(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 19/2010)በብአዴን የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ግንባር ቀደም ተብለው ከሚጠቀሱት አንዱ መሆናቸው የተገለጸው አቶ ተስፋዬ ጌታቸው በሕክምና ላይ እያሉ ሕይወታቸው አለፈ። የብአዴን ጽሕፈት ቤት ሃላፊና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሕዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ አቶ ተስፋዬ ጌታቸው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሕክምና ላይ እያሉ ትላንት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። የብአዴን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ከግንባር ቀደም የለውጥ አራማጆች አንዱ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካ ገቡ።
ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካ ገቡ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) እንደ መንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘገባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋሽንግተን ዳላስ አየር ማረፊያ ሲደርሱ፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃንን ጨምሮ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስ እና በዋሽንግተን ዲ ሲ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ ተብሎ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን 400 የፓርላማ አባላት ቅንጡ መኪና እንዲገዙ ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ዶላር በብድር መልክ መሰጠቱ ህዝባዊ ቁጣ አስነሳ።
የደቡብ ሱዳን 400 የፓርላማ አባላት ቅንጡ መኪና እንዲገዙ ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ዶላር በብድር መልክ መሰጠቱ ህዝባዊ ቁጣ አስነሳ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 19 ቀን 2010 ዓ/ም ) ቢቢሲ እንደዘገበው የሳልቫኪር መንግስት አጠቃላይ ለፓርላማ አባላቱ መኪና መግዣ 16 ሚሊዮን ዶላር ነው ያወጣው። የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ “የፓርላማ አባሎቻችን ሞተር ባይስክል መጠቀም የለባቸውም” በማለት ውሳኔው ትክክል እንደሆነ ለመከላከል ሞክረዋል። የፓርላማ አባላቱ የሳልቫኪር የሥልጣን ...
Read More »ኢንጂነር ስመኘው በቀለ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 19/2010) የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞተው የተገኙት በመስቀል በመስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ መሆኑ ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ እንዳደረገው መረጃ ደግሞ ኢንጂነር ስመኘው የሞቱት በጥይት ተመተው ነው። የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አዲስ አበባ A 29ሺ 722 በሆነው ቶዬታ ላንድ ክሩዘር መኪና ውስጥ በአዲስ አበባ አብዮት አደባባይ ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 19/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ። ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትም አብረው መግባታቸው ተመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቀትር ላይ የኢንጅነር ስመኘውን አሟሟት በተመለከተ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ መርሃ ግብር ተይዟል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫውን ከሚሰጡበት ዋሽንግተን ዋተር ጌት ሆቴል የተገኘው ምናላቸው ስማቸው ከስፍራው የሚከተለውን አድርሶናል።
Read More »በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረው ልዩነት መቋጨቱ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 19/2010) ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው ልዩነት መቋጫ ማግኘቱ ዛሬ በይፋ ተገለጸ። በሽምግልና ጥረቱ የተገኙት አባቶች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በተገኙበት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ለሁለት የተከፈለው ሲኖዶስ ወደ አንድ እንዲመጣ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ከ25 አመታት በኋላ የተሰደዱት ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ከእንግዲህ ሁለት ሲኖዶስ እንደማይኖርና ቤተክርስቲያኒቱ በአንድ ...
Read More »አቶ ደሴ ዳልኬ ከስልጣናቸው ተነሱ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 18/2010)የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደሴ ዳልኬ ከስልጣናቸው ወረዱ። በምትካቸው የቀድሞ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው ትላንት ተመርጠዋል። በቅርቡ በሐዋሳ ከተማ ከተካሄደው ግጭት ጋር ተያይዞ ወደ አካባቢው የተጓዙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአካባቢው ባለስልጣናት በፈቃደኝነት ስልጣን እንዲለቁ መጠየቃቸው ይታወሳል። በሐዋሳና በወላይታ ሶዶ ከተማ በተከታታይ ቀናት የተካሄዱትን ግጭቶች ተከትሎ የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም ...
Read More »የምህረት አዋጁ ሌቦችን አይመለከትም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 18/2010) አዲስ የወጣው የምህረት አዋጅ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩና የተከሰሱ እንዲሁም የተፈረደባቸውን ሰዎች እንደማይጨምር ተገለጸ። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በሙስና ማለትም በሌብነት ወንጀል የሚጠየቁና የተጠየቁ ግለሰቦች የምህረት አዋጁ አይመለከታቸውም። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ብርሃኑ ጸጋዬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እስከ ግንቦት 30/2010 ድረስ ያለውን ጊዜ ብቻ በሚሸፍነው የምሕረት አዋጅ ምህረቱ የሚመለከታቸው ሰዎች ተመዝግበው ሰርተፍኬት መያዝ እንዳለባቸውም ገልጸዋል። በዚህ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ችግር እየፈጠሩ ያሉ አካላት መኖራቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 18/2010)በኢትዮጵያ አሁን እየታየ ያለውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመቀልበስ ሕልም ያነገቡ አካላት በኦሮሚያ ክልል ችግር እየፈጠሩ መሆኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። በባሌ ጎባው ግጭት ውስጥ ከስልጣን የተወገዱ ግለሰቦችና የጸጥታ አካላትም ተሳታፊ መሆናቸው ተመልክቷል። ከዚህ ግጭት ጋር በተያያዘ 35 ሰዎች መያዛቸውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ገልጸዋል። ደምቢ ዶሎ ላይ ነፍሰጡሯን ኢትዮጵያዊ ገድለዋል የተባሉ ሶስት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ...
Read More »በወልዲያና ፍኖተ ሰላም እስር ቤቶች ውጥረት መንገሱ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 18/2010) በወልዲያና ፍኖተ ሰላም እስር ቤቶች ተቃውሞ መቀስቀሱ ተሰማ። የምህረት አዋጁ ላይ አልተካተትንም በሚል የተጀመረው ተቃውሞ ቀጥሎ ወልዲያና ፍኖተ ሰላም የሚገኙ እስር ቤቶች ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውም ተሰምቷል። በፍኖተ ሰላም እስር ቤት የሽመና መስሪያው ቤት መውደሙ ታውቋል። በወልዲያ እሳቱን ለማጥፋት የተጠጋው ነዋሪ በፖሊስ ሃይል መበተኑ ቁጣን አስነስቷል። በተያያዘ ዜና በቃሊንጢ ሌሊቱን የእስረኞች የድረሱልን ...
Read More »