.የኢሳት አማርኛ ዜና

የየመኑ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ጥገኝነት የመጠየቅ ሃሳብ እንዳላቸዉ ተገለፀ

የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በህዝብ አመፅ ከስልጣን የተባረሩት የየመኑ የቀድሞ ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በኢትዮጵያ ጥገኝነት የመጠየቅ ሃሳብ እንዳላቸዉ ረዳቶቻቸዉ ገለፁ ጥቂት ዘመዶቻቸዉ እንዳደረጉት ሁሉ ኦማንን እና የተባበሩት አረብ ኢምሬትስን ለመሳሰሉ አገሮች የጥገኝነት ጥያቄ ያቀርባሉ ተብለዉ ይጠረጠሩ የነበሩት የየመን የቀድሞ አምባገነን ፕሬዝዳንት አሊ አብደላ ሳላህ ለጥገኝነት ጥያቄያቸዉ የሚያስቧት አገር ኢትዮጵያ እንደሆነች ረዳቶቻቸዉ ገለፁ። የመንን ለረዢም አመታት በአምባገነን የመሩት ...

Read More »

ኢትዮጵያ የኮሜሳ ነፃ የንግድ ቀጣና አባል አገር ለመሆን ኢንዱስትሪያዊ ብቃት እንደሌላት ተገለፀ

የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ የምስራቅና የደቡባዊ አፍሪቃ የንግድ ቀጣና የጋራ ገበያ /ኮሜሳ /  ነፃ የንግድ ቀጣናዉ አባል ስለምትሆንበት ሁኔታ በቅርቡ በተደረገ ጥናት የአገሪቱ የማምረቻ ኢንዱስትሪ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ የመሆን አቅም እንደሌለዉና መሻሻል እንደማይታይበት ፎርቹን ጋዜጣ ገለፀ። ኮሜሳ ወጪዉን በሸፈነዉና የፋይናንስና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ያስተናበረዉን  ጥናት ያካሄደዉ መሰረቱን ዚምባብዌ ያደረገ ዚም ኮንሰልት የተባለ ገለልተኛ የኢኮኖሚና የፕላን አማካሪ ድርጅት ...

Read More »

ታጋይ ፍሰሃ አብርሃ አረፈ

የካቲት 21 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞ መከላከያ ሚንስትር ና የህወሓት መስራች የሆኑት የአቶ ስዬ አብርሃ የሶስት ጊዜ ታናሽ ወንድም የሆነው ታጋይ ፍሰሃ አብረሃ ዛሬ ሌሊት ህይወቱ አለፈ፡፡ ፍሰሃ ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ የህወሃት ታጋይ የነበረ ሲሆን፤ ከመንግስት ለውጥ በኋላ በተንቤን አውራጃ የሀገረ ሰላም አስተዳዳሪ ሆኖ ሰርቷል። በ1993ዓ.ም የተከሰተውን የህወሓት ክፍፍል ተከትሎ አቶ ስዬ አብርሃ ሲታሰሩ ፣ ፍሰሃም ለአራት አመት ያህል ...

Read More »

ጥምረት ከሚያዘጋጃቸው ስብሰባዎች መካከል ሁለተኛው በሂውስተን ቴክሳስ ተካሄደ

የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚሁ ስብሰባ ላይ የግንቦት7 ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ፣ የኦነግ የስራ አስፈጻሚ አባልና የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ  የሆኑት አቶ አዴሳ ቦሩ እና ተዋቂው አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ በእንግድነት ተገኝተዋል። የግንቦት 7 ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋል ጥምረት ለነጻነት፤ ለፍትሃና  ለእኩልነት በጄነራል ከማል ገልቹ ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር ባለፈው ሳምንት ...

Read More »

አስራ ሁለት ሺ ኢትዮጵያውያን በሱዳን ታሰሩ

የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዲያስ አዲስን በመግለጽ የዘገበው ደብረብርሀን ብሎግ ፣ በሰሜን ሱዳን ውስጥ በሚገኘው ኦምዱርማን እስር ቤት ውስጥ 12 ሺ ኢትዮጵያውያን ታስረው ይገኛሉ። ምንም እንኳ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን ያለ ህጋዊ ሰነድ ወደ ሱዳን  የገቡ ናቸው ቢባልም፣ ህጋዊ ወረቀት የያዙት ሳይቀር መታሰራቸው ተዘግቧል። በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያውያን ችግሩን በሱዳን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሲያመለክቱ ኢምባሲው  “አያገባኝም ” የሚል መልስ መስጠቱ ታውቋል። ...

