.የኢሳት አማርኛ ዜና

በዳውሮ ዞን ከፍተኛ የሆነ የውሀ እጥረት ተከስቷል

 መጋቢት 6 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-በዳውሮ ዞን በሚገኙ አራት ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የውሀ እጥረት መከሰቱን የዞኑ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዋካ እና በተርጫ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጡት በዞኑ ተፈጠረው የውሀ እጥረት ህዝቡ አንድ ጀሪካን ውሀ ለማግኘት በእጅጉ ተቸግሯል። ለዞኑ የውሀ ማስገቢያ ተብሎ የተላከው ገንዘብ በሙስና መበላቱንም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to ...

Read More »

በጋምቤላ በርካታ ሰዎች ክልሉን እየለቀቁ ነው

በጋምቤላ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጉዳት በማድረስ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ክልሉን እየለቀቁ ነው ከትናንት በስቲያ በጋምቤላ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ፣ የመሀል አገር ሰዎች ወይም በተለምዶ ደገኞች እየተባሉ የሚጠሩ ነዋሪዎች ተመሳሳይ ጥቃት  ይፈጸም ይሆናል በሚል ስጋት አካባቢውን በአለው የትራንስፖርት አማራጭ ሁሉ እየለቀቁ ነው። በርካታ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ክልሎች በመኪና መጓዛቸውን በአይኑ መመልከቱን ወኪላችን ገልጦአል።     በትናንትናው እለት በርካታ የፌደራልና ...

Read More »

መንግስት ቀለደብን ሲሉ መምህራን ተናገሩ

መንግስት የደሞዝ ጭማሪ አደረኩ ብሎ ቀለደብን ሲሉ መምህራን ተናገሩ የኢትዮጵያ መምህራን የኑሮ ውድነቱ ልንሸከመው ከምንችለው በላይ በመሆኑ መንግስትን የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርግ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። በደምቢያ፣ በደባርቅ እና በሌሎችም የሰሜን ጎንደር ትምህርት ቤቶች መምህራን የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ለጥያቄያቸው መልስ እንዲሰጣቸው ግፊት አድርገዋል። የመምህራኑ የስራ ማቆም አድማ ዛቻ ያሰጋው መንግስት በትምህርት ሚኒስትሩ በአቶ ደመቀ በኩል ባለፈው ሳምንት ፤ መንግስት አጥጋሚ ምላሽ እንደሚሰጥ ...

Read More »

በሶማሊላንድ በርካታ ኢትዮጵያውያን አለቁ

ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ለመጓዝ የሚፈልጉ ስደተኞችን በጫኑ ሁለት ተሽከርካዎች እየተጓዙ በነበረበት ሰአት ላይ ተሽከርካሪዎቹ በመገልበጣቸው በርካቶች አልቀዋል። የሟቾችን ቁጥር በአሀዝ ለማወቅ አልተቻለም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሶማሊላንድና በፑንትላንድ ድንበር አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያኖች በአደጋው መገልበጣቸውን ቢያስታውቅም፣ አሀዙን ከመግለጥ ተቆጥቦአል። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን አስከፊ ኑሮ እና ጭቆና ለመገላገል በርካታ ኢትዮጵያውያን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ አገር ጥለው እየተሰደዱ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርካታ ...

Read More »

አውሮፕላኖች በጨለማ ሲያርፉ አመሹ

የአፍሪካ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መብራት ጠፍቶ በበረራ ላይ የነበሩ አውሮፕላኖች በጨላማ ሲያርፉ ማምሸታቸውን ዘግቧል። ጋዜጣው  ምንጮቹን ጠቅሶ  እንደዘገበው፤ ከትናንት በስቲያ ከቀኑ 11 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2፡34 ሰዓት ድረስ  በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የአውሮፕላን መንደርደርያዎች መብራቶች በመጥፋታቸው፤ አውሮፕላኖች በጨለማ ሲያርፉ አምሽተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን  ለዚህ አሰቃቂ ክስተት ተጠያቂው  የኤርፖርቶች ድርጅት መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለአውሮፕላን መንደርደሪያዎቹ መብራት መጥፋት ምክንያቱ፤ ...

