ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል የሥነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሸን በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን (ኮንዶሚኒየም) ለባለዕድለኞች የማሰተላለፍ ሒደት ለሙስናና ብልሹ አሰራር የተጋለጠ መሆኑን በጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡ ኮሚሸኑ ያካሄደውና በቅርቡ ይፋ ያደረገው ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በከተማዋ ዲዛይንና አስተዳደር ልማት ቢሮ ካሉበት ለሙስና የተጋለጡ ችግሮች መካከል ቤቱን ትክክለኛነቱን አረጋግጦ በመፈራረም አያሰረክብም የሚለው ይገኝበታል፡፡ ኮሚሸኑ በጥናቱ እንደአብነት ካነሳው ውስጥ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያዊው የረዥም ርቀት ሯጭ በድራግ ምክንያት ታገደ
ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሌላ በኩል በሮም በተካሄደው የ 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ፋንቱ ማንጌሶ በአስደናቂ ሁኔታ ውድድሩን በማሸነፍ በተመልካቾችና በኮሜንታሮች ዘንድ ልዩ አድናቆትን ጭራለች። እንደ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ አትሌት ህዝቅያስ ሢሳይ ለሁለት ዓመታት ከማናቸውም ውድድሮች የታገደው ባለፈው ዓመት በተካሄደው እና ዘጠነኛ ሆኖ ባጠናቀቀበት የኒውዮርክ ማራቶን ላይ ኤሪትሮፖቲን ወይም በምህፃረ-ቃሉ ኢፒኦ ተብሎ የሚጠራቀውን ሀይል ሰጪ ድራግ ...
Read More »በከምሴ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድዋ እንዳያደርጉ ተከለከሉ
ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በከምሴ ልዩ ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ባለፈው አርብ ሶላት ሊያደርጉ በከተማዋ መሀል አደባባይ በሚገኘው መስጊድ ውስጥ ለመሰባሰብ ጉዞ ሲጀምሩ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት አካባቢውን ተቆጣጥረዋል። ነዋሪዎቹ ከመስጊዱ ግቢ አልፈው በአስፓልቱ ላይ በመቆማቸው የከተማው ትራፊኮች ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱትን መኪኖች ጉዞአቸው እንዲያቆሙ ለማድረግ ተገደዋል። በፌደራል ከባድ ...
Read More »በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን አደረጉ
ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዋሽንግተን ዲሲ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በስዊዘርላንድ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን አካሂደዋል፣ በካናዳም ተመሳሳይ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኣለም ኣቀፍ ጊዜያዊ ኣስተባባሪ ኮሚቴ (Ethiopia Muslims International Adhoc Committee) ለ ሜይ 31 ቀን 2012 ዓ.ም በመላው ኣለም « ድምፃችን ይሰማ » በሚል መሪ ቃል የጠራው አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ አካል የሆነው እና በስዊዘርላንድ ውስጥ ...
Read More »በአዲስ አበባ የሕዝብ ት/ቤቶች በመንግስት ተወረሱ
ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት 117 የህዝብ ትምህርት ቤቶች መካከል 115 ያህሉ ወደ መንግስት ትምህርት ቤትነት በያዝነው ዓመት ተዘዋወሩ፡፡ በህዝብ ይተዳደሩ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ወደ መንግስት የተዛወሩት በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይግለጽ እንጂ ሕዝቡ የት እና መቼ ጥያቄ እንዳቀረበ ያብራራው ነገር የለም፡፡ በህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራንና ...
Read More »ጋናውያን በመጪው ምርጫ ጨዋነት፣ ትእግስትና ብስለት እንዲያሳዩ በጋና የኢትዮጵያ አምባሳደር አሳሰቡ
ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አምባሳደር ጊፍቲ አባስያ ይህን የተናገሩት የግንቦት20ን በአል በኢትዮጵያ ኢምባሲ ተገኝነተው ባከበሩበት ወቅት ነው። አምባሳደሩዋ በግሌ ” የጋና ህዝብ በምርጫ 2012 ከዚህ በፊት ያሳየውን ጨዋነት፣ ብስለትና ታጋሽነት እንዶደግም “ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል። ኢማኑኤል ዶግቤቪ እንደዘገበው አምባሳደሩዋ በጋና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የኢኮኖሚ ግንኙነት የተጠናከረ አለመሆኑንም ተናግረዋል። ጋና በአፍሪካ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ካደረጉ በጣት ከሚቆጠሩ ...
