.የኢሳት አማርኛ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ነገ ዋሽንግተን ዲሲ ይገባሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 18/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ነገ ሐሙስ ማለዳ ዋሽንግተን ዲሲ ይገባሉ ተባለ። የፊታችን ቅዳሜ ከ25ሺ ከሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ጋር በዋሽንግተን ሲዲው ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚመክሩም ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ እለት ምሽት ላይ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ከተመረጡ 1 ሺ 500 ኢትዮጵያውያን ጋር የሚወያዩበት ሌላ መርሃ ግብርም ተይዟል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዋሽንግተን ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ከምሁራንና ከሌሎች ወገኖች ጋር ...

Read More »

የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለኢትዮጵያና ኤርትራ ግኑኝነት እንሰራለን አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 18/2010)በቅርቡ ወደ ኤርትራ የተጓዙት የኢትዮጵያ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ለኢትዮጵያና ኤርትራ ግኑኝነት መጠናከር በሙያቸው የራሳቸውን አስተዋጾ እንደሚያደርጉ አስታወቁ። አስመራ ላይ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት  አራት ታዋቂ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር  አስተዋጾ ላደረጉት  ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ  ምስጋና አቅርበዋል። የኪነጥበብ ባለሙያዎቹን አብርሃም ወልዴን ፣መስፍን ጌታቸውን፣ሰለሞን ቦጋለንና ሳምሶን ታደሰን በማነጋገር ጠይብ  ቃዲ  ከአስመራ ያጠናቀረውን ሪፖርት ብሩታዊት ግርማዬ ...

Read More »

የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት ለደረሰባቸው ጥቃት አስፈላጊው ካሳ እንዲከፈላቸውና ጥያቄያቸውም እንዲመለስላቸው ጠየቁ

የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት ለደረሰባቸው ጥቃት አስፈላጊው ካሳ እንዲከፈላቸውና ጥያቄያቸውም እንዲመለስላቸው ጠየቁ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) የማህበረሰቡ ተወካዮች ለጠ/ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ ዘንድሮም ሆነ ከዚህ ቀደም በተነሳው ጥያቄ ምክንያት ለአመታት ለተፈጸመው የሰው እልቂት ለሟች ቤተሰቦች የደም ካሳ እንዲከፈል ጠይቀዋል። “በዘንድሮው እልቂት፣ በተቋማትና ንብረት መውደም መንስኤ የሆኑ ንጹሃንን በማደናገር አሳስተው አሰለፉ፣ ጥፋትና ውድመት ያደረሱ ያደረሱ በየደረጃው ያሉ አካላት ...

Read More »

በሃረር ስርዓት አልበኝነት እየተስፋፋ በመምጣቱ ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው

በሃረር ስርዓት አልበኝነት እየተስፋፋ በመምጣቱ ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወኪላችን እንደገለጸው በአካባቢው የሚታዬው ስርዓት አልበኝነት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በቄሮ ስም የሚነግዱ ወጣቶች ውሃ ወደ ሃረር ከተማ እንዳይገባ ለማድረግ የየረርን ትልቁን የውሃ ቧንቧ በመስበር ውሃ መከልከላቸው ታውቋል። በሃሮማያ አካባቢ ደግሞ ውሃ በቦቴ ወደ ሃረር እንዳይገባ ለማድረግ የመኪኖችን ...

Read More »

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደረሰ

በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደረሰ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 18 ቀን 2010 ዓ/ም ) ትናንት በደብረማርቆስና አርባ ምንጭ እስር ቤት ቃጠሎ ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት ከደረሰ በሁዋላ፣ ዛሬ ደግሞ በወልድያ፣ ፍኖተሰላም፣ ሸዋ ሮቢትና መቀሌ እስር ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደርሷል። በወልድያ እስር ቤት በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ 2 ሰዎች ሲሞቱ 3 ሰዎድ ደግሞ ቆስለዋል። በመቀሌ እስር ቤት በተነሳው ቃጠሎም ...

Read More »

የማምረቻ እንዱስትሪዎች በዶላር እጥረት ለቅሶ ላይ ነን ሲሉ ባለሀብቶች ተናገሩ

የማምረቻ እንዱስትሪዎች በዶላር እጥረት ለቅሶ ላይ ነን ሲሉ ባለሀብቶች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኢትዮጵያ የማምረቻ እንዱስትሪ ባለሀብቶች ከአዲሱ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ከአቶ ይናገር ደሴ ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲሁም ያለውን የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ ለውጭ ባለሀብቶች መሰጠቱ ከፍተኛ ጉዳት እያመጣባቸው ነው። የሲዲኤፍ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤት 800 ሰራተኞችን ቢያስተዳድሩም፣ ወደ አምራች እንዱስትሪ የገቡበትን ...

Read More »

በደሴ ከተማ ሸዋ በር መስጂድ ውስጥ ጥቃት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች ተያዙ።

በደሴ ከተማ ሸዋ በር መስጂድ ውስጥ ጥቃት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች ተያዙ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) በትናንትናው እለት በደሴ ከተማ ሸዋ በር በመባል በሚጠራው መስጂድ ውስጥ ድምጽ አልባ የስለት መሳሪዎችን ይዘው በመግባት መስኪዱ ውስጥ የነበሩ ምእመናን ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በመስጅዱ ሃይማኖታዊ ፀሎት በማድረግ ላይ እያሉ ቁርአን እናስቀራለን በሚሉና አናስቀራም በሚሉ መሃከል አለመግባባት መፈጠሩን ምንጮቻችን ገልጸዋል። በወቅቱ በተከሠተው ...

Read More »

በላዎስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 17/2010) በላዎስ በመገንባት ላይ ያለ አንድ ግድብ በድንገት ፈርሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ ተሰማ። ለኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫነት የተገነባው ይህ ግድብ 770 ሜትር ርዝመት እንዲሁም 16 ሜትር ከፍታ እንደነበረው ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል። በፈረንጆቹ 2013 ግንባታው የተጀመረው ይህ ግድብ ለመደርመሱ ምክንያት የሆነውም በአካባቢው የጣለው ከባድ ዝናብ መሆኑም ተመልክቷል። ከጣለው ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞም ከ6,600 በላይ ሰዎች ቤት አልባ መሆናቸው ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ላበረከተው አስተዋጾ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት። በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኤርትራውያን ፌስቲቫል ላይ ተገኝተው የእውቅና ሽልማቱን የተረከቡት የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው። በፌስቲቫሉ ላይ የሁለቱ ሀገራትንና የአፍሪካውን ቀንድ ሰላም የተመለከተ ጉባዔ ተካሄዷል። በምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎችም ቀርበዋል።

Read More »

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን ለውጥ እንደግፋለን አሉ

(ኢሳት ዲሲ– ሐምሌ 17/2010) በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ገለጹ። የወንጌል አማኞቹ ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማሕበራዊ መስኮች በተወጠረችባቸው ጊዚያት ሁሉ በጸሎትና በምልጃ  ልመና ሲያደርጉ እንደነበረ ጠቅሰው አሁንም ለተጀመረው የሰላምና የእርቅ ጉዞ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ቃል በመግባት መግለጫ አውጥተዋል። እሁድ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ጉባዔ ላይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሀል የተደረሰው የሰላም ...

Read More »