Read More »

በጋምቤላ 17 ሰዎች ተገደሉ ሶስት ሴቶች ተጠለፉ

መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የጋምቤላ የኢሳት ምንጮች በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ ተማሪዎቹ የእረፍት ጊዜያቸውን ጨርሰው  በመጪው ሰኞ በሚጀመረው ትምህርት ላይ ለመገኘት ከጎደሬ ተነስተው ወደ ጋምቤላ ኮሌጅ በማምራት ላይ ነበሩ። ከቀኑ 10 ሰአት ላይ ጀዊ ከተማ ላይ የፌደራል ልዩ ሀይል ልብስ የለበሱት ታጣቂዎች ተማሪዎችን ከአውቶቡሱ እንዲወርዱ አዘው  ያላቸውን ሁሉ ንብረት እንዲያስረክቡ ጠይቀዋል። ጥቂት ቆይቶም ተማሪዎቹ በሆዳቸው እንዲተኙ ...

Read More »

በአወሊያ እንቅስቃሴውን የሚመሩት ሰዎች በደህንነት ሀይሎች እየተዋከቡ ነው

መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የአወሊያ መስኪድን እንቅስቃሴ የሚመሩት የሀይማኖት መሪዎች በደህንነት ሀይሎች እየተዋከቡ ነው የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት በአወልያ የተጀመረውን የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን እንቅስቃሴ በበላይነት የሚያስተባብሩት መሪዎች ካለፈው አርብ ጀምሮ በደህንነት ሀይሎች እየተዋከቡ ነው። ትናንት 7 የደህንነት መኪኖች የተቃውሞው  ዋና መሪ የሚባሉትን የኡስታዝ አቡበክርን መኪና ሲከተሉ ውለዋል። በእየአንዳንዱ መኪና ውስጥም ከ2 እስከ 3 የሚደርሱ የደህንነት አባላት ነበሩ። ዛሬ ...

Read More »

መንግስት ለመምህራን የደሞዝ ጭማሪ አደረገ መምህራን ግን ቀልድ ነው ብለውታል

መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ከመምህራን የተነሳበትን ተቃውሞ ለማብረድ መንግስት በትናንትነው እለት በእያንዳንዱ ደረጃ ላይ ለሚገ  መምህራን አንድ እርከን የደሞዝ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል። ጭማሪው የመንግስትን አቅም ባገናዘበ መልኩ የተፈጸመ መሆኑን መንግስት ተናግሯል። አንድ እረክን ጭማሪ ማለት 50 ብር እስከ 80 ብር የሚያካትት ነው። መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት ግን ጭማሪው በቀን ከ1 ብር ከ50 ሳንቲም አካባቢ ነው፤ ይህም መጠን አንድ ...

Read More »

የግልገል ጊቤ 3 የኤሌክትሪክ ሃይል ግንባታ ችግርን አልጀዚራ እንደዘገበው

መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ የአካባቢ ዉድመት ያስከትላል በተባለዉ አወዛጋቢ የግልገል ጊቤ 3 የኤሌክትሪክ ሃይል ግንባታ ስራ በአሻፈረኝ ባይነት መግፋቷን አልጀዚራ ገለፀ በኦሮሚያ ክልል የሚሰራዉ 243 ሜትር ከፍታ የሚኖረዉ የጊቤ 3 ግድብ ከአለም በትልቅነቱ አንደኛ እንደሆነ የሃይልና የዉሀ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ለአልጄዚራ ቢገልፁም ግድቡ በተገቢዉ ጥናት ላይ ያልተመሰረተና በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ የሚፈሰዉን የኦሞ ወንዝ መጠን በእጅጉ ሊቀንሰዉ ...

Read More »

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ አካሄዱ

መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ/ ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው በእንግድነት በተገኘበት ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገናኝተው ለኢሳት ያላቸውን ድጋፍ ገልጠዋል። የዝግጀቱ አስተባባሪ አቶ እንግዳ ታደሰ ኢሳት ያለበትን የገንዘብ ችግር አውስተው ኢትዮጵያውኑ ኢሳትን በገንዘብ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል። በርካታ ኢትዮጵያውያን ኢሳትን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል። በእለቱ ታዋቂው ድምጻዊ ዳምጠው አየለ እና ሌሎች የሙዚቃ ባለሙያዎች የሙዚቃ ዝጅትም አቅርበዋል። በኖርዌይ እና በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ...

Read More »