Read More »የቀድሞው የላይቤሪያ መሪ 50 አመት እስር ተፈረደበት
ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘ ሄግ የሚገኘው አለማቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በቻርለስ ቴለር ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት እኤአ ከ1991 እስከ 2002 በሴራሊዮን በተፈጸመው የእርስ በርስ ጦርነት እጃቸው አለበት ተብሎ ነው። የ66 ዓመቱ ቻርለስ ቴለር ወንጀሉን አልፈጸምኩም በማለት ቢከራከሩም ፍርድ ቤቱ ግን አልተቀበለውም። ቻርለስ ቴለር 14 ልጆች እንዳሉዋቸው ይነገራል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቀሪ ዘመናቸውን በእስር ቤት ...
Read More »በሚድሮክ ወርቅ እና በሻኪሶ ህዝብ መካከል ያለው አለመግባባት ድርጅቱን አደጋ ላጥ ጥሎታል ተባለ
ግንቦት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ንብረትነቱ የሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ የሆነውና በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር የሚገኘው ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ በሻኪሶ አካባቢ ሕገወጥ ሠፈራ ይቁምልኝ ሲል ሲያካሂድ የነበረው ሙግት በፊዴራልና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት በኩል ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘቱ ቢዝነሱ ሥጋት ላይ መውደቁን ምንጮች ጠቆመዋል፡፡ ሚድሮክ ወርቅ በሻኪሶ ለገደንቢ አካባቢ ሰዎች ተደራጅተው አነስተኛ ከተማ በመመሥረት ግልጽ ዘረፋ እየፈጸሙብኝ ነው ...
Read More »በሱዳን 4 ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው
ግንቦት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሱዳን ካርቱም ዉስጥ ሶባ ተብሎ በሚጠራዉ ኢትዮጵያዉያን የሚታሰሩበት ቦታ 4 ኢትዮጵያዉያን በፖሊስ ከባድ ድብደባ ደርሶባቸዋል።። ድብደባው ከመብዛቱ የተነሳ 3ቱ ሰዉነታቸዉ ድብደባዉን መቋቋም ተስኖት ራሳቸውን ስተው ሃዋዲስ በሚባለዉ ሆስፒታል ተኝተዋልል።። የቀረዉ 1 ደግሞ ወደ ሆስፒታሉ ሳይደርስ በእስርቤቱ ዉስጥ ሳለ ህይወቱን ማለፉን ምንጮች ገልጠዋል።። በሱዳን የሚገኝዉ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደ ቆሻሻና እንደ አህያ እየታደነ መታፈስ ...
Read More »ወይዘሮ አዜብ መስፍን በሙስና መሬት መውሰዳቸውን ያጋለጠ ሠራተኛ ታሰረ
ግንቦት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማዘጋጃ ቤቱ ሠራተኛ በቅጽል ስማቸው የሙስና እናት ተብለው የሚጠሩትን ወይዘሮ አዜብን ያጋለጠው፤ በቡራዮ ከተማ በተካሄደ እና በአዲስ አበባ ከንቲባ በኩማ ደመቅሳ በተመራ የግምገማ መድረክ ላይ ነው። የቡራዮ ነዋሪዎች ለጋዜጣው ዝግጅት ክፍል እንደተናገሩት፤ የግምገማው መድረክ በቡራዩ አካባቢ የመሬት ቅርምት ተፈጽሟል፤ በመንግስትና በህዝብ መሬት፤ ግለሰቦች አላግባብ በልጽገዋል፤ ከመሬት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ሙስና ተፈጽሟል” ተብሎ ...
Read More »