዮ ማርያም በአል ከፍተኛ ህዝብ ተገኝቶ የሚያከብረው ሀይማኖታዊ ክብረ በአል ነው። በእለቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ከአርባምንጭ እና ከሌሎች ከተሞች ...
Read More »አዲሱ የሊዝ አዋጅ በክፍለ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት ፈጥሯል
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢዎች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንደዘገቡት፣ የኑሮ ውድነቱ የፈጠረው ውጥረት ሳይበርድ አሁን ደግሞ የሊዝ አዋጁ መጨመሩ ህዝቡ አለመረጋጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በኦሮሚያ የሚኖሩ ሰው ሲናገሩ በእርሳቸው አካባቢ አዲሱ የመሬት ፖሊሲ የህዝብ አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው። ነገሮች ሊፈነዱ ተቃርበዋል የሚሉት እኝሁ ግለሰብ መድረክ የሊዝ አዋጁን በመቃወም ሊጠራ ያሰበው ስብሰባ ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ ...
Read More »የመንግስት ጋዜጠኞችና መድረክ መወዛገባቸው ተሰማ
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውዝግቡ መንስኤ መድረክ ባለፈው ዓርብ አዲሱን የሊጅ አዋጅ በመቃወም በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የመንግስትና የ ኢህአዴግ ድርጅት ልሳናት ጋዜጠኞች ከ ዋናው አጀንዳ በመውጣት ፦”ሰሞኑን አፋር ውስጥ በአሸባሪዎች የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ -መንግስት የያዘውን አቋም ትደግፋላችሁ?ወይስ ትቃወማላችሁ?” የሚል ጥያቄ አከታትለው በመጠየቃቸው ነው። ጋዜጣዊ መግለጫውን እየሰጡ የነበሩት የመድረክ አመራሮችም በስፍራው የተገኙ ጋዜጠኞች የየመጡበትን የሚዲያ ተቋማት ይገልጹላቸው ዘንድ ...
Read More »አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የዓፄ ሀይለሥላሴ ሐውልት ቅሬታና ተቃውሞ አስነሳ
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቻይና መንግስት በ200 ሚሊዮን ዶላር በተገነባው አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤትና አዳራሽ ቅጥር ግቢ ውስጥ የዓፄ ሀይለሥላሴ ሐውልት አለመቆሙ፤ በኢትዮጵያ የታሪክ ምሁራን ዘንድ ቅሬታና ተቃውሞ አስነሳ። ቻይና- ለአፍሪካ ህብረት እንደ ገጸ-በረከት በነፃ ገንብታ ባስረከበችውና ባለፈው ሳምንት የመሪዎቹ ጉባኤ ሲካሄድ ተመርቆ በተከፈተው ታላቅ ህንፃ ውስጥ፤ከፓን አፍሪካኒዝም ሀሳብ አራማጆቹና ከአፍሪካ አንድነት መስራቾቹ ቀደምት የአፍሪካ መሪዎች መካከል ...
Read More »ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በደረሰበት የከፋ ድብዳባ ጆሮው ሲደማ በዓይኑ ማየቱን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ተናገረ
ጥር 23 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአውራምባ ታይምሱ ማኔጂንግ ኤዲተር የነበረውና በቅርቡ በደረሰበት ጫና ለስደት የተዳረገው ጋዜጠኛ ዳዊት ይህን የተናገረው፤ ሰሞኑን የአቶ መለስ ፍርድ ቤት በነ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ላይ ፍርድ መስጠቱን ተከትሎ -ከህብር ሬዲዮ ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ነው። በ አንድ ችሎት ላይ ውብሸት ፍርድ ቤት ሲቀርብ ጆሮው ሲደማ መመልከቱንና ይህ የሆነውም በደረሰበት ድብደባ መሆኑን እንደተረዳ የገለጸው ጋዜጠኛ ዳዊት፤ ከዚያ ...
Read More »የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በአገሪቱ ውስጥ የሚሰሩትን ዋና ዋና ዘመናዊ ህንጻዎች መቆጣጠራቸውን ለማወቅ ታቸለ
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የምርመራ ክፍል ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰሩ ህንጻዎችን ባለቤቶች ለማወቅ ባደረገው ጥረት የተወሰኑትን ህንጻዎች ባለቤቶችና የወጣባቸውን ወይም የሚወጣባቸውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ ችሎአል። በተለምዶ ቦሌ መድሀኒአለም እየተባለ በሚጠራው ወይም ወረዳ አስራ ሰባት ውስጥ በምእረባዊያን የቤት ደረጃ የሚሰሩት ቤቶች 90 በመቶ የሚሆኑት በከፍተኛ ጄኔራሎች ባለቤትነት የሚሰሩ ወይም ተሰርተው የተጠናቀቁ ናቸው። በዚህ ስዕል የሚታየው በሶኮልላንድ ኩባንያ ...
Read More »በጋምቤላ ክልል ከመከላከያ ሰራዊት በተተኮሰ ጥይት 3 ሰዎች ሲገደሉ ሁለት ደግሞ ቆሰሉ
ጥር 22 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋምቤላ ክልል ፉኝዶ ከተማ የመከላከያ ማዘዢያ ጣቢያ ውስጥ በድንገት በተተኮሰ ጥይት ሶስት ሰዎች ተገድለው ሁለት መቁሰላቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ገልጧል። ጥር 19 ፣ 2004 ዓም ከሌሊቱ 8 ሰአት ሲሆን ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ታይተዋል ተብሎ፣ ሰራዊቱ በየአቅጣጫው በከፈተው ተኩስ የግለሰቦቹ ህይወት አልፎአል በክልሉ የሚታየውን የመሬት ነጠቃ በመቃወም በርካታ ነዋሪዎች ነፍጥ እያነሱ ...
Read More »