Read More »

የአቶ ስብሀት ነጋ የሰጡት አስተያየት አነጋጋሪ ሆኗል

የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሀት እርሳቸው የሚመሩት የሰላምና አለማቀፍ ተቋም ኢንሰቲቲዩት ባዘጋጀው ውይይት ላይ ነው፣ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ለምን በጥቃቅን የሙስና አይነቶች ላይ ብቻ ያተኩራል በማለት ጠይቀው፣ በኢትዮጵያ ሙስናን ለማጥፋት ፍላጎት እንጅ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ብሎ ነገር የለም። ይህ በሌለበት ተግባርም ውጤትም አይኖርም። ቁርጠኛ ሌባ አለ ቁርጠኛ ተዋጊ ግን የለም።” በማለት እርሳቸው በአምሳያቸው የቀረጹትን የመለስን መንግስት ነቅፈዋል። አቶ ...

Read More »

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሙስና ከተጠየቅኩ ወይዘሮ አዜብ መጠየቅ አለባቸው አሉ

የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የውስጥ ምንጮቹን በመጥቀስ እንገለፀው፤ይህ የሆነው የክልሉ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ-ደኢህዴግ ከየካቲት 5 እስከ የካቲት 11 ቀን 2004 ዓመተምህረት ድረስ ባካሄደው ግምገማ ላይ ነው። ቀደም ሲል በጋምቤላ በተደረገ ተመሣሳይ ግምገማ በ አኝዋኮች ጭፍጨፋ ተጠያቂ እንዲሆኑ ውሳኔ የተላለፈባቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦባንግ ኦሞድ፦” በ አኝዋኮች ግድያ እኔ የምጠየቅ ከሆነ፤ ድርጊቱ እንዲፈፀም ትዕዛዝ ያስተላለፈልኝ ...

Read More »

በስዊድን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ የተሳካ ዝግጅት አካሄደ

የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እኤአ ፌብሩዋሪ 25፣ 2012 በስቶክሆልም በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 6 ሰአት እስከ ምሽ ቱ 4 ሰአት በተከናወነው በዚህ ዝግጅት የኢሳት ጋዜጠኞች የሆኑት ገሊላ መኮንንና አፈወርቅ አግደው፣ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው መስፍን ነጋሽ፣ በእንግድነት ተገኝተዋል። ዝግጅቱ በክርስትናና እስልምና ሀይማኖት መሪዎች ጸሎት የተከፈተ ሲሆን በቅርቡ ለነጻነቱ ሲል ራሱን ያቃጠለውን የኔሰው ገብሬን በቅርብ የሚያውቁት መምህር ...

Read More »

በጋምቤላ የሚገደሉት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው

የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአካባቢው መሬት በመውሰድ በእርሻ ሥራ ላይ የተሰማራ ወጣት ሰሞኑን ተገደለ። በሊዝ ኪራይ  በጣም ሰፊ መሬት በመውሰድ በእርሻ ሥራ ላይ  የተሰማሩ ሦስት ወጣቶች ፤እርሻቸውን ጎብኝተው ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የተኩስ እሩምታ በመክፈት አንድኛውን ገድለውና አንድኛውን ክፉኛ አቁስለው ከአካባቢው ተሰውረዋል። ከስፍራው የደረሰን ተጨባጭ  መረጃ እንደሚያመለክተው፤መኪናው ውስጥ ከነበሩት ሶስት ወጣቶች መካከል አንድኛው ምንም ጉዳት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጅሊስ እኛን አይወክለንም፣ አህባሽን እና ኢህአዴግን ግን ሊወክል ይችላሉ አሉ

የካቲት 19 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወሊያ መስጊድ ከቀኑ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለሰባት ሰዓታት በቆየው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስትና በመጂሊስ ላይ ያነጣጠሩ ጠንካራ ተቃውሞዎች ተስተጋብተዋል።  ይሁንና፤ በመስጊዱ ውስጥ “መጅሊስ አይወክለንም፣ ኮሚቴው የማያውቀውና ከእውቅናው ውጪ የሆነው “ኢህአዴግም አይወክለንም” የሚሉ በርካታ በኤ 4 መጠን የተባዙ ወረቀቶችለምዕመኑ መበተናቸውና  በተለያዩ ቦታዎች ተለጥፈው መታየታቸው፤በተቃውሞው ማሰማቱ ሂደት ላይ እንቅፋት ፈጥሮ ነበር።   የተቃውሞ ወረቀቱ ከ ...

Read More »